Thursday, April 9, 2009

ዘመነ ጭልፊት

ቀናዒ ልቦና
አስተዋይ ህሊና
ጭልፊት መሪ ሆኖ
ማዕረጉን አጣና ;
ጆቢራም በዛና
ዐይን ባይን ሆነ
ድንገት አዘናግቶ
መሞጭለፍ ሆነና ;
የሰው ልጂ መለያ
ፈጣሪ የሰራው
በራሱ አምሳያ
በጎ ስራ ; ፍቅር ሞቶ ;
እንዳይን ጠፍቶ
እኩይ ግብር ; ጭካኔ
በሰው ልጂ እሳቤ ግዛቱን አስፋፍቶ
የፈጣሪም አምሳል ተረስቶ ;
በሰላም አገር ሳይጠር ; ሳይጠና ቆሪሩ
እኩይ ግብር ; ውሸት ብሶ በፈራሚው ;በባለወንበሩ
ሲያጋፍር ስርቆቱን ሳይነቃነቅ ከመንበሩ
ሕግም ጥላ ሆኖላቸው ሕዝብ ሲመዘብሩ
ጭራሽ በሰረቀዉ ; ለሚሰርቅበትም ማይረጉ
ያገር ልጆች ጠባቂ ወታደር ሲደረጉ
ሌባነቱን እንዲረሱ ሆነው ;ታጥቀው ለሌባ ሲያደገድጉ
""የለም ! ይኼ ሌባ ነው ያሉ "" ሲገደሉ ; ሲወገሩ
በጠራራ ፀሀይ በሐሩሩ
ሌቦች ሲሾሙ ;ሲከበሩ
ምን ሊያሳስት !
ይኼማ ነው ዘመነ ጭልፊት !!
ኤሎሄ ለሚል ኤሎሄ 'ሚልበት ::

ሕብረት ሙሾ ታውርድ
ጎበዝ ግን ይነሳ
እንባዋን በመጥረግ
ዘመኑን ለመናድ
ሞጭላፋ እንዲቀጣ
በሰረቀው ነገር መጀነኑ ቀርቶ
በውል እንዲዋረድ !!

መጋቢት 16, 2001, ዓ . ም
ቶሮንቶ

No comments:

Post a Comment

Blog Archive