"ወጣት ሴት የመሆን ጣጣ" በሚል ርዕስ ሶልያና ሽመልስ አና ማህሌት ፋንታሁን ላስነበቡን ግሩም መጣጥፍ የተሰጠ መልስ ነው። ልክ ጽሁፉን አንብቤ አንደጨረስኩ የተሰማኝን ሳልነካካው አንደወረደ ያነበብኩበት ፌስ ቡክ ገጽ ላይ የሰጠሁትን አስተያየት ነው ትንሽ ማስተካከያ አድርጌ አዚህ ላይ አምጥቼ የለጠፍኩት። ሌላ ጊዜ የራሴንም የነሱንም ጽሁፍ ደግሜ አይቼ የምጨምረውም የምቀንሰውም ነገር ሊኖር ይችላል። ለዛሬ ግን አዛው ላይ የሰጠሁትን ሃሳብ ላካፍል።
መሰረታዊ አና ውይይት የሚያስፈልገው ጉዳይ ወደ አደባባይ ይዛችሁ በመውጣታቸው አድናቆቴን አንገልጻለሁ። በጹሁፉ የተዳሰሱ ጉዳዮች ሰፋ ያለ ውይይትን የሚጋብዙ አንደሆኑ አንድና ሁለት የለውም። ከሴት ልጂ ወይንም ከወንድ ልጂ የህይወት ፍልስፍና አና የአኗኗር ዘየ ጋር ብቻ የተያየዘ ሳይሆን በማህበራዊ ፋይዳውም --ህብረተሰብን ወደ ፊት ለማራመድ ወይ ወደ ኋላ ለመጎተት ሊያሳድር የሚችለውን ተጽዕኖ ግምት ውስጥ በማስገባት መወያያት ያስፈልጋል። ሰፋ አድርገን ስናይ አንደኔ አንደኔ የጽሁፉ ጭብጥ በባህል አና ማህበራዊ አስተሳሰብ ባንድ በኩል አና ፤ በሌላ በኩል ተተኪ የሚባለው ትውልድ ራሱ ከሚፈጥረውም ይሁን ከሌሎች ማህበረሰቦች በፊልም ይሁን በሌሎች የመገኛና ዘዴዎች በሚያገኛቸው አስተሳሰቦች መካከል የሚነሳ ቅራኔን ወይ አለመጣጣምን በወጣት ሴቶች አንጻር የሚያሳየን ጽሁፍ ነው ባይ ነኝ። ጉዳዮ ወደ ርዕዮተ-ዓለማዊ እይታ አይወስድም አይባልም- ሊወስድ ይችላል። በነገራችን ላይ ብሎግ የጀመርኩ ሰሞን ላነሳቸው ከሞከርኳቸው ርዕሶች አንዱ ይሄ ነበር-ምንም አንኳን አዚህ ስላለው ማህበረሰብ ላይ ያተኮረ ቢሆንም። አንድ ጊዜ አንደ ክርክር ምሽት ቢጤም ለማዘጋጀት ሞክረን ነበር በጉዳዮ ላይ።
የዘረዘራችኋቸው ችግሮች መልካቸው ለየት ቢልም አዚህ ሰልጥኗል የሚባለው ማህበረሰብም ውስጥ አሉ። ከሌላ ከሌላው የዕድሜ አና የትዳር ነገር አዚህም አነጋጋሪ ጉዳይ ነው። በሰሜን አሜሪካ በትዳር መረበሽ ምክንያት "ሲንግል ፋሚሊ" የሚሉት ነገር ይበዛል። ዕድሜያቸው ከሰላሳ በላይ ሆኖ ያለትዳር የሚኖሩ ነጠላዎችም ቁጥራቸው የዋዛ አይደለም። በነገራችን ላይ አዚህ ሃገር አንደመጣሁ "quick divorce" የሚል በየቦታው የተለጠፈ ማስታወቂያ ግራ ያጋባኝ ነበር። የጠበቆች ዋነኛ ገበያ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ሰው ማፋታት መሆኑ ነው አንግዲህ። በሌላውም ጉዳይ ይሄ ማህበረሰብ "ሊቲጋንት" የሚባል አይነት ማህበረሰብ ነው። መካሰስ የሚወድ ይመስላል። የ"ህግ የበላይነት" ከመኖሩ ጋር የተያያዘ ነው ወይንስ በሌላ ምክንያት የሚለው "ሶጂዎሎጂካል" ጥናት አና ምርምር የሚያስፈልገው ይመስለኛል። የተጻፉ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ አንደሚችሉ ግን እገምታለሁ።
የፍቺ ቁጥር መብዛቱ የገረመኝን ያህል ከዛም የከፋ ነገር አለ። ከሁሉም የማልረሳው ነብሰጡር የነበረች ባለቤቱን ባሰቃቂ ሁኔታ የገደለም አለ-አዎ አዚ የ"ባህል ተፅዕኖ" በሌለበት ሰልጥኖአል በሚባለው ዓለም። ጉዳዮ ግን የጋዜጣው የፊት ገጽ ዜና ("ፍሮንም ፔጂ ኒውስ") አንደሚሉት አንኳን ለመሆን አልበቃም። አንግዳ ወይም ተከስቶ የማያውቅ ነገር ባለውመሆኑ ይሆን ከርዕሰ ዜናነት የተቀነሰው? ውስጠኛው ገጽ ላይ አንዳነበብኩት ነው የማስታውሰው። 'ቶሮንቶ ስታር' ወይንም 'ቶሮንቶ ሰን' ጋዜጣ ላይ። (አሁንም ጉዳዮ ባይያያዝም ትላንት አንግሊዝ ሃገር ሁለት ልጆቾን ያረደች አናት ሰምተናል።)
አዚህም ያለው የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብም አንደሌላው ማህበረሰብ በጾታ ግንኙነትም ሆነ በትዳር ላይ የሚከሰቱ ውጥንቅጦች ተጠቂ ነው። በማደግ ላይ ባሉ ሃገሮች ነጠላ ቤተሰብ (ልጂን ያለ አባት ወይ ያለ አናት የሚያሳድጉ ) አየበዙ አንደሆነ የሚጠቁም ንባብ አንዳነበብኩም አስታውሳለሁ። በተለይ መንግስታዊ ባልሆኑ የውጭ ድርጂቶች ተቀጥረው የሚሰሩ አናቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ልጆቻቸውን ያላባት ማሳደግ አየተለመደ መጥቶአል የሚል ነገርም ይሰማል። የሚሰሩበት የውጭ ድርጂት ውስጥ አብረዋቸው ከሚሰሯቸው የውጭ ሃገር ሰዎች ( ብዙ ጊዜ አለቆቻቸው ናቸው) አና የንባብ ተጽዕኖ ነው ወይንስ ተወልደው ያደጉበት ማህበረሰብ "የባህል ጫና" ነው ችግሩ የሚለው በርግጥ ጥናት አና ትንታኔ የሚጠይቅ ነገር ነው። ወይንስ ሁለቱም?
ከሌላ ከሌላው ግን የባህልን ተጽዕኖ ስናነሳ በግንኙነት ላይ ችግር የሚፈጥረው ባህላዊ አስተሳሰብ ብቻ ነው ብሎ ማለት የነገሩን ክብደት ማሳነስም ፤ የችግሮቹን ምንጮች በሙሉ አለማየትንም ያስከትላል። ከዚህ ከጽሁፋቸሁ የተረዳሁት ከባህል ጋር በተያያዘ የእኛ ባህል የአብዛኞቹ ችግሮች ፈጣሪ አንደሆነ ተደርጎ የታየ ይመስላል። ለምሳሌ ከታች ኮት ያደረኩኣቸው ግልጽ አይደሉም-
"...በዚህ ላይ የማኅበረሰቡ ግልጽነት ያጣ ጫና እና ማስፈራሪያ ለአንዲት ወጣት ሴት የመረጃ ምንጯ ጓደኞችዋ ብቻ፣ ትክክል የሚሆነውም ብዙዎቹ ጓደኞችዋ ያደረጉት ነገር ይሆናል፡፡ ..."
".... እነዚህ ጠንካራ እሴቶች በመካከለኛ የወጣትነት ዘመን ላይ ሲደረስ በከፍተኛ ተግዳሮቶች እና በተለመዱ ትዳርን የመጨረሻ የሴት ልጅ ስኬት አድርጎ በሚያይ ማኅበረሰባዊ እሴቶች ውስጥ ይዋጣሉ፡፡ ..."
"...እነዚህ ጠንካራ እሴቶች በመካከለኛ የወጣትነት ዘመን ላይ ሲደረስ በከፍተኛ ተግዳሮቶች እና በተለመዱ ትዳርን የመጨረሻ የሴት ልጅ ስኬት አድርጎ በሚያይ ማኅበረሰባዊ እሴቶች ውስጥ ይዋጣሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በሀገራችን ሴት ልጅ በተማረች እና በበቃች ቁጥር ስኬታማ የቤተሰብ እና የትዳር ሕይወት የመመስረት እድሏ ይቀንሳል፡፡... "
የአናንተን ጽሁፍ ተከትሎ ከተሰጠው አስተያየት አንዱ በማህበረሰባችን "ሴት ልጂ ምንም ቫልዮ" አንደሌላት የሚያስመስል ነገርም ተሰንዝሮአል። ታሪካችንም ማህበራዊ ግንኙነታችንም ሙሉ በሙሉ አንደዛ የሚያሳይ አመስለኝም። ተወዳጂ ሚስት፣ተወዳጂ እህት፣ተወዳጂ አናት አና ተወዳጂ ልጂም ጭምር ከሴትነት ውጭ ካየናቸው ሚዛናዊነትን ልናጣ አንችላለን። የሴቶች ተሳትፎንም በተመለከተ በምዕራቡ ዓለም በሚታወቀው መጠን እና ልክ ባይሆንም (በነገራችን ላይ የነሱም ታርክ የግማሽ ምዕት ዓመት ታሪክ ነው) ለሃገራችን ታሪክ አንግዳ ነገር አይደለም። በአኛ ማህበረሰብ ውስጥ "የሴት ወንድ ናት!" የክብር ልብስ ነው። ሴትነቱንም ወንድነቱንም አስተባብረው የያዙ ነበሩ በታሪክም። ርግጥ ነው በ"ፌሚኒስት ፐርስፔክቲቭ" ይሄ ራሱ የሚተች ነገር ሊሆን ይችላል። ትንሽ ወጣ ማለት አንዳይሆንብኝ አንጂ "ሚሊታንት" የሚባለው አይነት "ፌሚኒዝም" ጭራሽ አናትነትን ሁሉ የማይቀበል ነው። ተፈጥሮኣዊነቱን አየሞገተ ልጆች መፈጠር ያለባቸው ከሁለቱም የዘር ፍሬ ተወስዶ በ "ቴስት ቲዮብ" ነው ብሎ አስከማመን አና ለዛም አስከመታገል የሚደርሱ አሉ። ባደኩበትም ማህበረሰብ ውስጥ ቁጥራቸው ባይበዛም የሴት ወንድ የሚባሉ ሴቶችን አውቃለሁ። ከአመራርም ጋር በተያያዘ የዛሬን አያድርገው አና ብርቱካንን አይተናል...የኦብኮ አመራር አባል የነበረችውን አልማዝ አይተናል( ህወሃቶች በጣም ግፍ ፈጸሙባት የሚባል ነገር ብንሰማም)። ስድስት ኪሎ በነበርኩበትም ኪዜ ከወንዶች አመራሮች ጋር አኩል በትጋት ይሰሩ የነበሩ ልጆችን አይተናል። አና ራዕይ ያለው እና ፖለቲካ አንባቢ ላይ የባህል ተፅዕኖ አለ የሚለው ትንሽ ማብራሪያ ያስፈልገዋል ይመስለኛል።
የፖለቲካ አስተሳሰብ ከህብረተሰቡ እምነት አና ባህል ጋር በሚጋጭ ጊዜ የሚፈጠር ተቃውሞ ከሴትነት ጋር ተደርቦ መታየት ያለበት አይመስለኝም። በግሌ ለመናገር ያህል ባባህላዊ አንጻር ለሴቶች የሚገባውን ክብር መስጠት ያስደስተኛል። ልክ ለእናቴ አና ለእህቴ አንደምሰጠው ያለ። ለሴትነት የሚሰጠው አክብሮት በባህላችን መሰረትም አለው። ከ"ፌሚኒዝም" አንጻር ነገሩ ሲነሳ ግን ነገሩን በፖለቲካ መነጸር አንጂ በባህል አንጻር አላየውም። አንደ አሰተሳሰብ አውቅና ከምሰጠው በስተቀር አንዲህ ያለ አስተሳሰብ ለሚያቀነቅኑ የሃገሬ ልጆች የምሰጠው አውነተኛ ክብር የለኝም። የማላከብረው ራስን ከመሆን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ስለማይመስለኝ (ሰለማይመስለኝ!) ነው። ራስ የሚለው ጉዳይ አከራካሪ ሊሆን ይችላል። ከፊልም አና መስል ነገሮች ለሌላ ጉዳይ የተፈጠሩ የካፒታሊስት የፖለቲካ አስተሳሰቦችን እየያዙ "አኔ ይሄ ነኝ" ማህበራዊ አና ባህላዊ አክብሮት ይሰጠው ማለት ያስቸግራል። "እመቤቴ ማርያም" አያለ የሚያምን ማህበረስብ ለሴት አክብሮት የለውም ማለት ድፍን ያለ ነገር አንዳይሆን!
ትንሽ የተነዛበት ፕሮፓጋንዳ ጠንከር ባለ ሚዛናዊነት ስላልተመረመረ አንጂ የአኛ ባህል የትዳርን ተፈጥሮ አና ባህሪ ተረድቶ በ "አንተ ትብስ አንቺ ትብሺ" ዘየ አንዲያዝ የሚገፋፋ አና የማይናቅም ስኬት ያሳየ ነው። ትዳር አና የፍቅር ግንኙነት ውስጥ የህግ አና የፖለቲካ አስተሳሰብ መቀላቀል አና በዛ መመዘን ተፈጥሮውን መንሳት ይመስለኛል። የተቃራኒ ጾታ ግንኙነትም ሆነ ትዳር ስለ መብት አይደለም። አንደዛ ከሆነ ፓለቲካ አና ህግ ሆኖ ቁጭ ይላል። ስለ ፍቅር ነው። የችግሮቹን ምንጮች ስንመረምር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ለማለት ነው።
"ዘመናዊነት"ስ ራሱ የፈጠረው ችግር የለም? ድሮ ኋላ ቀርቶአል ይባል በነበረው ማህበረሰባችን ውስጥ የልጁቹን አናት በ25 ጥይት ደብድቦ የሚገድል ሰው መኖሩን በአጂጉ አጠረጠራለሁ። ከዚህ የወንጀል ድርጊት በፊት የተበላሸ ነገር አለ። አገሌ ነው አገሌ ነው ማለት ጣጣ ውስጥ ሳይገባ በተለያየ መልክ ከውጪ የተቀበልነው ባህል የራሱ የሆነ ድርሻ የለውም ለማለት እቸገራለሁ። በማያቸው የአማርኛ ፊልሞች ላይ የማስተውለው የወንድ አና የሴት ኮንቨርሴሽን አንኳን መመነጫጨቅ ሲንጸባረቅበት ነው የማየው። መመነጫጨቅ ከሌለበትም ልክ አንደውጪው በህዝብ ፊት ያልተለመደ መሳሳም ይስተዋልበታል። ፈጽሞ የባህላችን አይመስልም። አንደዛም አየሆነ አሁንም አንደ ጭራቅ እየታየ ያለው ባህላችን ነው። ባላችን ፍቅር ያልነገሰበት አና ለሴት ልጂ አክብሮት የማይሰጥበት ነበር ማለት ስሜታዊነት አልፍ ሲል ደሞ አላዋቂነት ሊሆን ይችላል። የነገስታቱ የፍቅር ታሪክ ራሱ የሚለው ነገር አለ። የቤተሰብ አና የትዳር ዋጋ ክተጋጋለ ወሲባዊ ስሜት ባነሰ ሁኔት አየታየ የመጣ ይመስላል። ይሄ ከባህላችን ጋር ግንኙነት አለው ማለት ትንሽ ፍርደ ገምድልነት ሊሆን ይችላል። ገበያ ያላችው ጹሁፎችንም ጸሃፍቶችንም እያየን ነው። በወሲብ ዙሪያ አደሚያጠነጥኑ አያየን ነው። አየሰማን ነው። የሙዚቃ ስራዎችም ይዘት አና መልዐክቶቻቸው ስለ ዘመኑ ግንኙነት የሚሉት ነገር አላቸው። ወሲብ ወሲብ ወሲብ።
ትዳር አንደስኬታማነት መለኪያ ቢታይ ችግር የለውም ባይ ነኝ። ነገር ግና ያለጾታ ምርጫ ለወንዱም በሴቱም ነው መለኪያ መሆን ያለበት። ያላገባ ሴት ስኬታማ ካልሆነ ያላገባ ወንድም አንደዛው። በትዳር ውስጥ ሊያጋጥም የሚችልም አለመግባባትም የትዳርን አላስፈላጊነት የሚያመላክት ሊሆን አይችልም። እድሜውን መለኪያ ጨብጦ ሌላ ቁምነገር ሳይሰራ የሚያልፍን ወንድ ማህበረሰቡ አንደችግር ቢያየው የአስተሳሰባችን መሰረቱ( አስካሁን ባለው) ማህበራዊ ስለሆነ አና የግለሰቡ ችግር ብቻ ተደርጎ ስለማይታይ መሆኑ ግምት ውስጥ ሊገባ ይገባል። በተመሳሳይ ሁኔታ ሴቶች ይሄን ነገር ሲያድርጉ ቢታዮ አንደችግር ከመታየት አያመልጥም። በእኛ ባህል። ከማግባት አና ካለማግባት ብቻም ጋር የተያያዘ ሳይሆን ስይገባ የሚሰራውም ነገር የሚወስነው ይመስለኛል። ያላገባች ሴት ስትመነኩስ አንደ ችግር ሊታይ አይችልም። ያላገባም ወንድ ሲመነኩስ አንደችግር ሊታይ አይችልም። የሚሸረሽረው አና የሚፈትነው ማህበራዊ አስተሳሰብ ስለማይኖር። በምንኩስናውም ውስጥ የሚገኝ ማህበራዊ ጥቅም ስለሚኖር። ለትዳር የሚሰጠው ክብር አና ክብደትም ከግለሰቦቹ ባለፈ ከሚያበረከተው ሃገራዊ ድርሻም በመነጨ ነው። ቤተሰብ የህብረተሰብ ቀጣይነት የሚረጋገጥበት አንደኛው መንገድ አይደለ አንዴ? ቤተሰብ ከሌለ የማህበረሰብ መስረቱ ምን ሊሆን ይችላል? የሴተኛ አዳሪነትንት የሚያስተቸው አና ነውር ያድረገው አንደኛው ጉዳይ ሃይማኖታዊ እይታ አና በማይነገድበት ነገር ላይ በመነገዱ ብቻ አይደለም። በቤተሰብ ምስረታ ላይ የራሱም የሆነ አፍራሽ ተጽዕኖ ስላለውም ጭምር ይመስለኛል።
ሰሞኑን ባነበብኩት አደፍርስ ዛሬ "ፊሚኒስት" ሊባሉ የሚችሉ አይነት ሴትን አይቻለሁ- ወይዘሮ አካላትን! (ገጽ 36 አካባቢ ይመስለኛል) አምስት ያህል ባል አግብተው ከአምስቱም አምስት ልጂ ወልደው ከአምስቱም የተፋቱ ናቸው። ግድ የለሽ ናቸው --- ይሄ ነው የሚባል የባሎቻቸው ትዝታ አስከማይኖራቸው ድረስ! ማቴሪያሊስትም ነበሩ ---የዛኑ ያህል ደሞ ማህበረሰባቸውን ወደው አንደማህበረሰባቸውም የኖሩ ናቸው በሌላ ገጽታው። "አደፍርስ" ላይ ከተነሱት ጠቃሚ ማህበራዊ ጉዳዮች አንዱ የግንኙነት አና የትዳር ጉዳይ ነው። የትዳርን መሰረት ምንነት በዘመናዊ ትምህርት የተገኘ እውቀትን ክማህበራዊ አስተሳሰብ አና ባህል ጋር አዋዶ ሳያጣላቸው ጥሩ አድርጎ አስቀምጦታል። ቁንጂና የሚባለውንም ነገር ልቅም አድርጎ ስሎታል! አዛ ላይ ያሉት አንስቶች ቆንጆቆች ነበሩ። ቁንጂናቸው ግን ከኮስሞቲክስ ስና መሰል ጉዳዮች ጋር ያልተያያዙ ነበሩ። አንዳንዴ የአኛን ማሀበረስብ በሌላ ማህበረስብ ከመስፈራችን በፊት መጽሃፉ ላይ አንደሚንጸባረቀው ያለንን አና የሌለንን በጥሞና ብናጤናቸው ጥሩ ይመስለኛል። ያለ በለዚያ ብዙ አደፍርሶች አሉ። ከውጪ አየተጫነበን ያለው ነገር በራሱ አደፍርስ ነው። ለማንኛውም ከዚህም ሰፋ ያለ መስል ስለሚያስፈልግ ጊዜ አንደፈቀደ አመለስበት ይሆናል። በድጋሚ ጂምሩ ግን ጥሩ ነው።
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
Blog Archive
- April (18)
- May (8)
- June (2)
- July (1)
- October (2)
- December (7)
- March (1)
- July (1)
- August (1)
- January (5)
- February (3)
- March (2)
- June (2)
- April (3)
- May (3)
- August (2)
- September (1)
- October (3)
- November (4)
- December (4)
- January (4)
- February (3)
- March (8)
- April (2)
- May (2)
- June (1)
- December (2)
- January (2)
- February (1)
- May (2)
- July (4)
- September (1)
- October (2)
- November (1)
- September (1)
- December (1)
- December (1)
No comments:
Post a Comment