ሰው መሳይ በሸንጎ
ለቀማኛ ወሮበላ ያደረ
እደሚለብሰው ካባ ህሊናውን ያጠቆረ
እውነት ዘብጥያ ሲጣል አብሮ በመንፈስም ያሰረ
ሱፉን ከካባ አስማምቶ
ከሱፍ መልስ ያለውን
ስብዕናውን አጨቅይቶ
ህሊናውን በሳስቶ; አድርጎ ቡትቶ
የሚበይንበት ወንበር ላይ ሲያዪት ተጎልቶ
ሰው መሳይ በሸንጎ
ፍርድ አዋቂ;አሳቢ በጎ
እሱ የሚቀመጥበትን ወንበር ሲያሽከረክር
ከላይ ግን ሲያሽከረክሩት
... እንደፈለጉት ሆኖ እንዲያድር
ሲያስብሉት ጥቁሩን ነጭ;ነጩን ጥቁር
የፍትህ ቅጣንባር ጠፍቶበት ሲደናገር
ምነው ራሱን እንኩአን ቢሽር
ውስጡን ኮስኩሶት ከሌባ;ለሌባ ማደር!!
ግን እሱም የሱ አይደል; አለበት ወታደር::
ለሚመለከተው ሁሉ,
ድሜጥሮስ ብርቁ
መጋቢት 24, 2001 ዓ.ም
ቶሮንቶ
No comments:
Post a Comment