Tuesday, June 9, 2009

የቀለም ውድነት :

ቀለም ; ሆድ ; መኝታው በብላሽ ተለምዶ
እነ አጂሮች አገር ሰው አለቀ ነዶ
አቅም የለኝም ላለ ለቀለም ለመክፈል
ምንም ችግር የለም
የባንክ አካውንቱ ኪሱ ተበርብሮ አራጣ ይሰጣል
ደሞ ወግ አይቀርም "እርዳታ ' ይሉታል ::
እንደዛች ያላትን ሁለት ዲናር እንደሰጠቺው
ያላትን አንጠፍጥፋ ; ሲያጥራት ተበድራ ያስተማረችው
እምየ ኢትዮጵያ -ሀገሬስ ምን ትበል ?!
እንዲያ እየተራበች ለዛ ሁሉ ማቲ ;ለዛ ሁሉ ፍልፍል
የከፍተኛ ትምርት እንዲሁ ስታድል
ኢትዮጵያ ምን ትበል ?
ወይ አንቺ እናት ዓለም
ጉዱን ብትሰሚ የሰለጠነውን የቱጃሩን ዓለም
የተማሪ ጥሬ -ስጋ እየበላ ገንዘብ እንደሚለቅም
ወይ ነጻ ዓለም !
ሰው ትምርት ሲራብ
ቅጥ ባጣ ዋጋ የሚቸበችብ !
ለነገሩ መጽሐፉ እንዳለው
ጽድቅ ለባለ ጠጋ አይቀልም
ግመልም በመርፌ ቀዳዳ አይሾልክም ::

ሰኔ 1,2001 ዓ .ም

ቶሮንቶ

የማይመለከታቸው አገሮች አሉ -ስካንዴቪያን አገሮች በአብነት ይጠቀሳሉ ::

No comments:

Post a Comment

Blog Archive