Friday, October 9, 2009

አለ አንዳንድ ሰዐት

አለ እኮ አንዳንድ ሰዐት
ለራስ የሀሴት መለከት የሚነፉበት
ከራስ ጋር በሰላም በፍቅር የሚጫወቱበት
አሁንን የሚያጣጥሙበት
ነገር ዓለሙን ረስቶ
አሮጌ ፋይል ዘግቶ
ቀልብን ለሀሴት አመቻችቶ
በቃ ነገር ዓለሙን ትቶ
......ጉራንጉሩን ረስቶ
ልብ እና መንፈስን አስማምቶ
ትላንት እና ነገን ወርውሮ
አሁንን በአሁን አጥሮ
እንዲሁ... በአሁን መደመም
ትላንት ሳይታሰብ...ነገ ሳይታለም
እንዲህ ያለ ሰዐት አያስደስትም!

ጥቅምት 2, 2002 ዓ.ም

ሀሚልተን

No comments:

Post a Comment

Blog Archive