Wednesday, February 6, 2013

"ጂሀዳዊ ሀረካት "

ጂሀዳዊ ሀረካት ከሚለው ወንጀል ነክ ፓለቲካዊ ተውኔት ጀርባ በዋነኛነት ልናይ ይገባል ብየ የማስበው የህወሀትን ስነ-ልቦና ነው :: ከዚያ ቅጥ ካጣ የትምክህት ስነ -ልቦና ጀርባ ደሞ የህወሀት ደጋፊዎችን ስነ -ልቦና እና ከስርአቱ ጋር አለን የሚሉትን "የደም " ትስስር ማሰብ ያስፈልጋል :: ጀሀዳዊ ሀረካት ብለው ባቀናበሩት ህወህት -ወለዳዊ (ልብ ወለድ እንዳልለው የጥላቻ እና የትምክህት ፓለቲካ ወለድነቱ ያደላል ) የተፈጠረው ቁጣ ባብዛኛው የመጣው (እስካሁን እንዳየሁት ) የህወሀት ደጋፊ ካልሆኑ ኢትዮጵያውያን ነው ::

የህወህት ደጋፊዎች ወይንም "የደም ' ትስስር ያላቸው ከሌላው ኢትዮጵያዊ የከፋ እፈና ስላለባቸው ነው እንዳይባል ከዚህ በፊት በተለያዮ ጥቅማችን ወይ መብታችን ተነክቶአል በሚሉብት ጉዳይ መቀሌ ላይ ሰልፍ ሲወጡ በኢትዮጵያ ቴሌቭዢን እንደታየ የሚዘነጋ እይደለም :: ስለዚህ ዝምታው የተቃውሞ ነው ለማለት ያስቸግራል :: ዝምታው የድጋፍ ቢሆን ነው ::

እየደገፉ ያሉትን ፓለቲካ ከዚህ በፊት ከነበረው እየከፋ ከሊቀመንበሩ መለስ ዜናዊ ሞት በኍላ "ዲፕሎማሲያዊ ' በመጠኑ ደሞ ስልታዊ ይመስል የነበረው ፓለቲካቸው የነበረችውንም ባህሪውን አጥቶ የዕውር የድንብር እየሄደ እንዳለ ሊቀመንበሩ ከሞተ በኍላ ያሉት ተከታታይ ፓለቲካዊ ሁነቶች በግልጽ እያሳዮ ነው :: በዚህ የመደናበር ሂደት ግን እየደረሰ ያለው ጥፋት ወደፊት በቀላሉ መመለስ የሚቻል ነገር ለመሆኑ እጠራጠራለሁ ::

ሕወሀት እና የህወሀት ደጋፊዎች እያደረሱት ያለው ጥፋት እና ህዝብ እየኖረው ያለውን የግፍ ጽዋ ለመታገል እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት ( እስከማውቀው ደረስ ) ተመጣጣኝ እይደለም ::

ክርስቲያኑ ቤተ -ክህነትን ከህወሀት ካድሬዎች አስረክቦ ከእጂ በደረት ብዙ በማይለይ ሁኔታ በተሽናፊነት ያመነ ይመስላል :: ጠንከር ያለው ተቃውሞ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኩል ስለነበረ ህወሀት በዛ ላይ የወሰደው ወታደራዊ የሚመስል ርምጃ የፓለቲካ ርምጃውና "በፍትህ ተቋማት "አማካይነት እየወሰደ ያለው ርምጃ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ የሚያረግበው ስላልመሰለው ጉዳያቸውን ሌላ መልክ ለመስጠት እያደረግ ያለውን ነገር እያየን ነው :: ውሸት ጥላቻ እና ትምክህት የህግ እና የፓለቲካ ሽፋን እግኝቶ ;ውሸት እና ትምክህት ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገለት ስው በሀገሩ ባለቤት እንዳይሆን የተደረገበት ሁኔታ ሳያንስ : ጭራሽ መንፈሳዊ እምነቱንም ጭምር በጉልበት እንዲተው መደረጉን አስከፊነት ለመግለፅ ቋንቋ ያጥራል ::

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በስህተት 'ኤዲት ' ሳያደርግ ለቀቀው በተባለው ከታች ባለው የቪዲዮ ክሊፕ ላይ አፉን በውል የፈታ የማይመስል የህወት ሰው እጁን በካቴና አስረው ባዶ ክፍል ውስጥ ለምርመራ ያስቀመጡት ልጂ ላይ ሲሳለቁ ማየትም የሚፈጥረውን ስሜት ለመግለፀ እንዲሁ ቋንቋ ያጥራል ::

Clik here to watch the clip

የህወሀት ሰዎች እንዲህ የሚሳለቁበትን ልጂ ልጂ እያለን የማውቀው መልክ በመሆኑ ልቤ እጂጉን አዝኗል :: እሁንም ከሚያሳርፉበት ዱላ ከሚያደርሱበት ግርፋት የበለጠ የሚያሳዝነኝ እንዲህ እጁን እስረው የሚለፋደዱት ነገር ነው :: በዚህ ድርጊት ህወህትን ልታዘብ አልችልም :: ተው ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም ሊሉ ያልቻሉትን ደጋፊዎቻቸውንም ወላጆቻቸውንም አልታዘብም ::
የማዝነው በራሳችን ነው -እንዲህ እንዲሆኑ በፈቀድንላቸው እና ስልጣኔ እና ያስተሳሰብ እድገት በሚመስል የባርነት እስተሳሰብ ለተናጥን::

No comments:

Post a Comment

Blog Archive