Sunday, April 5, 2009

የመርካቶ ቸርቻሪ

የመርካቶ ቸርቻሪ


ሸቀጥ አልባ ቸርቻሪ
ድብርት ዱካክ ያናወዘው ዘዋሪ
ተገኘ መርካቶ ኬኔዲ ላይብራሪ
ዱካኩን ሊያባርር
ወሬውን ይዞ ሲያዘዋውር
እነ ቤቲ አዩትና
ጠሩት ...ዳኒ ናና ..ና
ምላሱ ጫፍ ላይ የደረሰውን
የቅምቀማውን የፊልሙን
ወሬ ሊካፈሉት
ዙሪያውን ከበቡት ::
ወሬው እንደተጀመረ
ሁካታው የመርካቶውን መርካቶ ተወዳደረ
ያኔ ጨምጫሚው ቀና ብሎ ገልመጥ
ወግ ጠራቂውም 'አቦ ተወና አርፈህ ተቀመጥ '
አጣራቂዎቹም አብረው ማፍጠጥ
የሁሉም ዐይን ጎረጥረጥ
ጨምጫሚው ቦታ እንዳይቀይር
በጠፋ ወንበር
ዳኒም አጣራቂዎቹም የሚፈልጉት ነገር
ከዚያ ጨምጫሚውም ማጉረምገም
'ሁሉም እኮ አለው የራሱ ዓለም '
ሰው በቃ አይጨመጭምም ?!
ማጉረምረም ...
ፈልጐ ነገር እንደላስቲክ መለጠጥ
ጨምጫሚው በኃይል ጭብጨባውን ቢያቀልጥ
ወዲያው ግልምጫ ሲበዛ
ቢገባቸው ነገሩ እንዳልሆነ የዋዛ
ወሬ ቸርቻሪው ፍትልክ
እነ ቤቲም ቀስ ብለው ሹልክ
የኬኔዲ መርካቶ ቸርቻሪ
ጥናት ትቶ የሚቸረችረው
ወግ እና ጉራ ነው
ለነ ቤቲ ግን ""ሙድ "" አለው ::

መስከረም 22, 2001 ዓመተ ምህረት

No comments:

Post a Comment

Blog Archive