Saturday, April 4, 2009

ሁለት ሞት:

ሁለት ሞት :

አገር ጥሎ ተኮብልሎ
ከኑሮ ወጥመድ ላይመለጥ
ክልብ ሆኖ ላየ ...ከፀሀይ በታች ...የሚለውን አስቦ
አንደኛው ከሌላው ብዙ ለማይበልጥ
እንዲህ ሊኖር ፍዳ ተከፍሎ
አነሰም አደገም የነበረን ; የወንዝን ጥሎ
እለት ተለት እየተንከባለሉ እንደ አለሎ

ደሞ ይነገራል!
... ስም አይሞት ይባላል
ይኼው ሞቶ በቁም ተቀብሮ
በሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሂሳብ
ሰው ሲኖር ከመጠሪያው ተሰውሮ
ቀሪ ሀብቱን ስሙን ቀይሮ
ስም የማይገዛ ከሆነ
እንደምንስ ሊሸጥ ተወሰነ
ብዙ ሰው አለው ""ምን አለበት ?!""
እኔ ግን አልኩት ሁለት ሞት

መጋቢት 27, 2001 ዓ.ም
ድሜጥሮስ

No comments:

Post a Comment

Blog Archive