Friday, May 8, 2009

ለውብ ልጂ ከልብ በላይ ምን ይሰጣል?

አንዳንዴ የወደደ ሞኝ አይደል!
የመውደዴን ልክ ላሳይ ባስብ
ቀን ቀን ሳልጋደም በሀሳብ
ሌሊት ተኝቼ በምናብ
ሰርቼ ግድንግድ የፍቅር ግንብ
ልቤም ከትሞ በሷ ልብ
እኔ በሀሳብ ላይ;ሀሳብ በእኔ ላይ ሆነን
ሳስብ..ሳስብ...ሳስብ...
በሀሳብ ...
አንዴ በስሟ ትንሽዬ መጽሀፍ ስጽፍ
አንዴ ወጣ ብለን ጥሩ የዕረፍት ጊዜ ስናሳልፍ
መውደዴ እስኪገባት አለቅም ብዬ ዓይን ዓይኗን ሳያት
ድምጽ አልባ ሆኘ በዐይኔ ስለፍቅሯ ሳዜምላት
ቁንጂናዋን አንድ ባንድ ሳሳያት
ራሴን ያለፈቃዷ ሾሜ እንደውበቷ ነገረፈጂ
የኔ"'ሚስ ወርልድ"" እሷ ነች ብዬ ላውጂ
የሷን ደስታ; የሷን ስኬት እንደምመኝ ልነግራት ስዘጋጂ
ለካስ ናት ፍቅር የማትፈልግ ቆንጆ ልጂ::

ልጠይቅ እንጂ ፍቅር የያዘው ሞኝ አይደል!
ለውብ ልጂ
ለባለ ፀዳል ከልብ እና ከፍቅር በላይ ምን ይሰጣል?!

(የማትወደውን ለወደደ)
ሚያዚያ 6, 2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ

No comments:

Post a Comment

Blog Archive