Sunday, April 12, 2009

ናፍቆት

ናፍቆት

አሁን እዚህ ሆኘ ከሰው ጋ እያወራሁ
ወሬውን ዘንግቸ እኔ ነጉጃለሁ
"እዚህ ' እና 'አሁኔን ' 'ያ ' እና 'ትላንት ' ነጥቀው
አገር ቤት ወሰዱኝ ድንገት አንከብክበው
እነሱን ገፍትሬ ወደ ""አሁን -እዚህ "" ስመለስ
እንደቀጠለ ነው ወሬው ሳይደፈርስ
እኔም የመንተፍረት የት ሄደ እንዳልባል
ትክ ብየ ማየት ያዳመጥኩ ይመስል
ግን ምን አበረታው "ትላንትን " እንደዚህ
""አሁንን "" ቀምቶ የሚወስደው ከዚህ
እርጂናም ቢጫነው እንደዛሬም ባይሆን
የ 'ትላንት ' ጉልበቱ በናፍቆት ላይ ቢሆን
ትላንትም ቢደክም መች ይተኛል ነገ
እንዲሁ በተራው ሊወስደኝ ፈለገ
እሱ ግን ተሻለ ተስፋ ስላዘለ
የመሆን እድሉ ከትላንት ያየለ
እንደዚያ ከሆነ ትላንትን ቀንሶ
....ዛሬ ላይ መከተም
እሱን እየንኖሩ ነገን ለመተለም

ጥቅምት 2, 2001 ዓመተ ምህረት

No comments:

Post a Comment

Blog Archive