ሕይወት ገና በተሲዐት በቁም አንቀላፍታ
"'በጊዜ "" ተረታ ""ለጊዜ "' እጂ ሰጥታ
ዛቢያዋን - መሽከርከሪያ ምህዋሯን ስታ
ስታዘግም በሰው ምህዋር ""በጊዜ "" ባለፋንታ
እንበለ ሀገር ; በሰው ቀየ -በሰው ቦታ ;
""ጊዜ "" ግን ይሮጣል
የልቡን ይሰራል
ሕይወትን ገትሮ እንደጉድ ይበራል
ዘመን ይቆልላል ::
እንዲያ እየከነፈ ;
አንዳንዱን ያነሳል
አንዳንዱን ይጥላል
አንዳንዱን ይክባል
አንዳንዱን ይንዳል ::
ሕይወት ብርቱ ! እንደምንም ብላ ምህዋሯን ብታገኝ
""ጊዜ "" እንደሁ አይተዋት ; መሽከርከሪያ ጊዜ እንደልብ አይገኝ ::
ሚያዚያ 25, 2001 ዓ .ም
ቶሮንቶ
(ጊዜ ለባከነባቸው እና ለተፈናቀሉ )
No comments:
Post a Comment