Thursday, December 13, 2012

አራተኛው ፓትሪያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው።


ደጀ ሰላም ዌብሳይት ላይ አራተኛውን ፓትርያርክ በሚመለከት ለሚሰጠው የህዝብ አስተያየት (ፓል) የሰጠሁት መልስ ነው።
             ***
ትላንትና በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አዲሱ አበበ ኮማንደር አሰፋ ሰይፉ ከሚባሉ ኢትዮጵያዊ ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርጎ ነበር። ኮማንደሩ ስለቀደሙት ሊቃነ ጳጳሳቶች በፈተና መጽናት ያስታወሱን ከዚህ በፊት ቤተ-ክርስቲያኗ ስለነበራት ጥንካሬ አንደኛው ምንጭ አንደነበረ ጠቋሚ ነው። ከአቡነ ሚካኤል አና አቡነ ጴጥሮስ ተጋድሎ የማይተናነስ ጽናት ታይቶባቸዋል። ያንን ጥንካሬዋን ለመስበር ስለተፈለገ ነው ቤተክርስቲያኗ የፖለቲካ ዱላ ያረፈባት። አራተኛውም ፓትርያርክ አንደቀደሙት መሆን ሳይችሉ ቀርተው ሃገራቸውም ቤተክርስቲያናቸውንም ትተው ተሰደዋል። ነገር ግን ከዚያ የባሰአጂግ የከፋውን ጥፋት ያጠፋ ወገን ነበረ (ወይንም አለ)። ጊዜ የሰጣቸውን የፓለቲካ ጉልበት አና ሃይል ተጠቅሞ የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊ ህግ በተጣሰበት ሁኔታ የፕትርክናውን ቦታ አንዲይዙ የተደረጉት ሰው የክርስቲያናዊነት ስነ-ምግባር በውስጣቸው ቢያይል ኖሮ ፣ለቤተክርስቲያኒቱ ያላቸው ወገንተኝነት ቢያይል ኖሮ የቤተክርስቲያኒቷ መንፈሳዊ ህግ አደተጣሰ አያወቁ ፕትርክናውን መንበር ተቀብለው ባልያዙ ነበር። ቀብተው የፕትርክና ስልጣን የሰጧቸው ጳጳሳትም ወይአንደሃይማኖት መሪ የሚጠበቅባቸውን የተጋድሎ ስራ አልሰሩም። ወይ ደሞ ነገሩን ደግፈውት ነበር ማለት ነው።

ስለዚህ ማነጻጻር ካስፈለገ በመጽናት ደከም ማለት አና ክህደት በእኩልነት ሊዳኙ አይገባም። ቤተክርቲያኗ በፓለቲካ ጣልቃ አንደተገባባት በጊዜው በፖለቲካ አንጻር ጣልቃ የገቡት ሰው(የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ) በህይወት ስላሉ በማያሻማ ሁኔታ የእምነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። "ይቅርታም" የጠየቁበት ጉዳይ ነው። የአሁኑም የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት -ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ -ጉዳዮን በህሊናቸው ዳኝተው ባለፈው ሰሞን ደብዳቤ አንዲፅፉ ያነሳሳቸው ምክንያት ይሄው ይመስለኛል። ያንን በማድረጋቸው ደሞ የደረሳባቸውን ነገር መገመት አንችላለን። በዚያም ምክንያት ይመስለኛል የጻፍትን ደብዳቤ "ስቤዋለሁ" (አንደመሰረዝ አና ውድቅ አንደማድረግ ነው) አሉ።  "ያገር ክህደት ፈጽመዋል" አንደሚባሉት አስረኞች ፕሬዝዳንቱን  "ይቅርታ" አስጠይቀዋቸው ነገሩን  በጫና እና በማስፈራራት ያኔ አማጺያኑ ሃገሪቱን ሲቆጣጠሩ ወደነበረው ሁኔታ  አየወሰዱት ይመስላል።

ደበስበስ አድርገን ጉዳዮን በፓለቲካ መነጸር ያየነው አንደሆነ ---በእምነት ጣልቃ ገብነት መሆኑ ነው። በቲዮሪ ደረጃ ህገ-መንግስታዊ መሰረት ተሰጥቶታል ከሚባለው የሃይማኖት ነጻነት ጋር የሚያያዝ ይሆናል። ፈረጥ አድርገን እንናገረው ከተባለ ደሞ በተጠና ሁኔታ ቤተክርስቲያኒቱ አንደጠላት ተፈርጃ ስለነበር እና መዳከም አንዳለባት ይታመን ስለነበረ ለዚሁ የማዳከም ስራ ይተባበራሉ ተብሎ የታሰቡ ሰው ወደ ስልጣን መተው የደረሰው ነገር ሁሉ ደረሰ። እግዚያብሔር ጊዜ አለው አንደሚባለው ጊዜውን ጠብቆ መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት አሳየን። የተጣሰውን የቤተ-ክርስቲያን ህግ ማስከበር የሚቻልበት አጋጣሚ ተፈጥሮአል።  ጉዳዮን አንደ ፕሬዝዳንት ግርማ በአቅም ማነስ ማስፈጸም ባይቻል አንኳን በሚያሳምን ሁኔታ የቤተክርሲያኒቷን ህግ ተከትሎ ፍርድ መስጠት አና ሃሳብ መሰንዘር ይገባ ነበር።  በጳጳሳት መካከል የሚደረገው ውይይት ይሄንን እውነታ በመገንዘብ ለእውነታው ተገዢ በመሆን፣ ለቤተክርስቲያኒቱ ቀኖኗ አና የእምነት ነጻነት በመቆርቆር መንፈስ ቢካሄድ ኖሮ ስምምነት ላይ መድረስ በጭንቀት የሚያስምጥ ጉዳይ ባልሆነ ነበር።የህዝብ አስተያየት መሰብሰብም ባላስፈለገ ነበር። ምክንያቱም ፓትርያርኩ መንበራቸውን አንዲለቁ ስለተደረገበት ሁኔታ አና "አምስተኛ " ተብለው የተነሱት ሰው አንዴት ወደ መንበሩ አንደመጡ ፣ በቤተክርስቲያን ሰዎች በኩልም( ጳጳሳት) በፍርሃት ወይንም ያለፍርሃት ጣልቃገብነቱን አንደችግር ሳይቆጥሩ የድርጊቱ  ተባባሪ የሆኑበትን ጉዳይ ለህዝብ ይፋ ካልተደረገ - የሚሰጠው ሃሳብ የተዛባ አንደሚሆን አያጠያይቅም። ፓትሪያርኩ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለባቸው!  ከቤተክርስቲያኒቱ ህግ አንትጻር ፣ከተደረገውም ፓለቲካዊ ስህተት ፣ የእምነት ነጻነትን ከማስከበርም አንጻር ትክክለኛው ነገር ይሄ ነው። አራተኛው ፓትርያርክ በጉልበት የተነጠቁት መንበሩ ከተመለሰላቸው በኋላ ራሳቸው በእድሜም በጤናም ምክንያት የቤተክርስቲያኒቱን ጥቅም ግምት ውስጥ በማስገባት የሚወስዱት እርምጃ ይኖራል። የተደቀኑትንም አስቸጋሪ ሁኔታዎች አያነሱ መወያያት ይቻላል።

በሌላ በኩል ግን ፕሬዝዳንት ግርማ ደብዳቤያቸውን ከሰረዙ በኋላ ይዘውት የተነሱትን - አራተኛው ፓትርያርክ ወደ ሃገራቸው መመለስ ይችላሉ ነገር ግን በምርጫ አይወዳደሩም ወይንም መንበር አይዙም አይነት ኣስተሳሰብ -በቤተ-ክርስቲያን 'አባቶች' (ጳጳሳት) በኩል አንዲንጸባረቅ ማድረግ 'አልሸሹም ዘወር አሉ' አንደሚባለው ይሆናል። አሁንም ቤተክርስቲያኗ በጉልበት አንደተያዘች ነው የሚያመላክተው። ለስሙ ውይይት አየተባለ ይደረጋል አንጂ በጉዳዮ ላይ የፖለቲካ ውሳኔ አንደተወሰነም የሚያመላክት ነው። ከላይ አንደጠቀስኩት ጳጳሳቱም ተባባሪ ሆነው ለሌላ ሰው መንበር ሰጥተዋል። ምናልባት(ምናልባት!) የነሱ ሁኔታ ጠንካራ ቢሆን ኖሮ ያኔ ፓትርያርኩ እስክመሰደድ ላይደርሱ ይችል ይሆናል። ያኔ ስህተት ተሰራ። አለቀ ደቀቀ። የደረሰውም ነገር ደረሰ። አሁን ግን ተመልሶ በዛው በስህተቱ መንገድ መቀጠል በጣም አሳፋሪ ነው።  በክህደቱም አንደመቀጠል ነው። የቤተክርስቲያኒቱንም ጥቅም አያስከብርም። ጉድዮ የጳጳሳት አና የሲኖዶሱ ብቻ አንዳይሆን የሰንበት ተማሪዎችም ምዕመኑም የሲኖዶሱን አባላት አጋጣሚ ፈጥሮ ይሄን ጉዳይ በአጽኖት አንዲይዙት ማድረግ ይገባል።  ችግሩን አንደ ሃይማኖተኛ ሳይሆን አደዜጋ ያየነው አንደሆነም የእምነት ነጻነት አለመኖር ከነጻነት አለመኖር አና ህገ መንግስታዊ ስርእት አለመኖር ጋር የተያያዘ ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንደሚያደርጉት ትግል መደገፍ አለበት። የአንድን ጠባብ ጉልበተኛ የፖለቲካ ቡድን ቅጥ ያጣ የበላይነት ለማስከበር ሲባል የዜጎች  መብት አና ነጻነት በየመስኩ መታፈን አና ከጥቅም ውጭ መሆን የለባቸውም። አራተኛው ፓትርያርክ በጉልበት የተነጠቁትን መንበር እንዲያገኙ መደረግ አለበት። የፖሉ ፋይዳ አልታየኝም።

4 comments:

  1. merkorios he was a cadre

    ReplyDelete
  2. ምነው ይህን ያህል በኢትዮጵያ ምድር ሰው ጠፋ እንዴ? አቡነ መርቆርዮስ ተመልሰው ወንበር የሚይዙት? በጐንደር ሀገረ ስብከታቸው ጊዜ ከመላኩ ተፈራ ጋር በመተባበር በሠሩት ግፍ ይሁንታን አግኝተው ነው ወደ ፕትርክናው የመጡት፡፡ ከዛም ሕዝቡን በትነው ራሳቸውን ወደው ስደታቸውን ወደ አሜሪካ አድርገዋል፣ የንፁሃን ደም ባይኖርባቸው ኖሮ የሆንኩትን ልሁን ብለው ወደ ገዳማቸው ሄደው በንጽህናና በቅድስና ይኖሩ ነበር፡፡ ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ እንደተባለው ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፀሎቱ በእግዚአብሔር ደም የተመሠረተችው ቅድስት፣ ንጽሕት፣ አሃቲ ሃይማኖታችንን ከጠላት ሰይጣን ጠብቆልን 6ኛውን ፓትርያርክ ባርኮ ቀድሶ እንዲሰጠን የዘወትር ልመናችን ነው፡፡ እመ ብርሃን በምልጃዋ አትለየን፡፡

    ReplyDelete
  3. በምትለው ነገር ላይ እምነት አና እውቀት ካለህ ራስህን ሳትደብቅ ያለህን አይታ ከማስረጃ ጋር ብታቀርብ አንድ ነገር ነበር። እስኪ ያለ አግባብ የተነጠቁት መንበራቸው ይመለስ አና አንተ ያነሳኽው ጉዳይ እንቅፋት ይሁን።እኔ እንደማምነው አቡነ መርቆርዮስ ከመንበር የተነሱበት ምክንያት ቤተ-ክርስቲያኒቱን ከማዳከም አንጻር የነበረው የገዥው የህወሃት መንግስት ፓሊሲ አካል አንጂ በፓትርያርኩ ላይ አንደግለሰብ የተቃጣ አልነበረም። እኔም የፓትርያርኩ መንበር ይመለስላቸው ብየ ስጽፍ ጉዳዮ ስለ ቤተ-ክርስቲያን ቀኖና አንጂ ስለ አቡነ መርቆርዮስ አይደለም። አረመኔ የሚባለው ደርግ አኮ ያላደረገውን ብልግና ነው ጀግና ነን የሚሉት ህወሃቶች "ጀግንነታቸውን" ያሳዮበት። ከዚያ በኋላ አቡነ ጳውሎስ በእምነት አንጻር ያደረሱት ጥፋትስ ያደባባይ ሚስጥር ነው። የወንጀል ተባባሪነትን በተመለከትም የተመዘገበ የኦዲዮም የቪዲዮም ማስረጃ ያለው ከአባ ጳውሎስ ጋር በተያያዘ ነው። የቤተ-ክርስቲያን ቀኖና ይከበር ነው ጥያቄው። በዚህ አጋጣሚ "Anonymous" በሚል ባትፅፍ እመርጣለሁ። የምትሰነዝረው ሃሳብ በግላጭ ባለቤትነቱ የማን አንደሆነ አንዲታወቅ ያስፈልጋል። በምታምንበት ነገር ላይ ስለምትፅፍ/ስለምትጽፊ አንደዚያ ማድረግ ከባድ ነው ብየ አልገምትም። ያለበለዚያ ባለቤቱ የማይታወቅ ሃሳብ መፍቀድ ያስቸግረኛል። ምስጋና።

    ReplyDelete
    Replies
    1. The church is in an extermly delicate postion. The creation and propagation of a thrid entity claiming indepence is extermely worriesome. As for now no doctrinal divison is claimed but as the time moves that is not very unlikely. The thrid chruch "independent" will bread the fourth and the fivth, claiming all sorts of thing be it reform or any other thing. This will then enter Ethiopia creating a possiblity that, this generation will not pass this great church to the next. Those of us calling for the retrun of his holiness are not doing so based on petty poltical gains as TPLF is doing. Religion ,nationalism ,history are all here at crossroad.

      Delete

Blog Archive