Friday, August 6, 2010

""ኢትዮጵያ ትቅደም!""

በሚገርም ሁኔታ ""ኢትዮጵያ ትቅደም!"" የሚለው ሀሳብ እስከዚህ ሰዐት ድረስ ; ኢትዮጵያ ትበልጽግ ወይንም ወደፊት ትራመድ ከሚል መልዕክት ውጭ ሌላ ትርጉም ያለው አይመስለኝም ነበር:: አሁን ሳስበው ግን ሀሳቡ ስነምግባራዊ (ethical) መልዕክትም የያዘ ነው::

ስግብግብነት እና ሙስና የማህበራዊ ትስስር ደንባችንን (social norm) እየገዘገዘ ሊጥለው ትንሽ ቀርቶታል በሚባልበት በዚህ ሰዐት ""ኢትዮጵያ ትቅደም"" የሚለውን ሀሳብ እንዳልባሌ እና ካለፈው የደርግ ስርአት ጋር አያይዞ በፖለቲካ መነጸር ማየቱ ትክክል አይደለም::

ያው እኛ አገር ተማርኩ የሚለውንም የህብረተሰብ ክፍል ጨምሮ ሀሳቦች ከፈረንጆች ካልተሰነዘሩ በስተቀር ወይንም የውጭ ምሁራኖች የተናገሯቸው ነገሮች ካልሆኑ በስተቀር ብዙ ቦታ ስለማይሰጣቸው እንጂ "ኢትዮጵያ ትቅደም' የሚለው ሀሳብ ጆን ኤፍ ኬኔዲ '' ሀገሬ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን ምን አደረኩላት ብለህ ጠይቅ"" ብለው ከተናገሩት ነገር ቢበልጥ እንጂ አያንስም:: እንግዲያውስ ""ኢትዮጵያ ትቅደም"" ማለት ለኔ ለኔ አትበል ; አትስገብግብ ; መጀመሪያ ሀገርህን ኢትዮጵያን አስቀድም ማለት ነው:: አገርን ያለማስቀደም እያደረሰ ያለውን ችግር እንግዲህ ወያኔዎች በኢትዮጵያ እያደረሱት ካለው ጥፋት እና እየተከሉት ካለው የስግብግብነት እና የሙስና ባህል የበለጠ ሊያሳየን የሚችል ነገር የለም:: ኢትዮጵያን የሚመሩት ሰዎች ኢትዮጵያን ሳያስቀድሙ ከበታች ያሉት የመስተዳደሩ አካላት እንዴት ኢትዮጵያን ሊያስቀድሙ ይችላሉ???

""ኢትዮጵያ ትቅደም!"" የሚለው ሀሳብ እንደገና መንሰራራት ያለበት ሀሳብ ነው:: ኢትዮጵያ በግለሰቦች ቆዳ አትቀበርም! ዜጎቿ በኢትዮጵያ ቆዳ ይቀበራሉ እንጂ!

1 comment:

  1. "Ethiopia tiqdem" doesn't refer to the land as z derg did rather to the people who have been suffering from illmannered ruling system of the deads.

    ReplyDelete

Blog Archive