የዳግማዊ
ምንሊክ አና የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሃውልቶችን ከስፍራቸው ለማንሳት ዝግጂቱ አንደተጠናቀቀ ስሰማ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት
ቡድን በትክክልም የ”መለስን ራዕይ”ለማስፈጸም ደፋ ቀና አያለ አንደሆነ ተረዳሁኝ። ከዚህ በፊት በሌላ ፅሁፍ አንደገለጽኩት የ”መለስ ራዕይ” የሚባል ነገር አንደሌለ እና የመለስ አየተባለ ለመሸጥ የሚሞክረው
“ራዕይ” በትክክል የህወሃት ለመሆኑ አመላክቻለሁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የነበረው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሃገሪቱን አሰለጥናለሁ”
የሚል ነበር። አስቡት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ጉዳይ ወዝውዞት ከጣልያን ሃገር ድረስ ጦር ሰብቆ ሲመጣ። አቡነ ጴጥሮስ በግፍ ሃውልታቸው
የቆመበት ቦታ ላይ የተገደሉትም ዛሬ ህወሃት በሚጠቀመው ቋንቋ ሲመነዘር “ጸረ-ልማት” ናቸው በሚል ነበር።
ሲጀመር
“ልማት” የሚለው 'ዲስኩር' ከጥርጣሬ ይልቅ የህዝብን አመኔታ አንዲገዛ ማድረግ ያስፈልጋል። መረጃ በማፈን፣ ውዢንብር አንዲነግስ
በማድረግ ደሞ የህዝብን ትኩረት ለጊዜው በማስቀየር ሌላ የፓለቲካ ጥፋት ከበስከጀርባ መስራት ይቻል አንደሁ አንጂ የሕዝብን አምነት
መግዛት አይቻልም። በዚሁ ሃውልት ጉዳይ አንኳን የሚወራው ዜና የተደበላለቀ ነው። መጀመሪያ ይፈርሳሉ የሚል መረጃ ተለቀቀ። ህዝቡ
ሲጯጯህ ደሞ “የለም አይፈርሱም” የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ብቻ ነው ለጊዜው በባለሙያዎች “በክብር” ከቦታው የሚነሳው። ተመልሶም
በባለሙያዎች በክብር የነበረበት ቦታ “በክብር” ይቀመጣል” የሚል መረጃ ተለቀቀ። የኋለኛውን መረጃ የምድር ባቡር "ባለስልጣን" (መሆኑ
ነው) የተናገረው ተባለ። የባለስልጣኑን ቃል አንደወረደ ማመን ከተሞክሮ
አንጻር ስህተት ሊሆን ይችላል። ማን ይሆን? ከየት ይሆን ብሎ -ለማወቅ
ያህል- መጠየቁ ዘመኑ ከፈጠረው ፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይሆን ካለው ነባራዊ የፓለቲካ የሃይል ሚዛን አና አሰላለፍ ነው መታየት ያለበት። በ “ልማት” ስም መታሰቢያ ሀውልቱን በባለሙያ “በክብር ከማስነሳት” ይልቅ
ሃውልቱ በማይነካበት ሁኔታ ባለሙያዎች መስራት የተፈለገውን ግንባታ አንዲሰሩ ስለመቻላቸው ወይንም ስላለመቻልቸው ስለመሞከሩ አና
ስላለመሞከሩ የምናውቀው ነገር የለም። የራሳችንን ግምት ግን አንወስዳለን -የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?” የሚል
ጥያቄ ግምት ውስጥ በማስገባት። የህወህትን ተፈጥሮ አና ባህሪ ግምት ውስጥ በማስገባት!
“ልማት”ን የአስከፊ ጥፋት መጠቅለያ ‘ዲስኩር’ እያደረጉ (አንደጣሊያኖቹ) ዝርዝር መረጃ ሲታፈን አና ነገሮች ከህዝብ ጋር
ያለምክክር ሲደረጉ ጥርጣሬ ፣ሁከት፣አና ተቃውሞ አንደሚነሳ መዘንጋት ምን ማለት አንደሆነ አይገባኝም። ዛሬ ወታደራዊ ጉልበት ስላለ
አና የፖለቲካ መዘውር በሃይል ስለተያዘ ብቻም ህዝቡ አሉኝ የሚላቸውን ከቅርስንትም ያለፈ ትርጉም አና ዋጋ ያላቸውን ታሪካዊም ፣መንፈሳዊም ማህበራዊም ሃብቶቹን አንደፈለጉ መነካካት አሁን ያለውን ትውልድ አና ህዝብ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና በማድማት የሚያልቅ
ጉዳይ አይደለም። የአለመረጋጋትን መሰረት አየጣሉ አንደመሄድም ነው። ተቃውሞው በሌላ መልኩ በሌላ ጊዜ ሲከሰት እንዳሁኑ
በመጯጯህ አና በህዘን የሚያልቅ ጉዳይ ላይሆን ይችላል። ከ”ብሶት ተወለድኩ” የሚል ቡድን ብሶት ሊወልድ የሚችለውን ነገር መዘንጋት
የለበትም። የትውልዱ ማህበራዊ አስተሳሰብ አና የሃገር ፍቅር ከጥቅም ውጪ ተደርጎአል፤ ስጋት የሚፈጥር ተቃውሞ ሊፈጠር
አይችልም( “መቶ አመት አንገዛለን” አንደሚባለው”) የሚመስለው አስተሳሰብ ምናልባት ከትውልዱም የበለጠ የሚናገረው ስለገዢው ቡድን
ትምክህትና አላዋቂነት ሊሆን ይችላል። በውጭም በውስጥም ያለውን የጥፋት ትስስር (nexus)ገብቶት አንደ አቡነ ጴጥሮስ ለሃገር
ለመሞት የተዘጋጀ ትውልድ ቢነሳስ?
ሕዝቡ
“አለማለሁ” የሚለውን ቡድን የሚጠራጠረው ባህሪውን ስለሚይውቅ ብቻ አይደለም። አንዳንድ “ልማት” የሚባሉ ፕሮጀክቶች በእርግጥም የልማት መሆናቸው አጠራጣሪ
ስለሆነም ነው። ገዢውም ፓርቲ ለማወናበድም ዝም ለማለትም የሚምክረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ስለሚያውቀው ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ከመሬት
ተነስቶ አይጠራጠርም፤ተሞክሮውን ተመርኩዞ አንጂ! የበፊት የበፊቱን
አንኳን ትተን የቅርቡን የጥርጣሬ ምንጭ ለማስታወስ ያህል - የአፍሪካ የውሃ ማማ ናት በምትባለው ፤ ሰፊ የቆዳ ስፋት አላቸው ከሚባሉ
የአፍሪካ ሃገሮች በምትመደበው ሃገራችን ውሃ አና መሬት የጠፋ ይመስል የስኳር ልማት ዋልድባ ላይ እተክላለሁ ተባለ። በጎን ደሞ ሃገሪቱ ያልተጠቀመችበት እጂግ በጣም ሰፊ መሬት አላት አየተባለ ለውጭ ዜጎች ንጥቂያ አንጂ ሽያጭ አይመስልም በሚባል ዋጋ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን አጥተናል። “ልማቱ” በትክክል የህወህት አጂ ብቻ ይሁን ወይንም የውጭ ሃይሎች አጂ ይኑርበት
እስካሁን ድረስ የገባኝ ነገር የለም። በትክክል የማውቀው ነገር ቢኖር ግን ዋልድባ ድረስ የተሄደው የኢትዮጵይውያንን እምነት ለመዝረፍም አንጂ ለልማት ጉዳይ ብቻ አንዳልሆነ ከማንም የሚያገናዝብ ኢትዮጵያዊ አንደማይሰወር ነው።
የአቡነ
ጴጥሮስ መታስቢያ በ “ክብር” የሚነሳበት ዓላማ በትክክል ልማት ከሆነ ሃውልቱ የሚያስተጋባው መልዕክት በራሱ ልማትም ለልማትም አስፈላጊ
የሆነ መሰረታዊ ነገር አንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል። ሃውልቱ ካረፈበት ኩርማን መሬት ይልቅ ሃውልቱ የሚያስተጋባው መልዕክት ዘላቂነት
ላለው የልማት ተሰሳሽነት አስፈላጊ ነው። ልማት ለማጣደፍ የሃገር
ፍቅር ያስፈልጋል። የዜጎችን ስብዕና አና ህሊና ማልማት ለልማት አንደ መሰረትም አንደ ቅድመ ሁኔታም መታየት አለበት። በስልጣን
መባለጉ፣ በሙስና መዝቀጡ፣ የሃገር ጥቅም አሳልፎ መስጠቱ ፣ ሀገርን ለበላየ ሰቦች ጥሎ ወደ ሰው ሃገር ተሰዶ በሰው ሃገር መደላደሉ
ሁሉ የሚመጡት ልማት ካላየው -ካልለማ- ስብዕና ነው። የራስን ዜጋ በሆነ ባልሆነው መጨፍጨፍ አና የመሳሰሉት ችግሮች መነሻቸው ያለማ
ህሊና አና የሃገር ፍቅር አለመኖር ነው። ሃገሩን የሚውድ ዜጋ ሃገሩን የሚያገለግልበት ዕድል ሲያገኝ ሃገሩን አይዘርፍም። አያዘርፍምም።
ህውልቱ የሚያነበው አና የሚያዳምጠው የመንግስት አክል ባይኖርም የሚናገረው አነዚህን የሃገር ጠንቅ የሆኑ ማህበራዊ አና ፓለቲካዊ ተውሳኮች
በመቃወም ነው፤ ለሃገር ጥቅም እስከሞት ድረስ በጽናት መቆም እንደሚያስፈልግ ነው። እንዴት “ባለ ራዕይ” የሚያመልክ ፓርቲ አና መንግስት ይሄን ማየት ተሳነው?
የአቡነ
ጴጥሮስ ሃውልት መታሰቢያ የጠንካራ ስብዕና ፣ የሃገር ፍቅር፣ የቁርጠኝነት
አና የነጻነት ተምሳሌትነትን ነው ጧትና ማታ የሚያስተጋባው። በአስቸጋሪ ዘመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ አውነትን አንቆ ለእውነት
ስለተሰዋ ክቡር ኢትዮጵያዊ ነው የሚናገረው። የአቡነ ጴጥሮስ የመንፈስ ጽናት ፤ መልዕክት አና መስዋዕትነት የትግል ስንቅ ሆኗቸው ፋሺስትነትን በጽናት ታግለው ስለሞቱም ኢትዮጵያውያን
የሚያስታውሰን መታሰቢያም ነው። ጎበዝ ኢትዮጵያ አኮ በፋሽስት ጦርነት አንድ ሚሊዮን የሚደርሱ ዜጎቾን አጥታለች። ስልሳ ሺ ታጋዮች ለትግራይ
ተሰውላት ተብሎ ትግራይ ላይ ሃውልት የሚሰራ ቡድን በኢትዮጵያውን ሃውልት ለምን ይቀለዳል?? በቅርቡ የተሰራው የአባ ጳውሎስ ሃውልትስ ሃይማኖታዊ አይደለም ይፍረስ ሲባል
አይፈርሲም ሲባል አልነበረ አንዴ? ምነው አቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ላይ ተነቃ?! የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ “ለህወሃት ምኑ ነው?”
ነዋ ነገሩ! የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ህወህት የተዋጋውን ኢትዮጵያዊነት ጧትና ማታ የሚያስተጋባ ነዝናዣቸው ነዋ!
የገዢው
ቡድን በተለይም የህወህት ጽንፈኛ ደጋፊዎች የሚመስሉኝን ሰዎች (አንዳንዶቹ
በብዕር ስም የሚጽፉ የአመራር አባላትም ይመስሉኛል) በዎብሳይቶች ላይ የሚጽፉአቸውን ጽሁፎች እከታተላለሁ። በዋነኛነት ከማነባቸው
ውስጥ የሳይበር ኢትዮጵያን የፓለቲካ አምድ( click here )አንዱ ነው። በኦፊሲየል ሲነገር የማይሰማውን የህወሃትን የፓለቲካ እሳቤ
-በተለይም ከትምክህትና የበላይነት ስለ ልቦና ግንባታ ጋር የተያያዙትን
ህሳቦች ቡዙ ሳይነካኩ (አንዳንዴ ምንም ሳይነካኩም) አንደወረደ የሚያቀርቡ ግለሰቦች አይጠፉም።
አንደወረዱ
የሚቀርቡትን ትቼ ትንሽ አየተነካኩ አንዳንዴ የስነ-ጽሁፍም ገጽታ እየተሰጣቸው የሚሰነዘሩ ሃሳቦችን ለአብነት አቀርባለሁ። አንደዚህ
አይነት ሃሳቦችን ያንጸባርቃሉ ያልኳቸውን ጽሁፎች ለማየት በቅንፍ ውስጥ ያለውን ማጣቀሻ ይጫኑት( click here)
። ሃሳቡ የህወሃት ለመሆኑ ሁነኛ ማስረጃ ይሆናል ብየ ከማስበው ነገር እንዲህ ያለውን ጽሁፍ ብዙ ጊዜ የሚያሞካሿቸው (በዚያው መድረክ
ላይ ማለቴ ነው) ህወሃት ባደረገው የትጥቅ ትግል ተሳትፈናል የሚሉ ስልጣን ከያዙ በኋላም ተምረው በዲፕሎማሲ ስራ ላይ (ካያያዛቸው ይመስላል) የተመደቡ ይገኙበታል። ጉዳዩን
አዚህ ያነሳሁብትም ምክንያት ህወሃት የሚከተላቸውን “የልማት” ይሁን ሌሎች የኢኮኖሚ ፓሊሲዎች ዓላማቸው ህወሃት የበላይነት ስነ-ልቦን መገንባት አና የበላይነቱን ያስጠበቀበትን
የስልጣን ተዋረድ ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችለው ከመሆን ውጪ ሌላ ሊሆኑ አንደማይችሉ ለማመላከት ነው። አንዲህ አይነቶቹን ፓሊሲውች
ህወሃት በቀጥታ የሚያስትላልፋቸው አይደሉም ማለት ህወህት የውሳኔው አድራጊ አና ፈጣሪ አይደለም ማለትም አይደለም (በነገራችን ላይ
የህወህት አመራር ‘ሜንተሮችን’ አንማን ነበሩ? ናቸው?)።
ቅጥ
ባጣ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ እና የነጻው ፕሬስ ላይ የዘመተው ህወሃት መራሽ መንግስት ከዚሁ ጎን ለጎን በስፋት የተያያዘው ነገር የህዝብን
ስነ-ልቦና የሚዘርፍበት ፣ ማህበራዊ አስተሳሰባችን ርባና ቢስ የሚያደርግበት ዘመቻ ነው (ለአስተሳሰቦቹ ሃውልት የተሰራላቸው አንገበዋቸው
የኖሩ አና አንግበዋቸው የሞቱ ኢትዮጵያውያንን በመዘከር አንደሆነ አንዳይረሳ)። ማህብራዊ ስነ-ልቦና የሚዘረፍብት ምክንያት በዘራፊነት
አና በግፍ ላይ የተመሰረተ የስልጣን ተዋረድ የማይቀርለትን ተቃውሞ በመገንዘብ የተቃውሞውን ምንጭ አና ለስልጣን የበላይነቱ ችግር ይፈጥሩብኛል የሚላቸውን
ጉዳዮች ከምንጫቸው ለማድረቅ የሚደረግ ጥረት አካል ሊሆን አንደሚችል አገምታለሁ።
የመሃል
ሃገሩን ታሪካዊውን - ዓለም ጭምር ያወቀውን የነጻነት ትግል የሚያስታውሱ መታሰቢያዎችን በ “ልማት” ሰበብ “መልስን በክብር አንደነበረ አናደርገዋለን” አየተባለ እየሰወርን በነበረው
የርስ በርስ ጦርነት “ተሰው” የሚባሉ የህወሃትን ታጋዮች የሚያስታውስ
መታሰቢያ ትግራይ ላይ ለቱሪስት ማስጎብኘት አና “በክልሉ” የሚያድጉ
ህጻናትን ጭምር በዚህ መልክ ማነጹ አሁንም ትምክህት ክተሞላበት የፓለቲካ ስራ ውጪ በዋነኛነት ከ”ልማት”ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ያስቸግራል። የሆነስ ሆነና ትግራይ ላይ ያለው ሃውልት ስለ ርስበርስ ጦርነቱ ሙሉ ገጽታ ይሰጣል?
ለትግራይ ህጻናት ከ”ትግራዋይነት” እኩል ኢትዮጵያዊነት ስሜት አንዲፈጥሩ ያግዛል? የመሃል ሃገሩስ ታዳጊ ወጣት በራሱ አንኳን አነሳሺነት
(መንግስት አንደማያደርገው አርግጠኛ ስለሆነኩ ነው) የሃገሩን ታሪክ አንዲጠይቅ የሚያስታውሰው መታሰቢያ አንዳያይ የሚደረግበት ምክንያት
ስልታዊ የስነ ልቦና ዘረፋ ካልሆነ በስተቀር ምን ሊሆን ይችላል??
ህወህት
የአርበኛውን የአቡነ ጴጥሮስን መታሰቢያ ህውልት አነሳለሁ በሚልበት ሰዓት ጣሊያኖቹ በኢትዮጵያ ብዙ እልቂት ላደረሰው የጦር መኮንናቸው
(ግራዚያኒ) የመታሰቢያ ሃውልት ሊያቆሙ ነው። የህወህት መራሹ መንግስት ድርጊት ሳይታሰብ በአጋጣሚ የተደረገ ነው ? ምናልባትም
የአማካሪ ሃሳብም ያለበት ድርጊት ሳይሆንአይቀርም(ከላይ nexus
ያልኩበትም የጥርጣሬ መሰረት ይሄው ነው)። የህዝብ ስነ-ልቦና ዘረፋ የመጨረሻው ደረጃ መሆኑ ነው። ይሄ ጉዳይ በቸልታ የታለፈ አንደሆነ
አንድ ሰው ገስግሶ ዓይናችንን ሊያጠፋው ወደዓይናችን ሲጠጋ አይቶ አንዳላይ አንደመሆን ነው። በድርጊቱ ቀጥሎበት ዓይናችን ከተዛቀ የሚደርሰው ነገር ከአካል
ጉዳትኝነት የከፋ ይሆናል።
የአቡነ
ጴጥሮስ ሃውልት ሃይማኖታዊ የሆነ አና የነፍጠኞች ነው ተብሎ የሚታሰበው(
በህወሃቶች ዘንድ) የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሃይማኖት ቅርስ አይደለም። ክርስቲያን ላልሆነውም ኢትዮጵያዊም ቅርስ ነው። ታሪኩ የሃይማኖት
ሳይሆን የነጻነት ትግል ታሪክ ነው። ስለሆነም አሁን ባለው ነብራዊ
ሁኔታ በተሻለ ሁኔታ ተደራጂተው እየታገሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም አንደ ኢትዮጵያዊነታቸው በጽናት ሊቃወሙት አና ሊያወግዙት የሚገባ ድርጊት ነው።
የነጻነትን
ትርጉም አየጠየቀ “ሊበራሊዝምን” ከእምነት በማይተናነስ መልኩ ተቀብሎ ስለ ውጭ ሰዎች የነጻነት እሳቤ አና ትግል የሚነግሩን የፖለቲካ ሰዎች (“አደፍርሶች”)
፤ የአቡነ ጴጥሮስ አይነት ክቡር ዜጋ ስለ ነጻነት በተግባር የከፈለውን መስዋዕትነት የመነጋገሪያ ርዕስ አድርገው
ቢያወሩን ኖሮ ዛሬ አንዲህ አይነት ነገር ሲሰማ የሚሰማው ቁጣ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል በሆነ። የነ አባ ጳውሎስ ሃውልት
ተጎልቶ የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት በ”ክብር ከቦታው ይነሳል” አየተባለ ሲላገጥ ከመስማት የበለጠ ውርደት ለዚህ ትውልድ መቸም አይመጣም።