አንዳንዴ
ያለፍንበትን ዘመን
የኁአልዮሽ ስናጠነጥን
ከመስታወት ፊት ለፊት ቆመን
ትክለ ሰውነታችን እንደሚታየን
የወፈርነው; የከሳነው
ያማረብን ወይንም የጠቆርነው
ሁሉንም በውል እንደምናየው
ያለፈ ዘመንም ይሆናል መስታወት
ስብዕናችንን እንድናይበት
ዛሬም ሲደነግዝ-አለው መብራትነት::
የዘመን ዕይታ እንደውም ይበልጣል
ገጽን እያሳየ መች ይሽነግላል
ሕይወትን መዝኖ ልክን ይናገራል::
ግንቦት 14,2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ
No comments:
Post a Comment