Monday, October 1, 2012

ሃገራችንን አልተሰረቅንም ወይንም አየተሰረቅን አይደለም ማለት ይቻላልን?

ከሃገር ቤት የሚጽፉ ልጆች የጽሁፋቸው ጭብጥ ብቻ ሳይሆን ለዛውም የአንባቢን ይመስጣል። አኔ ደሞ በለዛ ነው የተለከፍኩት! ከሚጽፉት ነገር ለዛ ብዛት ፖለቲካ ሁሉ አይመስልም - አንደ ኮሜዲም አንደ ማህበራዊ ግንኙነትም ያደርገዋል። ለነገሩ - በ"ሶሻል ሜዲያ" አንዲያ ቢጻፍ የአባት ነው። ሶሻል ሚዲያ ግን የኢኮኖሚ የፓለቲካ የባህል አና የሃይማኖትም ጭምር ሜዲያ አይደለም ማለት ግን አይደለም። አንዲያውም የነሱ ባይበልጥ ነው።

የምጽፋቸው ተደጋጋሚ ፓከቲካ ነክ ጉዳዮች የፌስ ቡክ ጓደኞቸን እንዳያሰለች በማሰብ "ሶሻል ሚዲያ" አንደ ግብሩም ባይሆን አንደስሙ አንዲሆን የማደርግበት ጊዜ አለ። አንደዚያ ሳደርግ ታዲያ ፓለቲካውን ተወት አድርጌ ነው። አንደ ሃገር ቤቶቹ ልጆች ፓለቲካን አያዋዙ ለዛ አላብሶ መጻፍ መጻፍ ብችል ሁሌ ፓለቲካ ብጽፍ ደስ ባለኝ። ፓለቲካ የማያመልጡት ነገር ስለሆነ ብቻ ሳይሆን መጻፍም ስለሚገባን። ያለበለዚያ ሊነግስ የሚችለውን የድንቁርና ልክ የአቶ መለስ ለቅሶ አሳይቶናል። አዚህ ላይ ድንቁርናን የለካሁት በለቀስተኞቹ ሳይሆን በዛ ደረጃ አንዲለቀስ አና ለቅሶ የፓለቲካ ድጋፍ ማሰባሰቢያ አንዲሆን ተደርጎ --የነገር አና የከነገ ወዲያ ማህበራዊ አና ባህላዊ (ፓለቲካዊም ጭምር) አንድምታው ግምት ውስጥ ሳይገባ ---የለቅሶውን ሂደት ኢንጂነት ባደረጉት የፖለቲካ ሰዎች ነው። ስለዚህ የምጽህፋቸው የፖለቲካ ጽሁፎች በተቻለ መጠን ሃገር ቤት ያሉ የፌስ ቡክ ወዳጆች በሚጽፉበት መልክ ለማደረግ አሞክራለሁ።

ለቅሶ የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ አድርጎኣል አያሉ በሚዲያ አንዲስተጋባ ያደረጉ ግለሰቦች አና ቡድኖች በለቅሶው ሰበብ አንደተከፋፈሉ ያደባባይ ሚስጥር ሆኖል። ህወሃት በራሱ አንድም ሁለትም አንደሆነ ይነገራል። ኦህዴድ አፍንጫውን ነፍቶአል ይባላል። ደህዴን አና ብአዴን ለአንደኛው የህወሃት ስንጣቂ ምናልባትም "መለስ የተዋጋው ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ አኩልነት ነው" ሲሉ ለተደመጡት ወገኖች በገባርነት አና በጋሻ አጃግሬነት የመሰለፍ ፍላጎት(አቅምም ይኖራቸው ይሆናል) አንዳላቸው የሚጠቁሙ ጭምጭምታዎች አሉ ። አነኚህ ጭምጭምታዎች "ክሬዲብል" ይሁኑ አይሁኑ ጊዜ ብቻ ነው የሚያሳየን። አንደ አቶ መለስ ሞት!

ሌላኛው የህወሃት ስንጣቂ የነስብሃት የሚባለው ቡድን ደሞ አፍንጫውን ከነፋው ኦህዴድ ጋር ገጥሞኣል የሚባልም ወሬ አለ። አየሩሳሌም አርአያ ባስነበበንም በሌሎችም ጽሁፎች ማመሳከሪያነት አቶ ስብሃት ይመሩታል የሚባለውን ስንጣቂ ቀድሞ መገለል ደርሶባቸው የነበሩ የህውሀት አባላትን (የስየ ቡድን ይባሉ የነበሩ ሁሉ አንደተሰባሰቡበት ነው የሚነገረው)በባትሪ አየፈለገ አያሰባሰባቸው አንደሆነ አየሰማን ነው። በነገራችን ላይ የስየ የሚባሉ ቡድንኖችን ካናገሩ ስየን ራሱን አንደማያናግሩት ምን ማረጋገጫ ይኖራል?! ስየም ቢሆን ህውሀትነቱን አንቆ ገሎ አይመስለኝም በመድረክ ካርድ የሚጫወተው። ምናልባትም ህወሃትነቱን በውስጡ አየተንከባከበ -"አየኮተኮተውም" -አንዱ ወዳጄ አንዳለው- ይሆናል። የኦህዴድ አና አቶ ስብሃት የሚመሩት የህወሃት ስንጣቂ አንደሚባለው ገጥመው ከሆነ -ከጎሰኝነት የተለየ አጀንዳ ሊኖራቸው ይችላል ብየ የምገምትበት አገባብ የለም። የአቶ ስብሃት ቡድን ወታደራዊ የበላይነት አንዳለው( አሁን መንግስት ነኝ ከሚለውም ቡድን በተሻለ) አንድ አና ሁለት የለውም። ኦህዴድ ያልገባው ነገር ሃያ አንድ አመት አባላቶቹን አና ሌሎች ንጹሃን ዜጎችን ያስቀተቀጠበት የጎሳ ፓለቲካ አሁንም የሚያመጣለት ነገር አንደሌለ ነው። ያለወታደራዊ ሃይልስ (አሁን ባለው ሁኔታ) ኦህዴድ ምን የሚፈጥረው ነገር አለ? ጉዳዮ አንደ አበበ ቢቂላ ለብቻ በባዶ አግር ተሩጦ የሚያሸንፉት አይደለም። ትጥቁን ያሳመረ አና ወታደራዊ የበላይነት ያለው ቡድን ነው የሚያሸንፈው። ስለዚህ አንደሚባለው የነስብሃት ቡድን አንደ ስየ ቡድኖች ሁሉ የኦህዴድን ሰዎችን ሎቢ አያደረገ ልባቸውን ከፍቶት ከሆነ ህወሃቶቹ "ምጥንቃቅ" አንድሚሉት ያለ ነገር ያስፈልጋል። በእርግጥ ኦህዴድ አሰላለፉን ማሳመር ብቻ ሳይሆን የጎሳ ፓለቲካን ፋይዳ ቢስነትም በውል በመገንዘብ ኢትዮጵያዊ ከሆነው ሃይል ትብብር መፍጠር ይኖርበት ይመስለኛል። ኢትዮጵያዊ የሆነ ስል - ድንገት አባል ከሆነበት ድርጂትም የህወሃትን የፓለቲካ ስሌት አና አካሄድ በመጨረሻውም ሰዐት ቢሆን ገብቶት ህወሃት ለማስቆም ከቆረጡት ይሁን በተቃዋሚ ጎራ ከተሰለፉ ጋር መስራትም ይቻላል።

አሁንም በነገራችን ላይ ይላል ኣቤ ቶኪቻው ሲጽፍ-በነገራችን ላይ አቶ ስየ በአይተ ኣማረ ኣረጋዊ ሪፓርተር ጋዜጣ ላይ ያስነበበንን ጽሁፍ አንዴት አያችሁት? አንደ አኔ አንደኔ አንዳንድ ግልጽ የሆኑ ሊጠየቁ የማይችሉ ነገሮችን ቢጽፍም - ግልጽ ያልሆኑ አና አርስ በርሳቸው የሚጋጩም ነገሮች ተናግሮአል። ሙሉ በሙሉ ስህተት የሆኑ ነገሮችንም ጽፎአል። የአነጋገር ቶኑም ወደ መከላከያ ሚኒስተርነት ዘመኑ ጠጋ የሚል ይመስላል። አየተከላከለ ያለው ነገር አንዳለ አያሻማም። ለመድረክ ነው ወይንስ ለአንደኛው ስንጣዊ የሚከላከለው የሚለው ብቻ ነው የሚያሻማው። ከብዙ በጥቂቱ አንዷን ነገር ብቻ መዘዝ ላድርግ። በሰው ሞት (በኣቶ መለስ መሆኑ ነው አንግዲህ) ሰዎች ተደሰቱ ያሉትን ነገር ይነቅፉና ( ለሁሉም ባይሆን የአቶ መለስን ሞት ከፓለቲካ አንጻር አና ከፍትህ አንጻር የሚያዮት ወገኖች አንዳሉ የሚገባውን ያህል ትኩረት አልሰጡትም -ከሰብ አዊነት አንጻር አይታይም) መለስ ብለው ደሞ በአቶ መለስ ሞት የተፈጠረ አና ሊበላሽ የማይገባው የፖለቲካ አድል አንዳለ ይናገራሉ። ከአንድ ወዳጄ ጋር ስወያይ ---አንድነት ለዲሞክራሲ አና ለፍትህ የአመራር አባሎቹ በውጪ ሃገር አንዳኖሩ የሚከለክል ድንጋጌ ( የአንድነት ህገመንግስታዊ ልበለው) አለ ብሎኛል። አርግጥ ነው አይተ ስየን ለትምህት ላካቸው የተባለው አንድነት ነው። አቶ ስየም ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ ወደ ስድስት ወር ገደማ ሊሆናቸው ነው ይባላል። ይሄ ከሆነ አሜሪካ ቁጭ ብለው የማንን ጎፈሬ የሚያበጥሩ ይመስላችኋል?? አንድነትስ ቢሆን በቃህ ጨርሰሃል አስከዚህ ቀን ደረስ በስራ ገበታህ መገኘት አለብህ ብሎ መናገር ኣልነበረበትም?? ነው ብሎሏል?? ስገምት አቶ ስየ አሜሪካ ሆነው የፓለቲካ ስንቃቸውን አየቆጣጠሩ ሊሆን ይችላል--- የሃገራችን ፓለቲካ ቡራኬውም ማብሪያና ማጥፊያውም አሜሪካ አየሆነ ይመስላል -በሚያሳዝን ሁኔታ። ሌላው በዚህ ጽሁፍ ያሳዮት ግልጽ ስህተት -"ባለፉት ሃያ አንድ አመታት የተገኘ ሰላም አለ። የተፈራ ንብረት አለ።" ማለታቸው ነው አንዴት? ለማን የሚሉ ጥያቂዎችን በሚመልስ መልኩ አይደለም ይሄን ያሉት።

ይህ በአንዲህ አንዳለ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝንም ጉዳይ ቢያንስ በአንድ ገጻቸው ያደረ "ባቄላ" "የሆኑበት ሁኔታ ያለ" ይመስለኛል። በድንገት በራሳቸው መንገድ አያሳበሩ አሁን ያሉበት ቦታ ደረሱ ብሎ በአርግጠኝነት ለመናገር የሚቻል አይመስለኝም። የራሱ የሆነ የፖለቲካ ኢንጂነሪግ ነገር ይኖረዋል። በርግጥ ኢንጂነሩ ህወሃት ነበር ወይንስ ሌላ የውጭ ሃይል - ይሄም በሂደት ጊዜ የሚነግረን ነገር ነው የሚሆነው። በነገራችን ላይ "ከዘመነ ጺላ ወደ ዘመነ ጨምበላላ" የምትለውን ነጠላ ትረባ ህወሃቶች ወደዋት (ክፍለውበትም ይሆናል) ሰርኩሌሽኗን አልተቃወሙም። ወደ ኃይለማርያም ጉዳይ ስመለስ ሰሞኑን ፌስ ብክ ላይ ካየሁት አንኳን ከቢል ጌት ጋር ጥርስ በጥርስ ሆነው የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ አይቻለሁ። ከቢል ጌትስ ጋር ሻይ ቡና ብቻ ብለው ይለያያሉ ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ ወይንም ካለች አሱ/ሷ የዋህ ብቻ አይደለም/ችም። ቢል ጌትስም አንደሚያስመስለው ኮዙ አንደኛ ባሉ ሃገሮች ያሉ ህዝቦችን ኑሮ መቀየር ነው ብሎ የሚያስብ ሰው ካለ አሁንም ጉዳዮ ከየዋህነት ጋር (ቢያንስ ቢያንስ ማለቴ ነው) የሚያያዝ ነገር ነው የሚሆነው። ቢል ጌትስን አና የአሜሪካን መንግስት ተምታተውብኝ አይደለም። የሜዲያ አና አንደቢልጌትስ ያሉ ተጽዕኖር ፈጣሪ ሃይሎች የሚከተሉት አቅጣጫ ሃገራቸው ስለምትከተለው ፓሊሲ የሚለው ነገር ስላለ ነው። በገዛ ሃገራችን ከስየ ከኃይለማርያም ከእገሌ ከእገሌ አያሉ አያማረጡ አያሉ አንደሆነ ይሰማኛል። ሃገራችንን አልተሰረቅንም ለማለት "የማልችልበት ሁኔታ ነው ያለው" ።

No comments:

Post a Comment

Blog Archive