Monday, April 6, 2009

የሰፈሩ አዛውንት እና ፍንዳታ (ከሰፈር ትዝታዎች)

ወደ ማታ ሲሆን ሰፈር ሰብሰብ ብለን
ወሬ ስናወራ ግንብ ተደግፈን
አንድ ፍሬ እያለን ምንነቱን ሳናቅ ሴት ለካፊ ሆንን ::

ተሰብስበን ያዪት የሰፈሩ አዛውንት ሀሳብ ቢገባቸው
የምናውካካበት ምክንያት ባይገባቸው
ኧረ እናንተ ልጆች እባካችሁ አጥኑ
ሰዐቱም ጊዜ አይደል መሽቷል እኮ ቀኑ
ፍንዳታው ሲያማርር ያዛውንቱን ምክር
ድምጹን ከፍ አድርጎ መዘርጠጥ ሲጀምር
የመንደሩን አዛውንት ጓደኛው ይመስል
""ይኼ አራጌ ደሞ በጣም ያበዛዋል ""
ገና ከመምጣቴ ደርሶ ይለክፈኛል
"አንተ ምን አገባህ '
'ቦታው ያንተ መሰለህ ?'

መሄድ ተስኗቸው በከዘራ ብርታት እየተራመዱ
የሰፈሩ አዛውንት ልባቸው አልሞተም ...
የኮሪያን እና የኮንጎውን እልህ ሊያወጡት ወደዱ
ዘርጣጩ ሲያበዛው በጣም በስጨት ብለው
ምን የተረገመ አሁን በዚህ ብለው ለማነካካት ነው ::
እናንተ ግን ተባረኩ
እንዳይን በጠፋ እንዳትማረኩ
ብናገር አጥኑ ብላችሁ ልጆቼ ስለሆናችሁ
አስኮላውን ጨርሳችሁ ኮሌጅ በጥሳችሁ
ዲግሪውን ጭናችሁ ለራሳችሁ ለናት ላባታችሁ

እኔማ ምናለብኝ
ዕድሜ አላደኽየኝ
የተጠናቀኩኝ ቀኔ የደረሰ
ልጤ የተራሰ ቀብሬ የተማሰ
አጥኑ ማለቴ መናገሬ ለናንተው
በሉ እስኪ እግዜር ያብጀው ::

ጥቅምት 25, 2001 ዓመተ ምህረት

No comments:

Post a Comment

Blog Archive