እንደ ባሊና ኳስ ልብ እየነጠረ
ከሰው አልመከረ ;
እግር አልተነሳ ; ወሰን ተሻገረ ::
""ምን ለመሆን ነው
የሰው ነገር ...የሰው
ሲሆን እያወከው ?! ""
ብየ ብጠይቀው
ዝም አይነቅ ዝም !
መንጠሩን ግን አላቆመም ::
ነጥሮ ነጥሮ እንደገና መሬት ደረሰ
መሬቱ ላይ መሬት ሆኖ ቀረ ዝምታ ነገሰ
ትንሽ ቆይቶ ደሞ ተላወሰ
የታየውን ....ተነፈሰ
"" እንደኖርኩት ...እንደማውቀው
ልብ በዋዛ አይመታም
ወደላይ አይጉንም
መሬት ላይ አይነጥርም ::
እንዲህ የሚጉነው
እንዲህ የሚነጥረው
የመታው ቢለይ ነው !""
ሲል ቢነግረኝ
የልብ ንጥረቱ ና ስደቱ ገባኝ ::
ከስደትም የተሰደደ ልብን ለሚያውቁ
የካቲት 27, 2003,ቶሮንቶ
No comments:
Post a Comment