Thursday, January 20, 2011

በላ ልበልሀ - ከዘመን ጋር

መቼስ ይብዛም ይነስም የሆነ ጊዜ የሕይወትን ትርጉም መጠየቃችን አይቀርም:: አንዳንዶቻችን የምንወደውን ሰው (አባት;እናት; ጓደኛ ወይንም ሌላ) ባጣን ማግስት የሕይወትን ትርጉም የምንጠይቅ አለን:: አንዳንዶቻችን ከፍቅረኛ ጋር አምባጓሮ ተፈጥሮ ስንለያይ(ብሬክ አፕ ይሉታል ፈረንጆቹ) የህይወትን ትርጉም የምንጠይቅ አለን:: አንዳንዶቻችን ደሞ ያሰብነው እቅድ ሳይሳካ ሲቀር ለዘላለሙ የማይሳካ ይመስል ወዲያው የህይወትን ትርጉም መጠየቅ የምንጀምር አለን:: ይሄ በግለሰብ ደረጃ ነው:: እንድንጠይቅ የሚያደርገን ጉዳይ እና ራዲየሱ ግን እኛ እና በእኛ ዙሪያ ባሉ ሰዎች ዙሪያ ነው:: ከዚህ ያየለ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ ሌተ ከቀን የሚታገሉ እና የሕይወትን ትርጉም በዛ የሚሰፍሩ የመንፈስ ልዕልና የገነቡ ዜጎች ደሞ አሉ:: ያው ኢትዮጵያ በታሪኳ ብዙ እንደዚህ ያሉ ግለዘቦችን አፍርታለች:: በርግጥ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በተለይ ህዋሀት አመራር ያንን የኢትዮጵያን ወርቃማ ዘመን ጨለማውን ጎኑን ብቻ በማጉላት በመንፈስ ልዕልና የኖሩ ኢትዮጵያውያንን ታሪክ ካፈራረሰው በኍላ ሌላ ታሪክ ጽፏል:: ለጊዜው እሱን ወደ ጎን እንተወው እና ለህይወት በምንሰጠው ትርጉም ውስጥ ዘመን የራሱ የሆነ ተጽዕኖ አለው የሚል ጠንኳራ እምነት አለኝ:: ለመሆኑ ከህይወት ትርጉም ጋር ተያይዞ የሚነሳ ጥያቄን ለመመለስ ዘመን የሰጠን ነገር ምንድን ነው?? ዘመን የወሰደብንስ ነገር ምንድን ነው??? በዘመን ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ይቻላል ወይንስ ከዘመን ምርኮኛነት መውጣት አይቻልም?? በዚህ ጉዳይ ላይ እንድንወያይ እጋብዛለሁ:: በላ ልበልሀ ...

.

No comments:

Post a Comment

Blog Archive