በስደት ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ጥሩ ትምርህት ነው።
Thursday, December 27, 2012
Thursday, December 13, 2012
አራተኛው ፓትሪያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው።
ደጀ ሰላም ዌብሳይት ላይ አራተኛውን ፓትርያርክ በሚመለከት ለሚሰጠው የህዝብ አስተያየት (ፓል) የሰጠሁት መልስ ነው።
***
ትላንትና በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አዲሱ አበበ ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ ከሚባሉ ኢትዮጵያዊ ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጎ ነበር። ኮማንደሩ ስለቀደሙት ሊቃነ ጳጳሳቶች በፈተና መጽናት ያስታወሱን ከዚህ በፊት ቤተ-ክርስቲያኗ ስለነበራት ጥንካሬ አንደኛው ምንጭ አንደነበረ ጠቋሚ ነው። ከአቡነ ሚካኤል አና አቡነ ጴጥሮስ ተጋድሎ የማይተናነስ ጽናት ታይቶባቸዋል። ያንን ጥንካሬዋን ለመስበር ስለተፈለገ ነው ቤተክርስቲያኗ የፖለቲካ ዱላ ያረፈባት። አራተኛውም ፓትርያርክ አንደቀደሙት መሆን ሳይችሉ ቀርተው ሃገራቸውም ቤተክርስቲያናቸውንም ትተው ተሰደዋል። ነገር ግን ከዚያ የባሰአጂግ የከፋውን ጥፋት ያጠፋ ወገን ነበረ (ወይንም አለ)። ጊዜ የሰጣቸውን የፓለቲካ ጉልበት አና ሃይል ተጠቅሞ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ህግ በተጣሰበት ሁኔታ የፕትርክናውን ቦታ አንዲይዙ የተደረጉት ሰው የክርስቲያናዊነት ስነ-ምግባር በውስጣቸው ቢያይል ኖሮ ፣ለቤተክርስቲያኒቱ ያላቸው ወገንተኝነት ቢያይል ኖሮ የቤተክርስቲያኒቷ መንፈሳዊ ህግ አደተጣሰ አያወቁ ፕትርክናውን መንበር ተቀብለው ባልያዙ ነበር። ቀብተው የፕትርክና ስልጣን የሰጧቸው ጳጳሳትም ወይአንደሃይማኖት መሪ የሚጠበቅባቸውን የተጋድሎ ስራ አልሰሩም። ወይ ደሞ ነገሩን ደግፈውት ነበር ማለት ነው።
ስለዚህ ማነጻጻር ካስፈለገ በመጽናት ደከም ማለት አና ክህደት በእኩልነት ሊዳኙ አይገባም። ቤተክርቲያኗ በፓለቲካ ጣልቃ አንደተገባባት በጊዜው በፖለቲካ አንጻር ጣልቃ የገቡት ሰው(የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ) በህይወት ስላሉ በማያሻማ ሁኔታ የእምነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። "ይቅርታም" የጠየቁበት ጉዳይ ነው። የአሁኑም የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት -ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ -ጉዳዮን በህሊናቸው ዳኝተው ባለፈው ሰሞን ደብዳቤ አንዲፅፉ ያነሳሳቸው ምክንያት ይሄው ይመስለኛል። ያንን በማድረጋቸው ደሞ የደረሳባቸውን ነገር መገመት አንችላለን። በዚያም ምክንያት ይመስለኛል የጻፍትን ደብዳቤ "ስቤዋለሁ" (አንደመሰረዝ አና ውድቅ አንደማድረግ ነው) አሉ። "ያገር ክህደት ፈጽመዋል" አንደሚባሉት አስረኞች ፕሬዝዳንቱን "ይቅርታ" አስጠይቀዋቸው ነገሩን በጫና እና በማስፈራራት ያኔ አማጺያኑ ሃገሪቱን ሲቆጣጠሩ ወደነበረው ሁኔታ አየወሰዱት ይመስላል።
ደበስበስ አድርገን ጉዳዮን በፓለቲካ መነጸር ያየነው አንደሆነ ---በእምነት ጣልቃ ገብነት መሆኑ ነው። በቲዮሪ ደረጃ ህገ-መንግስታዊ መሰረት ተሰጥቶታል ከሚባለው የሃይማኖት ነጻነት ጋር የሚያያዝ ይሆናል። ፈረጥ አድርገን እንናገረው ከተባለ ደሞ በተጠና ሁኔታ ቤተክርስቲያኒቱ አንደጠላት ተፈርጃ ስለነበር እና መዳከም አንዳለባት ይታመን ስለነበረ ለዚሁ የማዳከም ስራ ይተባበራሉ ተብሎ የታሰቡ ሰው ወደ ስልጣን መተው የደረሰው ነገር ሁሉ ደረሰ። እግዚያብሔር ጊዜ አለው አንደሚባለው ጊዜውን ጠብቆ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት አሳየን። የተጣሰውን የቤተ-ክርስቲያን ህግ ማስከበር የሚቻልበት አጋጣሚ ተፈጥሮአል። ጉዳዮን አንደ ፕሬዝዳንት ግርማ በአቅም ማነስ ማስፈጸም ባይቻል አንኳን በሚያሳምን ሁኔታ የቤተክርሲያኒቷን ህግ ተከትሎ ፍርድ መስጠት አና ሃሳብ መሰንዘር ይገባ ነበር። በጳጳሳት መካከል የሚደረገው ውይይት ይሄንን እውነታ በመገንዘብ ለእውነታው ተገዢ በመሆን፣ ለቤተክርስቲያኒቱ ቀኖኗ አና የእምነት ነጻነት በመቆርቆር መንፈስ ቢካሄድ ኖሮ ስምምነት ላይ መድረስ በጭንቀት የሚያስምጥ ጉዳይ ባልሆነ ነበር።የህዝብ አስተያየት መሰብሰብም ባላስፈለገ ነበር። ምክንያቱም ፓትርያርኩ መንበራቸውን አንዲለቁ ስለተደረገበት ሁኔታ አና "አምስተኛ " ተብለው የተነሱት ሰው አንዴት ወደ መንበሩ አንደመጡ ፣ በቤተክርስቲያን ሰዎች በኩልም( ጳጳሳት) በፍርሃት ወይንም ያለፍርሃት ጣልቃገብነቱን አንደችግር ሳይቆጥሩ የድርጊቱ ተባባሪ የሆኑበትን ጉዳይ ለህዝብ ይፋ ካልተደረገ - የሚሰጠው ሃሳብ የተዛባ አንደሚሆን አያጠያይቅም። ፓትሪያርኩ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለባቸው! ከቤተክርስቲያኒቱ ህግ አንትጻር ፣ከተደረገውም ፓለቲካዊ ስህተት ፣ የእምነት ነጻነትን ከማስከበርም አንጻር ትክክለኛው ነገር ይሄ ነው። አራተኛው ፓትርያርክ በጉልበት የተነጠቁት መንበሩ ከተመለሰላቸው በኋላ ራሳቸው በእድሜም በጤናም ምክንያት የቤተክርስቲያኒቱን ጥቅም ግምት ውስጥ በማስገባት የሚወስዱት እርምጃ ይኖራል። የተደቀኑትንም አስቸጋሪ ሁኔታዎች አያነሱ መወያያት ይቻላል።
በሌላ በኩል ግን ፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤያቸውን ከሰረዙ በኋላ ይዘውት የተነሱትን - አራተኛው ፓትርያርክ ወደ ሃገራቸው መመለስ ይችላሉ ነገር ግን በምርጫ አይወዳደሩም ወይንም መንበር አይዙም አይነት ኣስተሳሰብ -በቤተ-ክርስቲያን 'አባቶች' (ጳጳሳት) በኩል አንዲንጸባረቅ ማድረግ 'አልሸሹም ዘወር አሉ' አንደሚባለው ይሆናል። አሁንም ቤተክርስቲያኗ በጉልበት አንደተያዘች ነው የሚያመላክተው። ለስሙ ውይይት አየተባለ ይደረጋል አንጂ በጉዳዮ ላይ የፖለቲካ ውሳኔ አንደተወሰነም የሚያመላክት ነው። ከላይ አንደጠቀስኩት ጳጳሳቱም ተባባሪ ሆነው ለሌላ ሰው መንበር ሰጥተዋል። ምናልባት(ምናልባት!) የነሱ ሁኔታ ጠንካራ ቢሆን ኖሮ ያኔ ፓትርያርኩ እስክመሰደድ ላይደርሱ ይችል ይሆናል። ያኔ ስህተት ተሰራ። አለቀ ደቀቀ። የደረሰውም ነገር ደረሰ። አሁን ግን ተመልሶ በዛው በስህተቱ መንገድ መቀጠል በጣም አሳፋሪ ነው። በክህደቱም አንደመቀጠል ነው። የቤተክርስቲያኒቱንም ጥቅም አያስከብርም። ጉድዮ የጳጳሳት አና የሲኖዶሱ ብቻ አንዳይሆን የሰንበት ተማሪዎችም ምዕመኑም የሲኖዶሱን አባላት አጋጣሚ ፈጥሮ ይሄን ጉዳይ በአጽኖት አንዲይዙት ማድረግ ይገባል። ችግሩን አንደ ሃይማኖተኛ ሳይሆን አደዜጋ ያየነው አንደሆነም የእምነት ነጻነት አለመኖር ከነጻነት አለመኖር አና ህገ መንግስታዊ ስርእት አለመኖር ጋር የተያያዘ ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንደሚያደርጉት ትግል መደገፍ አለበት። የአንድን ጠባብ ጉልበተኛ የፖለቲካ ቡድን ቅጥ ያጣ የበላይነት ለማስከበር ሲባል የዜጎች መብት አና ነጻነት በየመስኩ መታፈን አና ከጥቅም ውጭ መሆን የለባቸውም። አራተኛው ፓትርያርክ በጉልበት የተነጠቁትን መንበር እንዲያገኙ መደረግ አለበት። የፖሉ ፋይዳ አልታየኝም።
Tuesday, December 11, 2012
አደንዛዢ ማህበራዊ አስተሳሰቦች በነገሱበት የለውጥ ሃሳብ መዝራት ትርጉም አይኖረውም
ኢትዮጵያ
ውስጥ ለለውጥ ያለው ተነሳሽነት ለውጥ በሚያስፈልግበት ደረጃ የጠለቀ አይደለም የሚሉ አስተያየቶችን አልፎ አልፎ አሰማለሁ።ሊያስማማ ይችላል። አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከኑሮው ጀምሮ እስከ አምነቱ ድረስ የተዘረፈበት ሁኔታ
አለ። ስለዝርፊያው ትርጉም ያለው ተቃውሞ ( በተለይ ከምርጫ 97 ወደዚህ) እንዳላሰማ ይታወቃል። የዜግነት መብቱ አና የሃገር ባለቤትነቱ (ባላገርነቱ) ተረስቶ የኑሮ እና የደህንነት ዋስትናው ስልጣን ላይ ያለውን ወገን በመደገፍ አና ስልጣን ላይ
ባለው ወገን በጎ አድራጎት ላይ የተመሰረተ አንዲመስል ሁሉ ተደርጎአል። አሱም ምንም አልተባለም። ጭራሽ የሚጨበጨብለት የሚደነቅ ሁሉ ሃሳብ አየመሰለ ነው። ሃገርን የሚለውጠው ባለራዕይ ትውልድና ሕዝብ ሆኖ ሳለ ግለሰብ (ያውም የሃገር ፍቅር ያለነበረው) አንደ ራዕይ ፣አንደ ሃገር አና ህዝብ እየተመለከ ነው። ጉዳዮ ከደነዘዘ ማህበራዊ አስተሳሰብ የሚመጣም ነው።
የድንዝዝነቱ መጠን የሚለካባቸው ሌሎች ብዙ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። አሁን ባለው አኳኋን ምናልባት ኢትዮጵያ የማን ናት ብሎ መጠይቅ የአብዮት ጥያቄ ሊመስል ሁሉ ይችላል። አንዳልሞተ ሰው መለስ ዜናዊ በዚህ ገብቶ መለስ በዚህ ወጥቶ አየተባለ የሞኝ ተረት ሲተረትለት የሚዋለው ነገር ድንዝዝነቱን ከመለካት ባሻገር ስለሚተረክለትም ትውልድ ስለተራኪውም ባህሪ አና ዓላማም የሚለው ነገር ይኖራል። የበሬ ካራጁ አይነት ግንኙነት የነገሰ ይመስላል። እንደበሬ ሳር አያሳዮ ወደ ገደል ሲወስዱት ከማንም በላይ ችግሩ ያለው ካለተፈጥሮው የበሬ ባህሪ የተላበሰው ክፍል ላይ ነው---ከበሬም አኮ የሚዋጋም አለ። ግራ አጋብቶአል የዚህ ትውልድ ነገር።
የድንዝዝነቱ መጠን የሚለካባቸው ሌሎች ብዙ ጉዳዮችን ማንሳት ይቻላል። አሁን ባለው አኳኋን ምናልባት ኢትዮጵያ የማን ናት ብሎ መጠይቅ የአብዮት ጥያቄ ሊመስል ሁሉ ይችላል። አንዳልሞተ ሰው መለስ ዜናዊ በዚህ ገብቶ መለስ በዚህ ወጥቶ አየተባለ የሞኝ ተረት ሲተረትለት የሚዋለው ነገር ድንዝዝነቱን ከመለካት ባሻገር ስለሚተረክለትም ትውልድ ስለተራኪውም ባህሪ አና ዓላማም የሚለው ነገር ይኖራል። የበሬ ካራጁ አይነት ግንኙነት የነገሰ ይመስላል። እንደበሬ ሳር አያሳዮ ወደ ገደል ሲወስዱት ከማንም በላይ ችግሩ ያለው ካለተፈጥሮው የበሬ ባህሪ የተላበሰው ክፍል ላይ ነው---ከበሬም አኮ የሚዋጋም አለ። ግራ አጋብቶአል የዚህ ትውልድ ነገር።
አንዲህ
ያለውን በጉልበት አና በሌሎች ዘዴዎች የተፈጠረ የደነዘዘ አተሳሰብ የበለጠ ያጠቃው አረጋውያንን አና አቅመ ደካሞችን አይደለም።
አዎ የችግሩን አሳሳቢነት ይበልጥ የሚያጎላው አንዲህ ያለውን ሃሳብ አዝሎ አየኖረ ያለው ደሞ በንድፈ ሃሳብ ደረጃ የለውጥ ሃይል ነው የሚባለው የህብረተስብ
ክፍል ነው -ወጣቱ። የገባቸው ጥቂቶችን ፣የሚችሉትን አየሞከሩ ያሉትን አብሬ መውቀሴ አንዳልሆነ መጠቆም እፈልጋለሁ።የሚችሉትን ያህል
አየሞከሩ ያሉ የፖላቲካ መሪዎችንም -ሃገር ቤት ያሉትን ማለቴ ነው- አይመለከትም። ስለደነዘዘው ነው የማወራው። አዉቆ የተኛም ካለ -አውቆ ስለተኛውም ነው የማወራው።
አንቆቅልሹን ለመፍታት ሁነኛ ጥረት አየተደረገ አይመስለኝም። የሚለፉት አየለፉ ቢያንስ ለለውጥ ትርጉም ያለው አንኳን ዝግጁነት የማይስተዋልበት ምክንያት -ምናልባት ዓለት ላይ
አንደተዘራው አይነት ነገር ቢሆን ነው። በማህበራዊ አስተሳሰብ ደረጃ ብዙ የተመሰቃቅለ ጉዳይ አለ። ለለውጥ የሚሆን ማህበራዊ ስብዕና
ሳይኖር ለውጥ መጠበቅ ብልህነት አይደለም። ለውጥ አልመጣም ብሎ ማማረም አንዲሁ ትክክል አይደለም። ደጋግሜ አንደምለው በተነዛባቸው ፕሮፓጋንዳ ምክንያት አንደዋዛ አና አንዳልባሌ
ነገር የጣልናቸው ኢትዮጵያዊ ማህበራዊ አስተሳሰቦች አሉ። አነሱን አናንሳቸው አና እስቲ በነዛ በኩል ይሞከር።
ራሱን አየሳተ ያለው ትውልድ- የደነዘዘው ትውልድ መጀምሪያ ራሱን ይግዛ። አደንዛዥ ማህበራዊ አስተሳሰቦች በነገሱበት የለውጥ ሃሳብ መዝራት ትርጉም የለውም። ፍሬም አይኖረውም። አደንዛዦቹ ማህበራዊ አስተሳሰቦች ወይንም ወደዚያ የሚወስዱ
አስተሳሰቦች ይለዮ። ይዘመትባቸው። የመነጋገሪያ ርዕስም ይሁኑ።
Wednesday, December 5, 2012
የአባ ጳውሎስ ሃውልት መታሰቢያነት
ጓደኛየ ጋር ስለ ሀውልት ጉዳይ ተነሳና -የአባ ጳውሎስን
ሃውልት አነሳሁብት። "አሱ አንኳን ትክክለኛ
ቦታ ነው የተተከለው። ቦሌ የሙሰኞች
አና የሌባ መንደር
ነው። "የቦሌ ስብዕና ነበራቸው ማለቱ
ነው። የሲሳይ ንጉሱ "ረቂቅ አሻራ "
ትዝ አለኝ !
ምን ለማለት ነው ?
ከረባት ለሚለብሱ ሌባዎች
አክብሮት የሚቸር ትውልድ አና (ምሁራንም
ጭምር ) ተፈጥሮአል ለማለት ነው። አንዲህ
ያለውን ጉዳይ አየረሱ ለውጥ መጠበቅ
---ሰማይን ማረስ ይሻላል። ሌቦችን የሚያከብር
ስብዕና ከአስመሳይነትም የከፋ ችግር የተጠናወተው
ነው። የመስረቅ አዝማሚያ ነው። ሌባ
አንዴት አንድርጎ ነው ታዲያ ሃገሩን የሚለውጠው ? አንደዚህ አይነቶቹ
ሰዎች ጭራሽ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑበት
ማህበረሰብ የሚያፈራውስ ትውልድ ምን አይነት
ነው ?
ለለውጥ የሚያስፈልገው ስብዕና የአቡነ ጴጥሮስ ( ስለ ሃይማኖታዊ እምነታቸው አይደለም ያወራሁት - ማውራት ካለብኝ ግን አሁንም ይሄው ከላይ ያልኩት ጓደኛየ የአቡነ ጴጥሮስ ጽናት ይለያል --- የመጽሃፍ ቅዱሱ ጴጥሮስ አኮ ክርስቶስን ክዶታል አለኝ። ) አይነት ስብዕና ነው። ለቆሙበት ላመኑበት ነገር ዝንፍ ሳይሉ ማለፍ። ህይወት ማለት ይሄ ነው። አንደሳቸው ማድረግ ቢቀር ደሞ ቢያንስ ከረባት ለብሰው ስርቆት ለሚያጧጡፉ ሌቦች ባይጨበጨብላቸው ምን አለበት ? የሚያጨበጭበው አኮ ከሰረቀው እኩል የሞተ ስብዕና ተሸክሞአል ማለት ነው።
Subscribe to:
Posts (Atom)
Blog Archive
- April (18)
- May (8)
- June (2)
- July (1)
- October (2)
- December (7)
- March (1)
- July (1)
- August (1)
- January (5)
- February (3)
- March (2)
- June (2)
- April (3)
- May (3)
- August (2)
- September (1)
- October (3)
- November (4)
- December (4)
- January (4)
- February (3)
- March (8)
- April (2)
- May (2)
- June (1)
- December (2)
- January (2)
- February (1)
- May (2)
- July (4)
- September (1)
- October (2)
- November (1)
- September (1)
- December (1)
- December (1)