Wednesday, December 5, 2012

የአባ ጳውሎስ ሃውልት መታሰቢያነት


ጓደኛየ ጋር ስለ ሀውልት ጉዳይ ተነሳና -የአባ ጳውሎስን ሃውልት አነሳሁብት። "አሱ አንኳን ትክክለኛ ቦታ ነው የተተከለው። ቦሌ የሙሰኞች አና የሌባ መንደር ነው። "የቦሌ ስብዕና ነበራቸው ማለቱ ነው። የሲሳይ ንጉሱ "ረቂቅ አሻራ " ትዝ አለኝ !

ምን ለማለት ነው ? ከረባት ለሚለብሱ ሌባዎች አክብሮት የሚቸር ትውልድ አና (ምሁራንም ጭምር ) ተፈጥሮአል ለማለት ነው። አንዲህ ያለውን ጉዳይ አየረሱ ለውጥ መጠበቅ ---ሰማይን ማረስ ይሻላል። ሌቦችን የሚያከብር ስብዕና ከአስመሳይነትም የከፋ ችግር የተጠናወተው ነው። የመስረቅ አዝማሚያ ነው። ሌባ አንዴት አንድርጎ ነው ታዲያ ሃገሩን የሚለውጠው ? አንደዚህ አይነቶቹ ሰዎች ጭራሽ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑበት ማህበረሰብ የሚያፈራውስ ትውልድ ምን አይነት ነው

ለለውጥ የሚያስፈልገው ስብዕና የአቡነ ጴጥሮስ ( ስለ ሃይማኖታዊ እምነታቸው አይደለም ያወራሁት - ማውራት ካለብኝ ግን አሁንም ይሄው ከላይ ያልኩት ጓደኛየ የአቡነ ጴጥሮስ ጽናት ይለያል --- የመጽሃፍ ቅዱሱ ጴጥሮስ አኮ ክርስቶስን ክዶታል አለኝ። ) አይነት ስብዕና ነው። ለቆሙበት ላመኑበት ነገር ዝንፍ ሳይሉ ማለፍ። ህይወት ማለት ይሄ ነው። አንደሳቸው ማድረግ ቢቀር ደሞ ቢያንስ ከረባት ለብሰው ስርቆት ለሚያጧጡፉ ሌቦች ባይጨበጨብላቸው ምን አለበት ? የሚያጨበጭበው አኮ ከሰረቀው እኩል የሞተ ስብዕና ተሸክሞአል ማለት ነው። 


No comments:

Post a Comment

Blog Archive