Friday, March 29, 2013

Conquest through Music?

I have a feeling that the purpose of music is defeated and with that the nature of music itself. Claim of advancement in music has a lot to do with, I would say, commodification of music, the revenue it generates and the attraction it has got among investors as is the case with some other aspects of societal life. No doubt the music industry has got a very strong financial stand. Perhaps music has become less of pursuit to passion and art, and more of an enterprise from which lucrative financial profit could be amassed.

So, what investors in the industry do, apparently, is create musicians, invest in them and promote them. The point as to whether it is the case that the industry creates musicians or that it is musicians who create themselves as musician might be debatable for some. I tend to think that it is the former in most cases. Certainly, investors have the capacity to accomplish that due to the power of their financial standing which obviously enable them create connection to “influential” media outlets where they sell the created “talents”, among other things. They could simply select a good looking teenager and heavily invest in him or her, sell a “talented and artistic” image of the selected singer and then it is ready for profit and conquest. As was the case in history, profit, in all its forms, comes with conquest.

In addition to the financial motive, ideological value (“freedom” “opportunity” and what have you) will be embedded in the created ‘talent.’ If intended cultural conquest is not in disguised as “talent,” it could end up creating resistance rather than warm reception and appetite for emulation. In that case, resistance to their production represents both ideological and financial loss. Seemingly, the target of disguised cultural conquest is the section of population that is otherwise revolutionary and patriotic at the same time. The purpose might be loosening attachment to the things the youth values most: usually country and society.

Often times, the conquest is projected as embracing “modern music.” And with that comes propagation of thinking pattern that seem to accept the rhetoric of music as “international language.” Well, no question that the instruments and the way music is composed could be “international.”  Other than that there is not such this as “international music”

What is music outside of the message it conveys? Outside of lyrics?  Behind lyrics and messages in music we have song writers. Are song writers reflecting the values and cultures of the society from which they came? Or are they glorifying values and cultures of others? Do the things they glorify empower society? Are the things glorified desirable? It may not sound strange, or nor wrong for that matter, to observe a song writer for example in Florida –Miami glorifying sexuality. Equally, I will not be surprised if dances for such a song glorify sexuality.

The problem is when a song writer in Ethiopia (may be with subtle administrative and financial support) imitate Miami and dare to rape music tradition say from Gojjam or Gondor or Wollo or Guraghe and make it essentially Miami rather than the places where it is supposed to originate from- Ethiopian localities I mentioned above.

With corruption of the messages in music comes corruption of the dances.The Gonder Eskista is essentially being deformed. Producers are penetrating the cultural Gonder and deforming the culture and doing same in other parts of Ethiopia in the name of “modernizing music.” When an Ethiopian Music is deformed and produced in a way to emphasize “modernity” and the cultural context of other societies that have nothing to do with Ethiopian value or culture that is called conquest! And conquest through our locals which is what the British did in their colonization history.

Just observe how the originality, moderation, humility and faith reflected through traditional music is becoming a thing of the past before our eyes. It is alarming! And what is happening to Gonderigna? Oromogna? It is painful because instruments of conquest are our own people and yet they think they are “modernizing” Ethiopian music.

Yes, there is something distinctly called Ethiopian music just like there is distinctly Russian, distinctly Syrian, and distinctly Peruvian, distinctly Japanese music. Do not sell rubbish to your people in the name of “modernity”

Next time, I will write about the sociology of Ethiopian music the way I understand it. For now, let me just invite you one of my favorite Ethiopian Oldies of the mid 80’s.  “Engdayeneh” Alemayehu Eshete and KuKu Sebsibe

__________________

This article was first published on borkena website

Thursday, March 28, 2013

እውነቱ ምንድነው?!

መንግስት ከአሶሳ አካባቢ እንዲፈናቀሉ የወሰነባቸው ኢትዮጵያውያን አካባቢውን ለቀው በመጓዝ ላይ እያሉ አስከፊ የመኪና አደጋ እንደደረሰባቸው፤ በአደጋውም ምክንያት 59 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ የኢሳት ዜና አገልግሎት መጀመሪያ  በማርች 26 በሰበር ዜናው ቀጥሎ ደሞ በተመሳሳይ ቀን የምሽቱ የዜና ስርጭቱ እንደዘገበ የሚታወስ ነው። ቦርከና ድሀረ-ገጽም ኢሳትን በምንጭነት ጠቅሶ ዜናውን አካፍሎ ነበር።  ህኖም ሃገር ቤት ካሉ “ነጻ” ጋዜጦችም ሆነ ከህወሓት/ኢህአዴግ ፈርጀ ብዙ የዜና ተቋማት በጉዳዮ ላይ ተጨማሪ ዘገባ ለማግኘት ተሞክሮ ነበር። በጉዳዮ ላይ በሃገር ቤት ሜዲያ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የተዘገበ ነገር የለም። በይፋ በህወሓት/ኢህአዴግ ስር ያሉ የዜና ተቋማት በጉዳዮ ባይዘግቡ የሚገርም ነገር የለውም። ነገር ግን “በነጻ ጋዜጣ” ሂሳብ እንዲያዙ የሚፈልጉት ሌሎች የሃገር ቤት ጋዜጦች በጉዳዮ ላይ አለመዘገባቸው የሚያስነሳው ጥያቄ አለ። ከኢትዮጵያ ውጭ ያሉ ሌሎች የዜና ተቋማትም – እንደ የአሜሪካ ድምጽ የአማርኛ አገልግሎት እና የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ጣቢያዎችም እንዲሁ በጉዳዮ ላይ አልዘገቡም።

በአንድ ሃገር ውስጥ በመኪና አደጋ 59 ሰው ሲሞት ትልቅ ዜና ነው፤ በዓለም ዓቀፍ ደረጃም ጭምር! ስሞኑን በህንድ የመኪና አደጋ ደርሶ ትልልቅ የሚባሉት የዓለም ዓቀም ሜዲያዎች ዘግበውታል። በደቡብ አፍሪካም እንዲሁ የመኪና አደጋ ደርሶ ሰፊ የዜና ሽፋን አግኝቶል። በሁለቱም አደጋዎች በተናጠል የጠፋው ህይወት ኢትዮጵያ ውስጥ ከትላንት ወዲያ ደረሰ በተባለው አደጋ ከጠፋው ህይወት ያነሰ ነው።  ስለዚህ ኢትዮጵያ ውስጥ ደረሰ የተባለውን አደጋ ዓለም ዓቀፍ የሚባሉት የዜና ተቋማት (እንደ ሮይተርስ ፣አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣አሶሴትድ ፕሬስ ያሉ) ፣ሃገር ቤት ያሉ ጋዜጦች እንዲሁም በኢትዮጵያ ቋንቋ የፕሮግራም ስርጭት ያላቸውን እንደ አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ እና ጀርመን ድምጽ ራዲዮ ስለምን አልዘገቡበትም?! ለምን?!  አደጋው በአደጋነት ሂሳብ ብቻ የማይዘገብ እና ከዘር ማጽዳት ጉዳይ ጋር ስለሚነካካ ለመዘገብ አያስደፍርም የሚሉ ወገኖች አሉ። እንደሚባለው በዚህ አሳማኝ ሊባል በማይችል ምክንያት የ59 ሰው ህይወት ያለፈበትን አደጋ ሁኔታ እና የአደጋ መንስኤ ለሕዝብ አለማሳወቅ ከሜዲያ ፋይዳ እና ስነ-ምግባር አንጻር እንዴት ነው የሚታየው??

እንዲህ ያለ ጉዳይ ሲከሰት ኢፊሲያላዊ የሆነ መረጃ መገኘት የነበረበት ከፓሊስ ነበር። ያለው ተሞክሮ ግን ያንን አያመላክትም። ስሞኑን ሃገር ቤት – ያውም በመዲናዋ አዲስ አበባ -የሰው ህይወት ጠፋበት በተባለ ግጭት ላይ (የኮብልስቶኑን ያስታውሷል) ፖሊስ የማውቀው ነገር የለኝም እንዳለ ይታወሳል ፤ በሌሎች መስል ጉዳዮችም ላይ ፓሊስ መረጃ የለኝም የሚል መልስ የሚሰጥበት ተደጋጋሚ ሁኔታ አለ። 59ሰዎች ሞቱበት የተባለው አደጋ በትክክል ደርሶ ከሆነ ፤ በኢትዮጵያ ስም የሚነገድበት የህወሃት/ኢህአዴግ (“የኢትዮጵያ ዜና ድርጂት) ሰሞኑን የኢትዮጵያን ህዝብ በኢህአዴግ 9ኛ ጉባዔ እና የግድብ ወሬ እንዳፈነ አንድ እና ሁለት የለውም። ሌላ ጊዜ የጠፋ መርፌ የሚያገኙት የውጪ ሜዲያዎችም ጉዳዮ በትክክል ተከስቶ በዝምታ ማድበስበስ መርጠው ከሆነ ለአድሎአዊ አሰራራቸው ተጨማሪይ ማሳያ ይሆናል።

በሌላ አንጻር አደጋው ከናካቴው ያልተከሰተ ነገር ክሆነ ፤ ዘገባውን ለሕዝብ ያደረሰው ኢሳት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የመረጃ አሰባሰቡ ስራ በብርቱ ሁኔታ መፈተሽ ይኖርበታል። ምን አልባት ሆነ ተብሎ የኢሳትን ገጽታ ለማጉደፍ ህወሓት/ኢህአዴግ በዘዴ ያደረገውም ነገር ሊሆን ይችላል። እውነቱ ምንድነው?!
________________________________
 በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን www.borkena.com ማግኘትም ይቻላል። ድህረ-ገጹ በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና የአፍሪካ ዜናዎችንም ያካፍላል።
 

9ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ተጠናቀቀ


ማርች 28፣2013 (borkena) በባህርዳር ሲካሄድ የሰነበተው የኢህአዴግ 9ኛ ጉባዔ ተጠናቋል። የአሜሪካ ድምጽ እንደዘገበው ጉባኤው ኃይለማርያም ደሳለኝን በድርጂቱ ሊቀመንበርነት ፤አቶ ደመቀ መኮነን በድርጂቱ ምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል። ከአመራር አባልነት የተገለሉም እንዳሉም ታውቋል። ከተገለሉት አመራር አባላት በኢህዴግ ውስጥ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እንዳለው የሚነገርለት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩ አርከበ እቁባይ ፣ስዮም መስፍን፣ ጸጋየ በርሄ፣አባዲ ዘሙ እና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ  እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

በጉዔው ላይ የአቶ መለስ ዜናዊን የህይወት ጉዞ ያመላክታል የተባለ ዝክረ-ወዳሴ የቀረበ ቢሆንም በቀረበው ወዳሴ “ብዙ” የጉባዔው ተሳታፊዎች አልተደሰቱም ተብሏል። በዝክረ-ውዳሴው ካልተደሰቱት ውስጥ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ባለቤት  ወይዘሮ አዜብ መስፍን አንዷ ሲሆኑ ዝክሩ የዘለላቸው የመለስ የህይወት ጉዞዎች አሉ ባይ ናቸው። ለምሳሌ ያህል መለስ የ”አዲስ ራዕይ” ዋና አዘጋጂ የነበሩ ሲሆን አልተመለከተም በለዋል -ወይዘሮ አዜብ።

በአጠቃላይ ጉባኤው  የአመራር ድክመት ስለመኖሩ ጠቁሟል። በሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ መሰረት ደሞ ከአመራር አባልነት የተገለሉት የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩት አቶ ስዮም መስፍን ስለ ግንባሩ ውህደት አንስተዋል። ሪፓርተር የአቶ ስዮም ያለውን ሃሳብ እንደሚከተለው ጠቅሶታል፡- ‹‹ኢሕአዴግን የማዋሀድ ጥያቄ ከተነሳ 22 ዓመት አልፎታል፤ ጥናቱ መጀመር አለበት፤››

______________________________________
በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን www.borkena.com ማግኘትም ይቻላል። ድህረ-ገጹ በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና የአፍሪካ ዜናዎችንም ያካፍላል።

Sunday, March 24, 2013

የኢህአዴግ 9ኛ ጉባዔ፡”የልማት ኃይሎች ንቅናቄ”

ጉባዔው “የመለስ ዜናዊ  አስተሳሰቦቹ እና አስተምህሮዎቹ ይበልጥ የህዝብ ሃብት ሆነው እንዲስፋፉ የማድረግ አቅጣጫ የሚያስይዝ ጉባኤ እንደሚሆን ይጠበቃል” ኃይለማርያም ደሳለኝ 

March 24,2012 (Borkena) ኢህአዴግ  ለአራት ቀናት ይቆያል የተባለለትን 9ኛውን የድርጂቱን ጉባዔ “በመለስ አስተምህሮት ጠንካራ ድርጂቶች እና  የልማት ኃይሎች ንቅናቂ ለህዳሴያችን” በሚል መሪ  ቃል ትላንት  በባህርዳር ጀመረ። የኢትዮጵያ ቴሌቭዠን እንደዘገበው  9ኛው ጉባዔ 8ኛው ጉባዔ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ምን ያህል ተግባራዊ እንደሆኑ እንደሚገመግም አስታውቋል። ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ህልፈተ ህይወት ወራቶች በኋላ ውዝግብ በሚመስል ሁኔታ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣን የተሰጣቸው ኃይለማርያም ደሳለኝ እስካሁን የተደረጉት የድርጂቱ ጉባዔዎች ሁለት መሰረታዊ ነጥቦችን፡-

  • ድርጂቱ ውስጣዊ ዲሞክራሲያዊ ሁኔታውን የሚፈትሽበት እና ተግባርን ማዕከል አድርጎ በሚካሄድ ፓለቲካዊ እና ሪዮተ-ዓለማዊ  ትግል ድርጂታዊ ጥንካሬ የሚጎለብትበት እንዲሁም በዲሞክራሲያዊ መንገድ አመራሮችን መርጦ የትግሉን ቀጣይነት የሚያረጋግጥበት”
  • ከሕዝቡ የተቀበለውን አገር የመምራት እና የማስተዳደር ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን የሚገመግምበት እና ተገቢውን ትምህርት በመውሰድ ጠንካራ ጎኖቹ ይብልጥ እንዲጎለብቱ እና ደጋማ ጎኖቹ እንዲታረሙ እና ዳግም እንዳይከሰቱ ለትግል የሚዘጋጂበት የተጣመሩ ተልዕኮዎችን መፈጸም
የያዙ እንደነበሩ አስታውሰው 9ኛው ጉባኤ ሲካሄድም “የራሱ የሆኑ ታሪካዊ ገጠመኞችን በመያዝ ነው” በማለት ጠቁመዋል። ታሪካዊ የተባለው የመለስ ዜናዊ በሞት መለየት ሲሆን  ከዚሁ ጋር በተያያዘ 9ኛው ጉባዔ  አንግቦት የተነሳው  ዓላማ
“በመስዋዕቱ የተቀሰቀሰው ህዝባዊ ማዕበል ዳር እንዲደርስ እና በህይወት ዘመኑ ለሃገራችንም ሆነ ለአህጉራችን ከዚያም አልፎ ለዓለም ፍትህ ከድህነት እና ኋላቀርነት ለመላቀቅ የሚታገሉ ህዝቦች ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከቱ እና  እያበረክቱ ያሉ አስተሳሰቦቹ እና አስተምህሮዎቹ ይበልጥ የህዝብ ሃብት ሆነው እንዲስፋፉ የማድረግ አቅጣጫ የሚያስይዝ ጉባኤ እንደሚሆን ይጠበቃል” ሲሉ ገልጸውታል ።

“በአምስቱ ዓመት የልማት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለሁለት ዓመት ተኩል ዕቅድ አፈጻጸም አመርቂ ውጤት ተገኝቷል” መባሉ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ መታመማቸው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በሞተ ተለይተው ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣን እንዲረከቡ እስከተደረገበት ጊዜ  በብዙ ወራቶች በሚቆጠር እድሜ የፕሮጀት መስተጓጎል ከመኖሩ አንጻር ውጤት ተገኝቷል መባሉ አሳማኝ ባይሆንም፤ “የማስፈጸም አቅም” በጉባዔው ከዋነኛ አጀንዳዎች እንደ አንዱ መነሳቱ “ትራንስፎርሜሽን” ስለተባለው እቅድ መሳካት አጠራጣሪነት የሚሰጠው ፍንጭ አለ። ፕሮጀክት የማስፈጸም አቅም ግምገማ ክፕሮጀክት እቅድ ጋር ሊታይ የሚገባው የፕሮጀክት ቀረጻው አካል እንጂ ፕሮጀክት በማስፈጸፍ ሂደት መሃል ላይ እንደ ኮንትራት ውል ክለሳ ሊነሳ የሚገባ ጉዳይ ሊሆን አይችልም። ”የማስፈጸም አቅም በጥልቀት ይፈተሻል” መባሉ ምናልባት ከአስፈጻሚ አካላት መተካካቱ እና ከፋይናንስ አቅም አንጻር ሊታይ የሚችል ነው። የህወሓት መራሹ መንግስት የድህንነት እና የስለላ መዋቅር በአፈናው ልክ የተለጠጠ ስለሆነ ለተነደፉ የልማት ፕሮጀክቶች ሊውሉ የሚችለውን የተወሰነ የፋይናንስ አቅም ሊሻማው እንደሚችል አንድ እና ሁለት የለውም።

ሌላው ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ፓለቲካዊ ግብ ያለው የሚመስል በዋጋ ግሽበት የተመታ ኢኮኖሚ እየመሩ በ”ድንገት” የሞቱ ከመሆናቸውም በላይ ሁለት አስርት ዓመት በዘለቀው በጽንፈኛ የጎሰኝነት ስሜት ላይ የተመስረተ በሚመስል አስተዳደራቸው በወሰደው የመብት ጥሰት እና የኃይል  ርምጃ በርካታ ንጹሃን ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡ ፣ እስርና እንግልት እንደደረሰባቸው እና ለስደት እንደተዳረጉ እየታወቀ የመለስ ዜናዊ “አስተምህሮቶች…ለዓለም ፍትህ፣ከድህነት እና ከኋላቀርነት ለመላቀቅ አስተዋጾ አበረከቱ” መባሉ ምናልባት በገዢው ፓርቲ  ስር ለተኮለኮሉት ካልሆነ በስተቀር ለሌላው ኢትዮያዊ እንደ ፌዝ ከመታየት ያለፈ ዋጋ እንደማይኖራቸው መገመት አያዳግትም።  ይልቁንም አቶ መለስ ዜናዊ የብሄር ትምክህት የተጠናወታቸው የፓለቲካ ሰው እንደነበሩ ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተለያየ ጊዜ ከሰነዘሯቸው ፓለቲካዊ አስተያዮቶች በተጨማሪ በመሩት ስርዓት በተንጸባረቀው( እና አሁን ድረስ ባልተቀየረ) የስልጣን እና የሃብት ክፍፍል በቀላሉ መገመት ይቻላል። አቶ መለስ ለረዢም ጊዜ ከመሩት (እና ‘ከተዋጉለት’) የህወሓት ፓርቲ የተለየ የፖለቲካ እሳቤ እና አመለካከት ያልነበራቸው ሰው እንደመሆናቸው፤ምናልባት 9ኛው ጉባዔ “የመለስን አስተምህሮ ማስፋፋት” በሚል ጠቅላይ ሚኒስተር ዜናዊ ከጊዜ በኋላ በማህበራዊ ማለሳለስ እና በብልጣብልጥነት ሊሸፍኑት የሞከሩትን የህወሓት ራዕይ እና ዓላማ በሌሎች ከህወሃት ጋር በበታችነት በሚሰሩ ድርጂቶች ላይ የመጫኛ ስትራቴጂ ሊሆን የሚችልበትም ሁኒታ ሊኖር ይችላል።

ከዚሁ ጉባዔ ጋር በተያያዘ የኢሃዴግ መንግስት ቻይናን እና ሱዳንን (ሰሜን ሱዳን) ጨምሮ ስላሳ ያህል የውጭ ሃገር መንግስታትን እና ድርጂቶችን በእንግድነት የጋበዘ እንድሆነ ገልጾ የኤርትራ ተቃዋሚዎችም ከውጭ መንግስታት እኩል ግብዣ ተደርጎላቸው በጉባዔው በእንግድነት ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ስለመጋበዛቸው ወይንም ስላለመጋበዛቸው የተጠቆመ ነገር ባይኖርም ከህወሓት መራሹ መንግስት ተሞክሮዎች ተቃዋሚው እንዲህ አይነት ግንዣ እንደማይደረገልት መገመት አያስቸግርም።

________________________
በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን www.borkena.com ማግኘትም ይቻላል። ድህረ-ገጹ በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና የአፍሪካ ዜናዎችንም ያካፍላል።

Monday, March 18, 2013

የቆመ የመሰለው ህወሓት…

የህወሓትን መንግስት ግብር ፈጽሞ በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ጽንሰ ሃሳብ መስፈር እንደማይቻል ህወሓት በተደጋጋሚ ከወሰዳቸው ትርጉም አልባ አፈናዎች፣ ከሚከተላቸው ጥላቻ ፈጣሪ ፓሊሲዎች እና በሚያሳየው ቅጥ ያጣ የጉልበተኛነት ፍላጎቶች በግልጽ መረዳት ይቻላል። ከህወሓት መንግስት ጋር በተያያዘ ስለ መንግስት ተቋማት ፋይዳ ፣ስለዜጎች መብት ፣ በመንግስት እና በቢሮክራሲ መካክለ ሊኖር ስለሚገባው ከፓለቲካ ወገንተኝነት የጸዳ ግንኙነት( neutrality principle)፣ ስለ ህግ የበላይነት፣ ስለ ህገ መንግስታዊ አስተዳደር ማሰብ አይቻልም። የሚገርመው ነገር የህወሓትን መንግስት በነዚህ ዲሞክራሲያዊ ተቋማዊ የመንግስት መስተዳድር ገጽታዎች መስፈር አለመቻሉ ሳይሆን ፤ አምባገንነት የነገሰባቸው ፈላጭ ቆራጫዊ በሚባሉ መስተዳደሮች እንኳ መስፈር አለመቻሉ ነው። ህወሓት ከማንስም በታች ወረደ።
የመንግስት ስልጣን በያዙ ማግስት ዋና ዋና የሚባሉት የህዋሓት  አመራሮች በአንድ በኩል ከአውሮፓ ዪኒቨርሲቲዎች የተልዕኮ ትምህርት እያሯሯጡ በሌላ በኩል የፖለቲካ ስልጣን አደረጃጀት እና ከህዝብ ሊገጥማቸው የሚችለውን ፈተና እንዴት እንደሚወጡት የሚያስጠኗቸው (political tutor/mentor) የውጭ ወዳጆች እንደነበራቸው የሚጠቁሙ ሁኔታዎች አለ። በተመሳሳይ ሁኔታ ህወሓት እንደ አሰራር የ”ቡድን አመራር” የሚል ልምድ ስለነበረው ክላሽ ያነገተው የህወሓት “ተጋዳላይ” ሁሉ የመንግስትነት ስሜት ይሰማው ነበር። በህወሓት ‘ታጋዮች’ ደረጃ ይንጸባረቅ የነበረው የመንግስትነት ስሜት የርዮተ-ዓለም እይታውን እና የፖለቲካ ትምህርቱን የወሰደው ከህወሓት አመራሮች እንደመሆኑ(በካድሬዎች በኩል ቢሆንም) ፣ ህወሓት የሚሽከረከርበት  የፖለቲካ ምህዋር – “ትግሬነት” እና “ታጋይነት”-  በአንድ በኩል ታግለን አሸነፍነው የሚሉት “ጨቋኝነት እና ነፍጠኝነት” እና የጠላትነት ስሜት በሌላ በኩል ስለነበረ ከታች ያሉት “ታጋዮች” ጭምር ብዙ ቁም ነገር ሊሰጠው የማይችልን ጉዳይ በጥይት የሚዳኙበት ሁኔታም ነበር።  የህወሓት አመራሮች ትምህርታቸውን እና የተሰጣቸን የፖለቲካ ገለጻ ጨርሰውም ሀገር በስርዐት እና በተቋማት ሳይሆን በህገ-ህወሓት ልቦና መገዛት ቀጠሉበት።

ለብዙ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊ የሆነ ፣ከታሪካችን ጋር ትስስር ያለው እና ብዙ ኢትዮጵያዊ የተሰዋለት ሃሳብ በነፍጠኛነት ስለተፈረጀ  ያንን ያነገበ እንግልት እና ዘለፋ እንዲደርስበት ተደረገ። ከታች የነበሩ ‘ታጋዮች’ ጭምር በዚህ መንፈስ ነበር ሰው እንዳዋዛ በጥይት የሚገድሉት፤የሚያንገላቱት። ፕሮፌሰር አስራትን ወደ እስር የወረወራቸው የህወሓት መንግስት ነው። እታች በእስር ቤት ደረጃ ደሞ ኢትዮጵያዊነትን በጥፊ የመታ መስሎት ፕሮፌሰር አስራትን በዛ እድሜያቸው ተንጠራርቶ በጥፊ የመታውም የህወሓት ታጋይ በራሱ ቤት እሱም መንግስት ነበር።  እንደገና ከብዙ ዓመት በኋላ ብርቱካን ሚዴቅሳ ስትታሰር ፕሮፌስር መስፍን (ወደ ሰማኒያ ይጠጋ ነበር እድሚያቸው ያኔ) በሰደፍ የተመቱበት ሁኔታ አሁንም  ዓላማው ሽማግሌን መታገል ሳይሆን ፕሮፌሰር መስፍን በጊዜው ለህወሓቱ ታጋይ ያሳዮትን ኢትዮጵያዊነት መምታታቸው ነበር -በነሱ ቤት።

ትላንትናም እንዲሁ ለግራዚያኒ የሚታነጸውን መታሰቢያ ለመቃወም የወጡ ኢትዮጵያውያኖች በህወሓት መንግስት ከታሰሩ በኋላ ፕሮፌሰር መስፍን የታሰሩትን አድራሻ  ለማጣራት አንድ ፖሊስ ጣቢያ ሲጠይቁ የተሰጣቸው መልስ ”ምናባክ አውቅልሃለሁ፣ ግባና ጠይቅ” (ሰማኒያ ስድስት ዓመታቸው እንደሆነ እንዳይረሳ) ዓላማው ፕሮፌሰርን ማሳነስ ሳይሆን ፕሮፌሰሩ ሳያስነኩ ሳይሸጡ ሳይለውጡ ይዘውት የኖሩትን ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ለማሳነስ ነበር። በእነ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምም ላይ ተመሳሳይ ሊባል የሚችል አይነት ወከባ እንደደረሰ ከፍኖተ ነጻነት ዘገባ ግምት መውሰድ ይቻላል።

ከሃያ ዓመት በፊት የነበረው የህወሓት አስተሳሰብ ይሄው ነው። ከሃያ አመት በኋላም እየተንጸባረቀ ያለው አስተሳሰብ ይሄው ነው። የህወሓትን “በትግሬነት” ዙሪያ የሚያጠነጥን የሚመስል ነገር ግን በባህሪው “ጸረ-ትግሬነት”ም የሆነ ፓለቲካ በማህበራዊ ማለሳለስ እና ማድበስበስ የበላይነት ግንባታ ቢቀጥልም ከመጠነሰፊው የፕሮፓጋንዳ ሽፋን አቅም በላይ ሆነው እንዲህ እያፈተለኩ ወደ አደባባይ የሚወጡ ህወሓት ለኢትዮጵያውያን እና  ኢትዮጵያዊነትን ከውስጥም ከውጭም ለብሰው ለሚኖሩ ያለውን ንቀት እና ጥላቻ የሚያሳዮ ነገሮች ይስተዋላሉ።  የመብት ጥሰቱም ሊቆም ያልቻለው ህወሃት ከዚህ አስተሳሰብ መውጣት ባለመቻሉ ነው።ይሄንን በግልጽ ለመረዳት የነማን መብት ተደጋጋሚ የመብት ጥሰት ደረሰበት የሚለውን መጠየቅ ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል።
መንግስታዊ ተቋም፣መንግስታዊ አስተዳደር ፣ህግ እና የህግ የበላይነት የሚባል ነገር አሁንም ጭላንጭሉ የለም። ከአምባገነንም የተቃዋሚ ሃሳብ ባያከሩ እንኳ ራሳቸውን የሚያከብሩ አይጠፉም። በሽምግልና እድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ጭምር በተቋም ድረጃ እያሰሩ ማንገላታት ካስሩ በኋላ “ይቅርታ ጠይቁኝ” የሚል አምባገነን ስርዐት እና መንግስት አሁንም በወንበዴነት እና አልባሌነት ከመታየት ያለፈ አንድምታ አይፈጥርም።

ባለፈው ዓመት ይመስለኛል ትግራይ ላይ በትግራይ ያለውን የህወሓት አስተዳደር የሚቃወም ሰልፍ እንደተደረገ በዜና ማሰራጫዎች ሰምተናል። አሁንም ገፍቶ ሰልፍ አድርጋለሁ ብሉ የሚመጣ ካለ ትግራይ ላይ ያለው የህወሃት አመራር ያስራል የሚል ግምት የለኝም፡፡ አዲስ አበባ ላይ ሰልፍ ሲከለከል እና ሰልፈኛ ሲታሰር – ያውም ለግፈኛ የጣሊያን ጀኔራል የሚሰጥ ክብርን በመቃወም የተደረገን ሰልፍ- ነገሩን ሙሉ ለሙሉ ከአምባገነነት ባህሪ የመነጨ ርምጃ ለማለት ያስቸግራል። የትግራይ ህዝብ “በተሰው” 60,000 ልጆቹ ስም የሚከበረውን ያህል ሌላውም ኢትዮጵያዊ  በሚሊዮን የሚቆጠሩ የተሰው ጀግኖቹን እንዳሉት አምኖ ማክበር ባይቻል እንኳን የሚያከብሩትን ማጣጣል እና ለማሳነስ መሞከር ለማሳነስ እየሞከረ ያለውን እካል የሃልዮም የገቢርም ትንሽነት የሚጠቁም ርምጃ ሊሆን ይችላል።

እንነጋገር ከተባለ እነዛ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች በክብር በፍቅር የተሰውት ለጎጥ አይደለም። ለአማራነት አይደለም። ለኦሮሞነት አይደለም። ከጉራጌኔት አይደለም። የተሰውት ለኢትዮጵያዊነት ነው። ህወሓትም ሃያ አንድ ዓመት ሙሉ ሲቀጠቅጠው ኖሮ ኢትዮጵያዊነት ንቅንቅ ያላለበት ምክንያት ይሄው ነው። በመጨረሻ ህወሓት የመስዋዕትነት መታሰቢያ የሆኑ ታሪካዊ ቅርሶችን በልማት ስም አፈርሳለሁ የሚልበትም ምክንያት ለጸረ-ኢትዮጵያዊነቱ ተጨማሪ ማሳያ ከመሆን ያለፈ ሊሆን አይችልም።

የቆመ የመሰለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ እንዲሉ ህወሓት “ጉልበቴ እንዳለ ነው እልተነካም” የሚል አንድምታ ለመፍጠር እየወሰደ ላለው ወደ እብደት እየተቀየረ ላለ ጎጠኛ ርምጃ ለከት ቢያበጂለት ጥሩ ነው። “ባለ-ራዕዮ” የህወሓትም መሪ እንዲህ አለሁ አለሁ ሲሉ ነው በድንገት የሌሉት። እየሌሉም ህወሓት ምን ያህል ጊዜ አሉ እያለ ያሰበው? መንግስታዊ ስርዐት ሳይፈጥሩ፣  የሚሰሩ እና ተዓማኒነት ያላቸው የመንግስት ተቋማት ሳይፈጥሩ የወንበዴ አይነት ባይሪ እያሳዮ በፖሊስ እና በፖሊስ ጣቢያ ብርታት እየዘረፉኩ እና እየረገጥኩ እቀጥላለሁ የሚል ቡድን የተደላደለ መንግስት አለኝ ብሎ የሚያስብ ከሆነ “የባለ ራዕዮ” መሪ ታሪክ ሊደገም ይችላል። ህወሓትም የህወሓትም ደጋፊዎች ማስታወስ ያለባቸው ጉዳይ ይሄንን ነው።
_______________________________
በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን  www.borkena.com ማግኘትም ይቻላል። ድህረ-ገጹ በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና የአፍሪካ ዜናዎችንም ያካፍላል።

Sunday, March 17, 2013

ህወሓት ስለምን ሰልፉን ለመከልከል ፈለገ?

ለግራዚያኒ የሚቆመውን መታሰቢያ ሃውልት በመቃወም በአዲስ አበባ ከሚደረገው ሰልፍ ጋር በተያያዘ ህውሓት ያደርጋል ብየ የወሰድኳቸውን ግምቶችን ውጨ በ"ምን ያደርግ ይሆን?" ስሜት ስጠባበቅ ነበር። ዛሬ ጊዜው ደርሶ የሆነውን ሰማን። ስለ እውነት ለመናገር የህወሃት መራሹ መንግስት ሰልፉን ሳያስተጓጉል ቢፈቅድ ኖሮ ብዙ ጊዜ ህወሓት ተለክፎበታል የምለውን የበታችነት ስነ-ልቦና ልክፍት ትክክለኛነት ራሴን ለመጠየቅ እጀምር ነበር። ሰማያዊፓርቲ ከሌሎች ከባለራዕይ ወጣቶች እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር የጠራውን ሰልፍ የህወሃትን ስነ-ልቦና በእጂጉ የሚያደማ እንደሆነ ግልጽ ነበር ለኔ። የተቃውሞ ሰልፉ ከፖለቲካዊ ፋይዳው ይልቅ ስነ-ልቦናዊ ፋይዳው የህወሃትን ሂሊና እንደሚበጫቀጭው ግልጽ ነበር ለኔ። ይሄ ጉዳይ በ"ባለራዕዮ" መሪ "ራዕይ" ላይ የተቃጣ ጥቃትም ሊሆን ይችላል- ለሕወሓት (በትክክል ወይንም በስህትተ)። ሰልፉ እንድምታው በደንብ ከተጤነ ህወሓትን እንደፖለቲካ ቡድን የሚያሳንስ ስልፍ ነበር። እኛ (ከህወሓት ወገን ያልሆነው) በየካትቲ ወር በሶስት ቀን አዲስ አበባ ላይ ብቻ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ተሰውተውብናል- ዛሬ ለተቃውሞ በተወጣበት ግለሰብ ምክንያት-- በዋነኛነት ምክንያቱ የልግዛ አልገዛም ቢሆንም። ህወሓት ደሞ ጀግና ነኝ እያለ ወደ ላይ የሚዘልበት ጉዳይ በ17 ዓመት ከደርግ መንግስት ጋር ባደረኩት ትግል 60 000 የትግራይ ልጆች ሰውቻለሁ እያለ ነው።

የኢትዮጵያውያን ትግል በሆነ መልኩ በተዘከረ ቁጥር የህወህት የታላቅነት ቅዠት መሬት ይልሳል። በተጨማሪ የህወሓት ፖለቲካ ከወራሪው ጣሊያን ፓለቲካ ጋር የሚያገናኘው ቢያንስ ሁለት ያህል ታሪካዊ ትስስር አለ። አንደኛ ህወሓት ወደ ስልጣን ሲመጣ አክርሮ የያዘው የጎዛ ፓለቲካ ጀማሪዎቹ ጥሊያኖች ነበሩ። ኢትዮጵያ ታደርግ የነበረውን ጸረ-ጣሊያን ትግል ለማዳከም ጣሊያን ከወሰዳቸው የፖለቲካ ርምጃዎች ዋነኛው ኢትዮጵያን በዘር ላይ በተመሰረተ ክልላዊ አስተዳደር መከፋፈል ነበር- ልክ ህወሓት በስራ ላይ ያዋለው ዓይነት። ሁለተኛ - በህወሓት የትጥቅ ትግል ( እነሱ እንደሚሉት"ሁለተኛው ወያኔ እንቅስቃሴ") የተቀነቀነው በትግራይ ላይ ደርሶአል የተባለው የዘር ጭቆና አንደኛው መሰረቱ የጣሊያን እና የእንግሊዝ ፕሮፓጋንዳ መሆኑ ነው። ከትግራይ ውስጥ መገለል ብቻ ሳይሆን እግሩም እጁም የተቆረጠ አይጠፋም። መስረቱ ግን የብሄር ጭቆና ሳይሆን በጣሊያን ወረራ ጊዜ ከጣሊያን ጎን ሆነው ኢትዮጵያን በወጉ ላይ በተሳበጩ አርበኞች ( ህወሃት ነፍጠኛ የሚላቸው እና በአማራነት የከሰሳቸው) የተወሰደ ርምጃ ነበር። ከዚያው ከትግራይም እንዲህ ያደረጉ አርበኞች እንደነበሩ ይነገራል።

የሆነ ሆኖ የዛሬ ህወሓት የወሰደው ርምጃ ሰልፉን ላዘጋጁ ኢትዮጵያውያን ግቡን የመታ ነው ባይ ነኝ። እርግጥ ነው ሰው ታስሯል። መታሰሩ ሳይሆን ቁም ነገሩ እስከዛሬ ባለን ተሞክሮ ህወሀት ወደ እስር እና እንዲህ ወዳለ ርምጃ የሚገባው ሲባትት እና አለቺኝ የሚላት የበላይነት ድርግም ያለችበት መስሎ ሲሰማው ነው። ስኬት ነው።
 __________________
በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን  www.borkena.com ማግኘትም ይቻላል። ድህረ-ገጹ በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና የአፍሪካ ዜናዎችንም ያካፍላል።
  

Thursday, March 14, 2013

"ልሂቃንነት" ? "ሕዝባዊነት?"

ይሄኛው ጽሁፍ ትላንትና 'ፌስ ቡክ' ላይ ላጋራሁት ሃሳብ ትችት ለሰነዘረ የ 'ፌስ ቡክ ጓደኛ'' የሰጠሁት መልስ ነው። 
ግል ለማድረግ ያህል በእስራኤል ሃገር የ"ቁንጂና ውድድር" አሽናፊ የሆነችውን ትውልደ ኢትዮጷዊ ወጣት የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ከባራክ ኦባማ ጋር ራት ስለጋበዛት አንድ የእንግዚዝ ጋዜጣ የሰራውን ዜና ብዙ ኢትዮጵያዊ በመደነቅ ሲቀባበሉት ሳይ ግነቱን እና አንድምታውን ግምት ውስጥ በማስገባት ፌስ ቡክ ላይ ለሰነዘርኩት ሃሳብ የተሰጠውን ትችት መልስ ለመስጠት ያህል ነው።  አስተያየቱ እንዲህ ይላል ፡-

"ድሜጥሮስ ደሞ ታበዛዋለህ እንኳን እሷ ልደቱ አያሌው እድሉን ቢያገኝ ጥሩንባውን አንችለውም:: ምነው አንተ critical thinker ብለህ ያልካቸው እንኳን እንደ ግብዳ ስኬት እንደዚህ አይነት ፎቶ ሲለጥፉ አልነበር By the way ain't it a big deal for a 21 years old girl won a pageant and invited to have a dinner with the head of states of US?" 
  
የኔ መልስ ፡-


ጁኒየር - እንዲህ ባለ ጉዳይ ላይ ማብዛት ችየ ባበዛው እና ባባዛው እንዴት ደስ ባለኝ። ነገር በምሳሌ እንዲሉ አጠር ያለ ምሳሌ ልወርውር። ትላንት የተመረጡት የካቶሊክ ጳጳስ ዛሬ መሄድ ወደሚፈልጉበት ቦታ ሊወስዳቸው የተዘጋጀው ደልቃቃ ሊሞዚን ምቾት ስለነሳቸው (የህሊና) "እንዲህ ያለ ነገር አያስፈልግም። ያኛው መኪና በቂ ነው" በማለት ወዳልተንደላቀቀው (ለነገሩ ያልተንደላቀቀ የመሰላቸው ራሱ የተንደላቀቀ ሊሆን ይችላል። የህሊና ሙግታቸውን ግን ልብ ይሏል!) መኪና አመሩ። ዛሬ ስለሳቸው ባየሁት የዜና ትንታኔ ጎልቶ የወጣው ይሄው ሊሞዚን እምቢ የማለታቸው ነገር ነበር። ዜና ሆነ! ፋይዳው ግን ዜና መሆኑ ላይ አይደለም። ፋይዳው በዚህ ድርጊታቸው ያስተላለፉት መልዕክት ነው። ድሎት ለለመዱት የቫቲካን ቤተኞች እና ለሰሚውም ጭምር የሚለው ነገር አለው። "exclusivity" እንደ ስኬት ለሚቆጥር፣ ትህትና ለሚጎድለው፣ ለደልቃቃ ኑሮ ሲል ለሚሞት እና ለሚገል የህብረተሰብ ክፍል እና ተከታዮቹ - መልዕክት አለው። ሰውየው ሊሞዚኑን ቢጠቀሙ ኖሮ የተለመደ(ኦርዲናሪ) ነገር እሱ ስለሆነ ብዙ ቁብ ባልተባለ ነበር። ( በነገራችን ላይ ድርጊታቸው ስለሰውየው መንፈሳዊ ህይወት ብቻ ሳይሆን ስለመጡበት ማህበረሰብ ማህበራዊ አስተሳሰብ የሚጠቁመው ነገር አለ። አርጀንቲናውያን ለማህበራዊ ፍትህ ያላቸው ግምት ጠንካራ ስለሆነ ይመስለኛል መንግስትን በቋፍ ላይ የሚያኖሩት። መንገድ ላይ ወጥተው መንግስት ሳይገለበጥ እንመለስም ብለው ስርዐት ቀይረው የሚገቡ ናቸው። እንደ ቸ ጉቬራ ያለው ቅን እና ገራገር የፓለቲካ ሰው የወጣውም ከዛው ማህበረሰብ ነው) የሆነ ሆኖ የሰውየው የወደፊት ሁኔታ እንደሚቀጥሉበት ወይ እደማይቀጥሉበት (ሪዛይን ያደርጉም እንደሆነ) የሚታይ ነው።

ወደ ቁንጂና ውድድር አሽናፊዋ ጉዳይ ስለመለስ- ልጂቱ ከእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሽሞን ፔሬዝ ቤት (ወይንም ቢሮ እርግጠኛ እይደለሁም) ተደውሎላት በሰውየው መኖሪያ ቤት ከኦባማ ጋር እራት እንድትበላ ስትጋበዝ እሽ በማለቷ ወይንም ጉዳዩን በማስመልከት ምናልባት ላናገሯት የእግሊዝ የሜዲያ አሰተያየት መስጠቷ ምንም ችግር የለውም።(በነገራችን ላይ ፕሬዝዳንት ባይሆን ኖሮ የማያቃት ሰው ደውሎ እቤቴ ራት ብይ ቢላት ትሄድ ነበር? እንደዛ ካደረገችማ ኢትዮጵያዊ እይደለችማ። ጎንደሬነቷስ የታለ ማስባሉ አይቀርም። ሃሃ)። ችግሩ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ (ያውም ተማረ የሚባለው)ዜናውን እንደትንግርት አይቶ እንደ ዱላ ቅብብል እየተቀባበለ ላይክ ሲያደርገው ማየት ስለ ፖለቲካ ብስለታችን እና ስለ ነጻነት ስላለን ግንዛቤ እንድጠይቅ ያስገድዳል። ነጻነት የእሳቤ ብቻ ሳይሆን የእኗኗር ዘየም ውጤት ነው። ነጻ ለመሆን የሚፈልግ ትውልድ እና ሕዝብ ዓለምን እና ህይወትን ሳናውቀው እንደዋዛ ነጻነታችንን እንድናጣ ቀላል የማይባል አስተዋጾ ባበረከቱ አደንዛዥ ማህበራዊ ልማዶች እና አስተሳሰቦች ብሎም እያዋዙ እያስመሰሉ ሲያስፈልግ ደሞ በጉልበት በሚገዙን ሰዎች የዓለም እይታ ዓለምን የሚያይ ከሆነ ነጻ የሆን እድሉ የመነመነ ነው። የነጻነት ጥንስሱ የለማ። ነጻነት ከንቃት ህሊና ለንቃተ ኅሊናው ጋር መሳ ለመሳ ከሚሄድ የአኗኗር ዘየ የሚወለድ ጉዳይ ነው።

ሲጀመር የ"ቁንጂና ውድድር" የሚባለውን ሃሳብ ከቁምነገር የማልጽፈው ጉዳይ ነው። የ"ቁንጂና ወድድር" ውጤት ደሞ እንዲህ የፓለቲካ ሰዎችን ግምት(በድንገት ሳይታሰብ የሆነ ነገር እይመስለኝም) አግኝቶ የዜና ሽፋን እንዲሰጠው ሆኖ ሲቀርብ መታየት ያለበት እንዲህ ባለ ፕሮፕጋንዳ ማስተላለፍ የተፈለገው መልዕክት ምንድን ነው? በመጀመሪያ ይሄ ታሪክ ስለ 'ኤሊቲዝም' ነው ስለ 'ህዝባዊነት' የሚተርከው? ኮንፎርሚስቶች ( መስሎ አዳሪዎች) ዲዛይንድ' በሆነ “ሶሻል ሞቢሊቲ” - ለ'ልሂቃኑ' ቅርበት እንዲኖራቸው ሲደረግ የሚዳነቀውን ያህል ስርዐቱን ያልተቀበሉት (“ዲሴንት የሚያደርጉት”)  በየቦታው በተቸከሉ ማህበራዊ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችካሎች ጋር እንዳይንቀሳቀሱ ተደረገው የታሰሩ ሚሊየኖችም አይታወሱም። አይዘከሩም። ስደተኞች ላይ ያለው ትርፍ ከጉልበት ዋጋ (“ከሌበር ቫሊዮ”) ጋር የተሳሰረ ብቻ አይደለም። "አይዲዮሎጂካል" ሊዮም እንዲኖራቸው ይፈለጋል። ምናልባት የምዕራቡን ዓለም አስራር አይተኽው ይሆናል።

ዜና ፣ ዶክመንታሪ፣ቃለ መጠየቅ ወይንም ሌላ ታሪክ ሲስራ በውስጡ የርዮተ-ዓለም ትርፍ እንዲኖረው ተደርጎ በብልጠት ስለሚሰራ ለማያቅ ሰው እውነቱን ከውሸት ፣ ግነቱን ከሚዛናዊ ዜና ለመለየት ያስቸግር ይሆናል። እንዲህ እንድልጂቱ ባለው ታሪክ ውስጥ የፖለቲካ ስዎችን (ያውም የዓለም መሪዎች የሚባሉትን) ትኩረት አግኝቶ ሲሰራ - ልጂቱ ብታውቀውም ባታውቀውም ማውራት የተፈለገው ስለ "ስኬት" እና "ዕድል" ብቻ አይደለም። ታሪኩ የ"ኮንፎርሚቲ '(መስሎ እንዳረጉት ሆⶈ የማደር) ታሪክ ነው ወይንስ የጥረት እና የትግል? "ኮኦፐሬቲቭ" የመሆን ታሪክ ነው? ስ ቡክ ላይ እንዳልኩት ከእስራል በኢትዮጵያውያን አይሁዶች ላይ ስለሚደረሰው የሚንሰማው ነገር የተለየ ነው፡፡ ጭራ በቅርቡ ኢትዮጵያውያኖቹ እንዳይዋለዱ ያለ ዕውቀታቸው የማምከኛ ክትባት ይከተቡ እንደነበር ሰምተናል። የእስራኤልም ባለስልጣናት ጉዳዮን አምነው በይፋ ይቅርታ ጠየቁበት የተባለ ጉዳይ ነው። ልጂቱ ተሳካላት የሚባለው እንግዲህ እንዲህ ባለ ማህበረሰብ ውስጥ ነው። ከዚህ የ"ስኬት" ዜና ጀርባ እና ከተሰጠው የዜና ሽፋን ከዚህ በፊት ከነበረው ተሞክሮ በመነሳት መውሰድ ያለብን ግምት አለ።

ልጂቱ በልጂነት አቅሟ ደረሰብኝ ያለችው ነገር አስባ፤ የተደረገላት ጥሪ እንዲፈጥር የታሰበውን አንድምታ ገብቷት ያንን ግምት ውስጥ አስገብታ  ግብዣውን ባትቀበል እና  አለመቀበሏ  ዜና ቢሆን ኖሮ ታሪኩ ከ 'ኢሊቲዝም' የበለጠ የህዝባዊነት ታሪክ ይሆን ነበር። የተለመደ እና የሚጠበቅ (ኦርዲናሪ) ከመሆን ይልቅ ያልተለመደ እና አስተማሪ ሊሆን ይችል ነበር። እንዳልኩት በልጂቱ ለመፍረድ እይደለም። ንቃተ ህሊና ከዕድሜ ጋር ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ማህበረሰባዊም መሰረት አለው። (ለነገሩ ቁጥራቸው ብዙ ባይሆንም ከልጂቱ ብዙ በማይርቅ ዕድሜ ክልል ሆነው ኢትዮጵያ ውስጥ ስለነጻነት እያነሱ የሚጥሉ እና ክህዝባዊ ሃሳብ ጋር የሚኖሩ እንዳሉ ፍንጮች የሚታዮ ይመስለኛልእንዳናደናግራቸው እንጂ)። ማህበራዊ ንቃት ህሊና ቢ
፣ጠንካራ የነጻነት ስሜት እና ነጻነት ለማግኘት ትጋት ቢኖር ልጂቱ ያለችበት ዕድሜ ብርቱ የለውጥ ፈላጊነት እና የአርበኝነት ስሜት የሚስተዋልበት ዕድሜ ነው። ነገሮችን ለማገናዘብ የሚያንስ ዐድሜ አይደለም። በታሪክ የምናውቃቸው የታላላቅ አብዮቶች ሞተር የሆኑት በዚህ የዕድሜ ክልል ያሉ ዜጎች   እንደሆኑ መዘንጋት አያስፈልግም። የሆነ ሆኖ እንዳልኩት ልጂቱን ነጥሎ ለመተቸት ወይንም አገኘሁ የምትለውን 'ስኬት' ለማሳነስ ወይ ለማጣጣል ሳይሆን የኔ ጉዳይ በማህበረሰብ ድረጃ ዜናውን እየተቀባበልን የተረዳንበትን መንገድ ለመተቸት ነው። ነጻነት ፈላጊዎችም የነጻነት ትርጉም እና ፋይዳ የገባቸውም ሰውችም አያስመስለንም።  የምንጋራቸው እና የምናጋራቸው ሃሳቦች ለንቃተ ህሊና መዳበር እና ለነጻነት ለሚደረገው ትግል ያላቸውንም ሚና ግምት ውስጥ ማስገባ የሚያስፈልግ ስለሚመስለኝ ነው።

በመጨረሻ እኔ የማደንቃቸው "critical thinker" እነማን ናቸው? እሱን እብራራ እና እመለስበት ይሆናል እንደሁኔታው።


_________________________


 ወድ አንባቢያኖቼ- ቦርከና ብሎግን ወደ ዌብ ሳይት ለመቀየር እየሰራሁ ነው።   በቅርቡ ያልቃል ብየ እጠብቃለሁ። ስራው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ አሳውቃለሁ። በ'ፌስ ቡክ'ም ቦርከና የራሱ ገጸ-ተከፍቶለታል።  መከታተል ለምትፈልኩ ይሄን ሊንክ ተከትላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።   https://www.facebook.com/pages/Borkena/294762583969356?ref=hl

Saturday, March 2, 2013

We need an Adwa Mentality

Just for the record, Adwa is not the cause of our pride. Adwa is an outcome. It is an outcome of well constructed social values, invincible psychology, realistic world view free of illusion, self respect and dignity, selflessness and last but not least spirituality. Of course all these values are building blocks of patriotism. 

Patriotism is not a luxury, an illusion or mere love for adventure as some tend to put it. It’s a response to a situation created by others. It’s a pursuit of dignified life and the sanctification of freedom -not ’personal freedom’, if there is such a thing in the real sense of the phrase. Patriotism is an act of doing something great with one’s life in the interest of freedom of your people whose values you cherish most.

Patriotism has to be distinguished from pursuit of personal desires and goals so strongly (often times at the expense of collective desires, societal values and even the values of being human) in a fashion we observe in Hollywood movies where a loner wins his battle at the end of the day and is celebrated as a person of ‘extraordinary’ achievement. Once celebrated, the celebrated could be used in the conquest of collective values and creation of other loners. That is not patriotism.

Patriotism is not born out of the desire to create personal wealth or fame. It springs from spiritual and philosophical approach to life, and attachment to society, not detachment from society. Personal desire that is not related to the task of defending the interest, freedom and dignity of one’s own people has to vanish first for the noble virtue of patriotism to flourish. Patriotism is a virtue that people with great insight about life and imagination pursue. It’s partly divine in that all the great messengers in different religious traditions lived up to the ideals of patriotism-living for what they believed to be true and something that benefit others ,not just self. In an organic society patriotism is a way of life and mass action. Patriotism is not an enterprise of loners! Patriotism is essentially a rejection of mediocrity in life. It is an act of defiance of what is ordinary and pursuit of the extraordinary. Patriotism is real, deep, fulfilling and rewarding in terms of satisfaction. He who is selfish cannot be a patriot.

Selfishness is at odds with values essential for patriotism. Selfishness is the work of illusion. It tends to impel the thinking that what is noble is ‘self.’ For selfishness, the ‘collective’ is a source of threat and yet a means to achieve an end for ‘self.’ For patriotism the ‘collective’ is a friend, not a source of threat. Selfishness emanates from, among other things, greed and immorality, which could in a way be related to atheism of a sort.

Selfishness pretends to be genius and rational while it is an ultimate expression of irrationality. Selfishness could sell ones country out to others- irrespective of the way it manifests itself. The destructive nature and aspects of selfishness is not so much related to ‘bounded rationality.’ It’s related to illusion of faith in “self.” Selfishness in matters related to the interest of one’s own country is fundamentally a declaration (whether it is in action, word or some other forms) that one do not belong to the society she/he came from. It could be a way of looking society, from which one came from, down. It could be an act of venerating “self” and venerating the party that one thinks is in the service of ‘self’ as distinct from society or country. Selfishness sounds like affirming “self” while it is denial of ‘self’? What is “self” without the whole? What is in selfishness is fear. What is in Patriotism is faith and courage.


Patriotism is not something easy to fight with. Of course a  culture that is a fertile ground for patriotism is prone to be conquered as it breads resistance for domination. What would a thinking enemy do is to invest with all its power to weaken attributes and human values essential for patriotism. I cannot help thinking about one particular Ethiopian comedy at this point.


One of the inorganic practices with which the Americans create an individual celebrity or an idol – “American Idol show” – is replicated in Ethiopia in the past ten or so years. Obviously, the label is changed to “Ethiopian Idol.” Clearly, the idea does not fit well in a society that idolizes selfless act, patriotism, and a culture that does not idolizes pursuit to self-interest. In the comedy video I linked below, Dereje, the comedian, seemed to brace the idea of selecting an individual idol (celebrity) on stage and runs his own “Yegele Idol show” (literally ‘my personal Idol Show’). The title itself seem to ridicule the idea of idol show. Then, contestants started to show what they got, their singing talent. Demelash Gobeze, dressed in Ethiopian attire and in a very Ethiopian way, faced the judges.

When asked as to which musicians he admire, Demelash answered that he admire the famous Ethiopian singer -Tilahun Gesesse. The judge threw another specific question: “which foreign musician do you admire?” Demelash responded I admire “Miklo jakseno” [Micheal Jackson]. The judge can’t help asking “why.” Demelash was bold when he replied that he admire Michael Jackson because Michel Jackson admire him which suggests that the idea of ‘celebrity’ is strange for Demelash. It does not necessarily mean that Demelash is not familiar to the concept “celebrity.” It may rather mean that Demelash has his own celebrities, most likely Ethiopian patriots in history.

Demelash was then invited to show off his talent: singing. Demelsh started singing about his world- something that is very close and dear to his heart, which is Ethiopia and what Ethiopia means to him. He was singing it in an Adwa mentality- self-respect, patriotism and loving who you are as people.

The geographical description in his song is not merely geographical description. Mountains are not admired in the sense of admiring nature. There appears to be a social value embedded in them- something related to bravery, to the idea of standing tall and to valor, which all sit well with patriotism. When the judges, one of whom was comedian Dereje, gave a verdict that Demelash didn’t make it this time around, Demelash was not shown crying like contestants we see in American Idol. He was very calm and requested the judges to give him one more chance. The judges did so. Nothing changed. Demelash was angry and had to pull his sword, which was not visible at first, wanted to show them of an Adwa mentality: defiance of judgements of others. It is conceivable that what was judged, for Demelash, was Ethiopia. His disappointment did not end in self-pity. It rather triggered defiance and Adwa mentality. Well, may be the comedy is not presented very well. Yet, it’s entertaining and educational at the same time. Moral of the story is how patriotic values are subtly ridiculed on stages and how selfishness and conformity are propagated as an attributes of winning personality and “success.” Something selfish and what could rather be displeasing is rewarded. Obviously, such a practice is not about promoting art. It’s about conquering culture and collective values.

Selfless people are very hard to corrupt which is not the case with selfish people – and which why no selfish people could make of a patriot or defend the interest of a country. Adwa was a showdown between different values as much as it was a military showdown. And one of the significances of Adwa is the defeat of selfishness (call it Banda or whatever), defeat of people who bought into the propaganda of “civilising mission” which is the equivalent of what is now “progress and freedom.” The latter, of course, is an embodiment of subtle continuity of domination agenda and I don’t see any convincing reason to think that the domination agenda will die any time soon other than constantly changing its forms.


Just like people we call ‘banda’ in history were given ‘opportunity‘ for buying into the world view of the then “civilizers” (colonizing powers), those who bought into the world view of contemporary “progressive” powers are given ‘opportunity‘ – and with it the task to promote (through cultural diplomacy and other means)  the world view of those with the lust for wealth and domination(power).

The struggle is between opportunism and principle, between morality and immorality, between selfishness and selflessness. Clearly, what is moral, selfless and valuable for patriots might sound naive to opportunists. Sadly, opportunism and immorality are, apparently, shaping the world in multifarious ways and they are given ‘rational and progressive’ look while they are simply manifestations of selfishness and immorality.
The image of freedom and moral living is being deformed before our eyes. Attacks are intensified on aspects of society that foster moral living, values that promote the whole rather than the individual and aspects of societal life that give society human values. For example, the attacks (with the use of selfish citizens, popular comedy shows, mainstream media or other means) on religion- whether it is Islam or Christianity -is evident and has now become a trend. It’s not hard to imagine that the attack is meant to weaken the source of strength for collective values. It is a subtle way of disempowering and weakening the sources from which society draws its strength. The attacks would in no way help even the freedom of the individual ultimately.

The nature of freedom is not complex. Yes, there could not be an absolute freedom but freedom could be better. It is nothing other than selfishness and illusion to promote a fundamentally slavery like situation as ‘freedom.’ It’s wicked. It’s immoral. And worst of all, when someone is in this kind of business, she/he need not and should not sell it as something very desirable by portraying selfish acts as if they are an acts of caring for the freedom of the society.

A mentality that made Adwa possible is critically important in this age to restore dignity and freedom in the real sense of the term. I am not in illusion to believe that those who work with and for TPLF, or some other powers will develop an Adwa mentality as selfishness could be addictive in its own right. What I hope is for innocent citizens not to imitate selfish ones and not to be overwhelmed by an apparent and temporary success of deceit and opportunism which is sometimes being sold as ‘modernity.‘ What I hope is a generation that do not take selfish ones seriously!

I have to reiterate that selfish citizens are harmful to society in that they could collaborate with an entity (be it local or foreign) while pursuing selfish motive and harm the very existence of the country. They may even go to the extent of fighting on the side of enemy. That is what people we refer to as ‘banda’ did to Ethiopia.

Life is short and it could be even shorter. It’s not worth to live the ideals of opportunism and selfishness at the expense of the interest of our country and our people. Whoever managed to kill a selfish desire has a great potential to be a hero, a savior and patriot. The satisfaction that springs from such deeds and acts is immeasurable. It’s as eternal as Adwa and it is a righteous act. We need an Adwa mentality and stand tall for the values of being Ethiopian, for the values of freedom and for the values of being human, not for sordid gains and the illusion of “self.”

Happy Adwa 117th Anniversary!

Blog Archive