Thursday, October 25, 2012

አቶ ኃይለማርያም ባልዋሉበት “ኩበት” ለቀማ


አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን ተሰጥቶኣቸው ከተቀበሉ ወዲህ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደር በኢትዮጵያ ዴቪድ ሽን
በኢትዮጵያ ስላለው የፓለቲካ ሁኔታ ያላቸውን አስተያየት ይሁን፣ ሃሳብ ይሁን ፣መረጃ ባልለየለት መልኩ ገለጻ ቢጤ አድርገው ነበር። በኢትዮጵያ አዝጋሚ ለውጥ አንጂ ለውጥ አይኖርም ሲሉ ተናግረዋል። ምናልባት በሚስጥራዊ መርጃ ላይ የተመሰረተ ትንበያ ይሆናል ፤ ወይንም ደሞ ውስጥ ለውጥ የሚሄደው የለውጥ አንቃቃሴ ገንፍሎ መጀመሪያ የህወህትን አስተዳደር ፈንግሎ ለነሱም ሌላ ስራ አንዳይሰጣቸው በማሰብ ለማሸማቀቅ፣ስነ-ልቦና ለመስበር አና በወሬ ለመፍታት ተብሎ የተሰጠ ሃሳብ ሊሆን ይችላል። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፓርላማም ከፓርላማ ውጪም በተያዮ ቃለመጠይቆች የሰጡት ሃሳብ ከአምባሳደሩ ሃሳብ ጋር ሙሉ ለሙሉ የማይመሳሰሉ ቢሆንም የአምባሳደሩን ሃሳቦች የሚያጠናክሩ ይመስላሉ። ለአቶ ኃይለማርያም “ለውጥ አይኖርም!” -አዝጋሚም ቢሆን። ሃሳባቸው “የታላቁን መሪ ራዕይ” ማስፈጸም ብቻ ነው።

“የታላቁን መሪ ራዐይ ብቻ ነው የማስፈጽመው” የሚለው አስተሳሰብ የሚያስነሳቸው ስነ-አመንክዮዓዊ ጥያቄዎች አና አንድምታ በውል የተጤነ አይመስልም። ምንም ጉዳዮ ግልጽ ቢሆን አቶ ኃይለማርያምም ሆነ አብረዋቸው ከህወሃት/ኢሃዴግ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች አስተሳሰቡን በማስተጋባት አየመሰከሩት ያሉት ነገር መለስ ዜናዊ በራሱ አድራጊ ፈጣሪ ነበር የሚለውን ክስ ነው። በራሱ መንግስት ነበር አንደማለት ነው። የፈረንሳይ አብዮት ሰበብ ሆኖ አንገቱን ለ “ጊሎቲን” የሰጠው ሊዊ አስራ ስድስተኛ አንዲሁ ነበር የሚያስበው - “መንግስት ማለት አኔ ነኝ”። አነ ቢስማርክም፣ አነ ሞሶሎኒም፣ አነ ሂትለርም፣ አነ ናፖሊዮንም በምግባራቸውም ቢሆን ከዚህ ተመሳሳይ የሆነ አስተሳሰብ ይንጸባርቅባቸው ነበር። የመለስ ዜናዊ ጉዳይ ግን የሚለይበት አብይ ነጥብ አለ። መለስ ዜናዊ ህወህት ውስጥ ገነው ተጽዕኖ ፈጣሪ ቢሆኑም ቅሉ በህወሃት ውስጥ ተፆዕኖ የመፍጠር ኣቅማቸው መሰረት የነበረው ለህወሃት የፖለቲካ ቡድን በሃልዮም በገቢርም የነበራቸው ታማኝነት ነው። አንደፊተኞቹ የስልጣናቸው መሰረት ብሄራዊነት አልነበረም። ያ ማለት የመለስ የሚባለው ራዕይ የህወሃት "ራዕይ" ነው ማለት ነው። ከመለስ በኋላ ሌላ መልክ ተሰጥቷቸው የመለስ ናቸው የተባሉትን "ራዕዮች" ህውሀት በብቃት መርምሮ ተቀብሎኣል አልተቀበለም የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ ፤ መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመኑ በራሱ የአስተሳሰብ አቅም ብቻ መራ ማለትም ደሞ ከአላዋቂነት ይቆጠራል። አንደኛ ነገር የመለስ "ራዕይ" ከውጭ የኢኮኖሚ እርዳታ ጋር ወይንም ያለ ኢኮኖሚ ርዳታም ከሚጫኑ ሃሳቦች አና አንዳንዴ ቀጭን ትዕዛዝም ጭምር ነጻ ነበር ማለት “ከነባራዊ” ( ነባራዊ ማለት ፍትሃዊ ማለት አንዳልሆነ አየተስተዋለ) ሁኔታ መራቅ ነው የሚሆነው ። ሁለተኛ ነገር መለስ ዜናዊ ህወሃት ውስጥ ካሉ የአመራር ጓደኞቹ አልፎ አልፎም ቢሆን ተቃውሞም ይገጥመው አንደነበር ይነገራል። ህወህት ከአስር አመት በፊት ተራብሾ “የመለስ” የተባለው ሃሳብ አሸንፎ የሚባረሩት ከተባረሩ በኋላ አንኳ በተነሱ ውዝግቦች ምክንያት ለግድያ የሚፈልጉት ህውሃቶች አንደነበሩም ይነገራል። እርግጥ ባለፈው ምርጫ ተወልዶ ባደገበት ሃገር -አድዋ- ደርሶ ለመምጣት የነበረውን የሴኪዮሪቲ አጀብ ያየ ፣ በምርጫው ማግስት ከአንድ ወንበር በስተቀር ሁሉንም የፓርላማ ወንበር አሸነፍን በማለት መለስ ዜናዊ ጥይት በማይበሳው ሳጥን ውስጥ ለአራት አና አምስት ደቂቃ ንግግር አስኪያደርግ ድረስ የነበረውን ጭንቅ ላስተዋለ በትክክልም ከራሱ(የህወሃት) ጓደኞችም ጭምር ራስ ምታት የሆኑበት ሰዎች አንደነበሩ ይጠቁማል። በህወሃት ውስጥ ይሁንታቸውን ያገኘ ወገኖች ቢኖርሙ የራሱን “ራዕይ” ብቻ በመጫን ይሁንታቸውን አገኘ ማለት ያስቸግራል። ስነ-ልቦናቸውን በማጥናት ቢያንስ የነሱን “ራዕይ” የሚመስል ነገር በጽናት አንደሚያምን በሆነ መልኩ ሲያሳይ ነው የስልጣኑ መሰረት የሆነውን ህወሃትን የመጫወቻ ካርድ ሊያደርግ የሚችለው። ስለዚህ የ “ራዕዮ” የፖለቲካ ባለቤት ህወሃት ነው ማለት ነው።አቶ ኃይለማርያምም ሆኑ ሎሎች “የእህት” ድርጂት አባሎች “የታላቁን መሪ ራዕይ” አንቀይርም ሲሉ ለማለት ያህል አንጂ ነገ ህወሃት ብድግ ብሎ አጀንዳውን ከነስትራቴጂው ቢቀይር የ”እህት”ድርጂት አባሎች አና አመራሮቻቸው ይሄኛው “የታላቁ መሪ ራዕይ” ጋር ይጋጫል ብለው ያስቆማሉ ማለት አይደለም። ከህወሃት ውጭ ካሉት ያመራር አካላት የተወሰነ ጥንካሬ ገንብቶአል አየተባለ የሚነገርለት አቶ በረከት ስምዖንም ለማስመሰል ካልሆነ በስተቀር በውኑ ከህወሃት ተጻራሪ የሆነ ግብ አለው ለማለት የሚያስችሉ ተጨባጭ አና አሳማኝ ጠቋሚዎች የሉም። ምናልባት ከህወሃት ይልቅ ማልያውን ለብሶ ለሚጫወትለት አና ለሚጫወትበት “አህት” ድርጅት ተጻራሪ የሆነ የፖለቲካ አጀንዳ አና ፍላጎት ይኖረው ይሆናል። ጭራሽ ሰሞኑን በኤርትራውያን የፓልቶክ ሩም በሌሊት ቁጭ ብሎ ይወያይ አንደነበረም ይነገራል። ይሄ ታዲያ ህወህት ውስጥ ሁለት ቡድን አለ የሚለውን ነገር ያጠናክር አንደሆነ አንጂ በረከት በትክክል ለብአዴን አንደሚጫወት አያሳይም። ምናልባት መለስ አና በረከት ተመሳሳይ የሆነ “ራዕይ” ኖሮአቸው ሊሆን ይችላል።

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም በመለስ በኩል ይንጸባርቅ በነበረው የህወሃት የፖለቲካ አጀንዳ አና “ራዕይ” አምነው ተጠምቀው ነው ወደ መንበሩ ጠጋ ተደርገው ተቀምጠው የነበረው። መደባዊ ጀርባቸው ተጠንቶ፣ ለጎሳ ፓለቲካ ያላቸው ታማኝነት ተጠንቶ፣ለህወሃት ፓለቲካ ያላቸው ታማኝነት ተጠንቶ፣ በፓለቲካ አንጻር የሰውየውን ሃሳብ መነካካት ይቻል አንደሆነ አና አንዳልሆነ ተጠንቶ፣ በፍጹም ስጋት ሊሆን የማይችል የፖለቲካ መፈናፈኛ ( ፖለቲካል ቤዝ) አንደሌላቸው ተጠንቶ ነው የተሰጣቸው የፓለቲካ ቦታ የስጣቸው። አንድ ብሎግ ላይ አንዳነበብኩት ሰውየው አግር ላይ ተወርዋሪ ነበሩ ይባላል። ፊንላንድ ሃገር የትምህርት ኦድል ተገኝቾ በእድሉ ተጠቃሚ አንዲሆኑ አንደተመረጡ በአስተዳደሩ ሲነገራቸው ተወርውረው አግር ስል ለጥ ብለዋል ይባላል። ወላይታ ተወልዶ ያደገ ሰው ምንም “ቦርን አጌይን” ቢሆን አንዳደገበት ልምዳ “ወላይታ ላይታ!” ብሎ ወደ ላይ ካልዘለለ ምን ዋጋ አለው?! : ) ወሳኝ በሆነ ትግል አና ውሳኔ በሚጠይቅ ሃገራዊ ጉዳይ ላይ ጠላትን ለመጥለፍ ካልሆነ በስተቀር አግር ስር በመወርወር የሚፈጠር ነገር የለም። ህወሃትም የወደዳቸው በተወርዋሪነታቸው አንደሆነ አገምታለሁ። ህወሃት አጂ የሚነሳውን አንደነብሱም ባይወደው አይጠላውም።

አቶ ኃይለማርያም በዕጩነት አና በምክትልነት ዘመናቸው የዋሉት ከሟቹ ቅላይ ሚኒስትር አግር ስር ነው። የዋሉት ከህወህት ጋር ነው። ኣቶ ኃይለማርያም የሟቹን ጠቅላይ ሚኒስትር ባህሪ “ሳያላምጡ አንደዋጡት” ገና በመጀመሪያው የጠቅላይ ሚኒስትርነት የፓርላማ ውሏቸው ለማየት ችለናል። አማተር አና አድል ካገኘ ሊያድግ የሚችል የአምባ ገነንነት ዝንባሌ አሳይተዋል። በዚህ ባሳዮት ተፈጥሮአዊ በማይመስል የአምባገነንነት ዝንባሌያቸው ከሊቅ አስከ ደቂቅ ነው የተሳለቀባቸው። ፕሮፌስር መስፍን “ራሱን ፈልጎ ያግኝ” አሏቸው። በጨዋኛ ባይናገሩት ኖሮ በሌላ አነጋገር “አይረባም” ማለታቸው ነው! በባርነት መንፈስ እና ባርነት ዓለም እየኖረ ያለ ሰው ነው ማለታቸው ይመስለኛል። በፌስ ቡክ አንዲሁ ያልተጻፈ ነገር የለም። በበኩሌ ከመለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት በፊት በምክትልነት አና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ወደ ስልጣን ሊመጡ የቻሉበትን ሁኔታ አና ከመለስ ዜናዊ ስርዐተ ቀብር ጋር ተያይዞ የነበረውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት ከአቶ ኃይለማርያም የፖለቲካ “ኩበት” ይለቀማል የሚል ነገር አልጠበኩም ነበር። ባለመለቀሙም አልተገረምኩም። የዋሉበትን ስለምናውቅ። የ”በሳሉን መሪ ራዕይ” በየፈርጁ አየሞካከሩት አንደሆነም አይተናል። ሰሞኑን ገርባ ባቲ ኣካባቢ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ የተወሰደው የግፍ ርምጃ የሚያመላክተውም ሁለት ነገር ነው። አቶ ኃይለማርያም ወይ በትክክል የ”ባለ ራዕዮን መሪ” ፈለግ በግድያውም በአፈናውም መስክ ለማስቀጠል አስበዋል። ወይ ደሞ አንዲ ያለውን ቅጥ ያጣ ህገ-ወጥ ግድያ አንዳይከሰት ለማድረግ አና ለማስቆም የፓለቲካ ስልጣን አና ጉልበት የላቸውም ማለት ነው። ሁለቱም ደሞ አደገኛ ነው። በሌላ በኩል ግን አቶ ኃይለማርያም አንዲህ የተልፈሰፈሱት ኃይለማርያም ስለሆኑ ነው ብሎ ለማመን ያስቸግራል። ደቻሳም ቢሆን ፣ዓለሙም ቢሆን ፣አያሌውም ቢሆን ፣ከድርም ቢሆን፣ተማም ቢሆን የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ተወግዶ በተጠያቂነት አና በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ ተቋማዊ ነጻነት አና የስራ አመራር ባህል እስካልተፈተረ ድረስ ይሄው ነው። ብአዴን ቢመጣ ኦህዴድ ቢመጣ ደህዴን ቢመጣ የሚለወጥ ነገር አይኖርም። ጠንከር ያለ ለለውጥ የተዘጋጀ - አስከ ሞት የቆረጠ -ጠቅላይ ሚኒስተር ስልጣን አገኘ ማለት የህወሃት የበላይነት እና ፈላጭ ቆራጭነት ፍላጎት ፈተና ይገጥመዋል ማለት ስለሆነ! ህወህት የበላይነቱን ለማሰጠበቅ የፈጠራቸው የመንግስት ስልጣን አደረጃጀት አና ተቋማት ዛሬም በሙሉ ሃይላቸው አሉ። የጎደለው ጠቅላይ ሚኒስተር ነበር። ሊቆጣጠሩት የሚችሉትን ሰው አስቀምጠውበታል። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ሳይዳከም ለውጥ አይመጣም። የህወሃት ፈላጭ ቆራጭነት መሰረቱ ደሞ ከምንም በላይ ወታደራዊ ሃይሉ ላይ የተመሰረተ አንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው። በደህነንት ቢሮ ያሉትን የህወሃት አመራሮች ከታች ያሉት ማዳክም የሚችሉበትን አጋጣሚ አና ሁኔታ ተጠቅመው አስካላዳከሙት ደረስ የህወሃት የስልጣን የበላይነት ትርጉም ባለው ሁኔታ እክል ሊገጥመው አይችልም።

ከዚያ መልስ ከአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ መልቀም ስላልተቻለው የፖለቲካ “ኩበት” ስናወራ -ኩበት በዚህ ሰዓት ይጠቅማል ወይ? "ከኩበት" የተሻለ ነገር አይገባንም ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ ነው። ሌላ ሌላውን ትተን መሰረታዊ የሆነ ህገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ያስፈልጋል፣ የፍትህ ስርዕቱ የፍትህ ስርእት መመስልም መሆንም አለበት፣ የነጻው ፕሬስና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ህዳሴ አንመራለን አየተባለ በመካከለኛው ዘመን አና ከዛ በፊት ከነበረው አንደነበረው በሰይፍ አና በሰደፍ መያዝ የለበትም። አነኚህ ወሳኝ ርምጃዎች በአዝጋሚ ለውጥ ይመጣሉ ብየ አላስብም። የአዝጋሚ ለውጥ ዲስኩር (ፍላጎት ካለ ፍላጎትም) ጭራሽ ወደማይቀልበስ የባርነት ዓለም አና ዘመን የመውሰጃ ከፓለቲካ ዘዴ ሊሆን ይችላል። ከአዝጋሚ ለውጥ “ኩበት”አንኳን ይገኛል ብየ አላስብም። የሙስሊም ኢትዮጵያውያኖች ትግል አንግበው ለተንሱት ዓላማ አያስገኘ ያለውን የለውጥ ፍንጭ አያየን ነው። ህወሃት በድንጋጤውም መሃል ቆም ብሎ ሲያስበው የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ጥያቄ ባለመመለስ አና በማወሳሰብ የሚያመጣው የፓለቲካ ኪሳራ ጥያቂያቸውን በመመለስ ከሚደርስበት ኪሳራ ያነስ መስሎ ስለተሰማው ይመስለኛል። እውነትም ደሞ የመጀመሪያው ዋጋ ከዋለ ካደረ አይቀመስም። ጥያቄያቸውን በማስመለስ ሂደት በተዘዋዋሪ ህወሃት በመሰረታዊ ሁኔታ አንዲዳከም አስተቃጾ የሚያደርግበት ሁኔታ ስለሚፈጥር። ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓለቲካ መሪዎች ዘብጥያ ሲጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የፈጠሩትን ዓይነት ጫና መፍጠር ስላልተቻለ አንኳን መሰረታዊ የፕሬስ ነጻነት አና በነጻነት ያለገደብ የመደራጀት መብት የሚከበርበት ፍንጭ ሊገኝ ቀርቶ የታሰሩትን ጋዜጠኞች አና የፓለቲካ መሪዎች ማስፈታት አንኳን አልተቻለም። ጭራሽ መብታቸው ተረግጦ ያላግባብ አስር ቤት የተጣሉ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ድረስ “አሸባሪ” አየተባሉ አየተፌዘባቸው ነው ያለው። አቶ ኃይለማርያምም ፌዙን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ማዕረግ አያስተጋቡት ነው።

በህወሃት/ኢሃዴግ በኩል የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” የሚባለው የፖለቲካ ድንቁርና ነጠላ ዜማ እያደረሰ ያለውን ጥፋት መስፈርም የቻሉ አይመስሉም። የመለስ ዜናዊን መሞት ህውሀትን በግልጽ እንደጎዳው ከሚያመላክቱ ጉዳዮች አንዱ ሆኖ አግኝቸዋለሁ። ከላይ ለመግለጽ አንደሞከርኩት ህወሃት ሲፈጠር ይዞ የተነሳው የህወሃት የሚለው “ራዕይ” ነበረው። ነበርን( አለንም?) ለሚሉትም ራዕይ ብዙ “ታጋዮች አንደተሰውባቸው” አና “የተሰው ታጋዮች” መማያ መገዘቻ አንደሆኑም አይተናል። ሰምተናል። ምንም ይሁን ምን ተሰው የተባሉት በለጋነት እድሜ የተሰውት “ለበሳሉ መሪ ራዕይ” አይመስለኝም። መለስ ዜናዊ በልጂነታቸው “ከተሰው”ታጋዮች ጋር ሲነጻጸር አንደ ሃገር መሪ ሳይሆን በግላቸው የተሻለ ዓለም አይተው ነው የሞቱት። የጫካ የተባለውን ትግል ጨርሰው ከዛ በኋላ ትምርህርታቸውን ተምረው ጨርሰዋል። አንኳን ራሳቸው ልጆቻቸውን የታጋይ ሳይሆን “የሞላው የደላው” የሚባሉ አይነት ሰዎች የሚያስተምሩትበት ውድ ትምህርት ቤት ውጪ ሃገር ድረስ ልከው ያስተማሩ ናቸው። “አንድ ቀን ሳያርፉ” ሞቱ የሚባልላቸው አይነት ሰው አይደሉም። በአንድ ጀምበር ታግለንታል የተባለው ነገርም “ተሰው” የተባሉትም ታጋዮች ተረስተው ሞቶም መለስ መለስ ሲባል መዋሉ ከፖለቲካ ባዶነት በስተቀር ሌላ የሚያሳየው ነገር የለም። መለስ ዜናዊ በኣካል ቢኖር ይህ አንዲደረግ ይፈቅዳል ብየ ኣላስብም። መለስ ዜናዊ የፖለቲካ መሰሪ አንጂ ሞኝ አልነበረም እና! ከበቀለበት የተጋጋበት አንዲሉ የ”በሳሉ መሪ ራዕይ” ዜማ ከህወሃት አባላት በእህት ድርጂቶች የፓለቲካ አላዋቂዎች አና መሪዎች ይበልጥ ተዜመ! በአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝም ተሰማ። ችግሩ የለውጥ ጥያቄ ማድበስበሻ ሆኖ ለረዢም ጊዜ ሊቆይ አይችልም። በውሽት ላይ የተመሰረተ ፐሮፓጋንዳ ስር ሊይዝ አይችልም።አንዴት ይሄን ማየት አቃታቸው?!

No comments:

Post a Comment

Blog Archive