Saturday, April 4, 2009

የፍትሕ አርበኛ

የፍትህ ተሟጋች አርበኛ
ተገኝታ ቆፍጣና እንስት ዳኛ
ልጓሙን አጥብቃ ይዛ
በፍርሀት በብረት; ሳትገዛ
አላስነካም ብላ ፍትህን በዋዛ
በነጻነት ስለፍትህ ስትበይን
ስለእውነት ሳታጋንን
ሆኖባቸው የራስ ምታት
ለሚገዙት ""በእንተ ሰማዕታት""...
በዱላ; በብረት
የጎሪጥ ሲያዩአት
ገባትና የፍትህ መሰረት መናጋት;
በቆይታ መሰረት ልታጸና; ልታደላድል
በሴት አቅሟ ገባች ወደ ትግል::

ጥሊያንን እንደተፋለሙት የእናት አርበኞች
ወኔዋ ሳይከዳት; ሳትል ፍንክች
ልክ ልክ ስለተናገረች
በውሸት እና በብረት እንደገና ታሰረች
እንደምን የታደለች!!
ለእምነቷ -በእምነት የጸናች
ስንቱንስ እንስት ለትግል አነሳሳች!!
እኔ አልኩአት የሴት ወንድ-የእውነት አገልጋይ
ይጠብቅሽ ኤልሻዳይ!


ለብርቱካን ሚዴቅሳ

ድሜጥሮስ ብርቁ
መጋቢት 23, 2001 ዓ. ም
ቶሮንቶ

No comments:

Post a Comment

Blog Archive