ተሸክሞ የብሶት ቁልል
ችጋርና ርሀብ ቤቱን ሰርቶ
ቁራሽ ምኞት ሆኖ አርፎ
በፈረቃ እየተበላ ስንቱ
በየቤቱ ራሱን ስቶ
ቁራሽ ፍለጋ ተከልቶ
ቀየውን መንደሩን ትቶ;
ከሁለት ያጣ እንዲሉ
ቁራሹም ጠፍቶ ላመሉ
ቀየውንም ቁራሹንም እየተራበ
ጉደኛ አሳዳሪ...
""ዕድገት"" አለ እያለ ከበሮ ደረበ::
"" ህዳሔ አለ ...ዕድገት አለ
አስፋልት ተነጠፈ
ጥርጊያ መንገድ ተደለደለ
ለዕድገት ተብሎ..
ለአረቡ; ለቻይናው; ለህንዱ መሬት ታደለ
ዕድገት አለ:: ""
እንዲህ አይነት ፌዝ እየሰማ
አበሽ ልቡ እየደማ
በረሀብ የሚፈጀው
ረሀብ እና ባርነት ያደረጀ 'ሚታገሰው
እስከመቼ ነው?!
የ""አትንኩኝ"" ባይነት መንፈስ
ነጻነት ባበቀለበት ምድር
ዛሬ "አትንኩኙን" ማን ቀጠፈው
ማን ቀላቀለበት ከአፈር::
ምነው አበሽ ዝምታ አበዛ አንገቱን ሰበረ
"'ከመናገር ደጃዝማቺነት ይቀራል"" ተረስቶ
ስለምን ለዘራፊ አሳዳሪ አቀረቀረ??
ኧረ እንደልማድህ አበሽ
ኑር እንደ አባት አደሩ
ችጋር; ባርነት ለሚደግስ
እስከመቼ እሺሩሩ??
ጥር 2003 ቶሮንቶ
No comments:
Post a Comment