Thursday, March 28, 2013

9ኛው የኢህአዴግ ጉባዔ ተጠናቀቀ


ማርች 28፣2013 (borkena) በባህርዳር ሲካሄድ የሰነበተው የኢህአዴግ 9ኛ ጉባዔ ተጠናቋል። የአሜሪካ ድምጽ እንደዘገበው ጉባኤው ኃይለማርያም ደሳለኝን በድርጂቱ ሊቀመንበርነት ፤አቶ ደመቀ መኮነን በድርጂቱ ምክትል ሊቀመንበርነት መርጧል። ከአመራር አባልነት የተገለሉም እንዳሉም ታውቋል። ከተገለሉት አመራር አባላት በኢህዴግ ውስጥ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ የበላይነት እንዳለው የሚነገርለት የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩ አርከበ እቁባይ ፣ስዮም መስፍን፣ ጸጋየ በርሄ፣አባዲ ዘሙ እና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ  እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል።

በጉዔው ላይ የአቶ መለስ ዜናዊን የህይወት ጉዞ ያመላክታል የተባለ ዝክረ-ወዳሴ የቀረበ ቢሆንም በቀረበው ወዳሴ “ብዙ” የጉባዔው ተሳታፊዎች አልተደሰቱም ተብሏል። በዝክረ-ውዳሴው ካልተደሰቱት ውስጥ የሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ባለቤት  ወይዘሮ አዜብ መስፍን አንዷ ሲሆኑ ዝክሩ የዘለላቸው የመለስ የህይወት ጉዞዎች አሉ ባይ ናቸው። ለምሳሌ ያህል መለስ የ”አዲስ ራዕይ” ዋና አዘጋጂ የነበሩ ሲሆን አልተመለከተም በለዋል -ወይዘሮ አዜብ።

በአጠቃላይ ጉባኤው  የአመራር ድክመት ስለመኖሩ ጠቁሟል። በሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ መሰረት ደሞ ከአመራር አባልነት የተገለሉት የህወሓት ከፍተኛ አመራር አባል የነበሩት አቶ ስዮም መስፍን ስለ ግንባሩ ውህደት አንስተዋል። ሪፓርተር የአቶ ስዮም ያለውን ሃሳብ እንደሚከተለው ጠቅሶታል፡- ‹‹ኢሕአዴግን የማዋሀድ ጥያቄ ከተነሳ 22 ዓመት አልፎታል፤ ጥናቱ መጀመር አለበት፤››

______________________________________
በዚህ ብሎግ ላይ የሚወጡ ጽሁፎችን www.borkena.com ማግኘትም ይቻላል። ድህረ-ገጹ በተጨማሪም ወቅታዊ የሆኑ ዓለም ዓቀፍ እና የአፍሪካ ዜናዎችንም ያካፍላል።

No comments:

Post a Comment

Blog Archive