Friday, February 22, 2013

የመናገር ነጻነት ዘመቻው ለህወሃት መራሹ መንግስት ምኑ ነው?

ሰሞኑን የዞን 9 አባላት የብሎጋቸውን በኢትዮጵያ መከልከል ተከትሎ ከክፈቱልን ያለፈ ፤ መሰረታዊ ሊባል የሚችል ዘመቻ ማህበራዊ ድህረ ገጾች ጀምረዋል፡፡ በዚህ ደረጃ ምላሽ መስጠቱ እና መጠቀም የሚቻለውን መድረክ ተጠቅሞ የችግሩን ጥልቀ ለማመላከት መሞከር ጥሩ ነው። ነገር ግን የመጻፍ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እየተጠየቁ ያሉትን ቡድኖች('ፎርማሊ' ካወራን መንግስት ናቸው -ያውም ፈላጭ ቆራጪ) ባህሪ  ግምት ውስጥ በማስገባት ዘመቻው እነዚሁ ቡድኖች አምነትውበት በማናለብኝነት የወሰዱትን ርምጃ ከማስቀየር ይልቅ በስነ ልቦናቸው ለተቀረጸው የትምክህት እና የበላይነት አስተሳሰብ ሃሴት የሚሰጥ ሆኖ ስለተሰማኝ ለነሱ ትክህት ሃሴት ላለማዋጣት ስል በዚህ በዘመቻ አልተሳተፉኩም።

እንኳንስ የመናገር ነጻነት አይደለም ለእምነት ነጻነት ጀርባቸውን ሰጥተው የክስርቲያኑን የእምነት ተቋማት በቁጥጥር ስር አድርገው ሙስሊሙንም እንዲሁ እምነቱን ለመንጠቅ ቤት ለቤት ጭምር አሰሳ የገቡ ሰዎች ናቸው፡፡ የመናገር እና ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት ጋር በእጂጉ የተቆራኘ  የጋዜጣ ህትመት ማስቆም ሳያንሳቸው ዜጎችን --ያውም ኩሩ ሀገር ወዳድ ዜጎችን በሽብረተኛነት በመክሰስ ፣ብዙ እንግልት በማድረስ እና ክብራቸውን ጭምር ለማዋረድ በመሞከር ሌሌች ዜጎች የዜግነት ክብር እና ነጻነት  ጥያቄ ቅብጠት እና በህይወት መቀለድ እንዲመስላቸው በማድረግ የባርነትን እስተሳሰብ በደህንነት ተቋማት ፣በህግ ተቋማት እንዲሁም የማህበራዊ ድንዝዝነት በሚያስፋፉ ሌሎች ልማዶች የሚስፋፉበትን መንገድ በስውርም በግልጽም በማበረታታት  የባርነትን መስረት ለማጽናት ሌት ከቀን የሚሰሩ ለመሆናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሁኔታ ያለ ብዙ ምርምር ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

የህገ-መንግስት ጉዳይ እና የዜጎች መብት ፋይዳ ሳይገባቸው ቀርቶ ነው እንዳይባል፤ ትግል ጀመርንም ጨረስንም የሚሉባቸውን ቀናቶች በብሔራዊ ደረጃ ጭምር እንዲከበርላቸው የሚፈልጉ ናቸው። እንዲያውም ያለባቸውን የስነ-ልቦና ችግር ከሚያመላክቱ ነገሮች  እንደኛው ይሄው ነው። ህወሃት ስልሳ ሺህ  ሰው ሰዋበት የሚሉትን በዓላቸውን የሚያዳንቁትን እና ሰው እንዲያዳንቅላቸው የሚፈልጉትን ያህል ለኢትዮጵያ ነጻነት ከጎጠኝነት በጸዳ በንጹህ የሃገር ፍቅር ስሜት የወደቁ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያኖች ጉዳይ እንዲነሳም እንዲታወስም እይፈልጉም። ታሪኩ ሲነገር ያሳንሳቸዋላ!

የሃሳብ ነጻነት ወደሚያፈኑበት ጉዳይ ስመለስ -የሚያፍኑበት እና ሃሳብ እንደጦር የሚፈሩበት ጉዳይ ምንድን ነው የተባለ እንደሆነ መሳሪያ እንቆ የተኮፈሰ የፓለቲካ ስብዕናቸውን የሚያኮስስ ስለሚመስላቸው። እደፊኛ የሚነፉትን ፕሮፓጋንዳ የሚያስተነፍስ ስለሚመስላቸው። የሃሳብ ልውውጥ ላይ ያለ ስለት ስለሚያስፈራቸው። አንግበው ለተነሱት የትምክህት እና የበላይነት ግንባታ ዓላማ እንቅፋት እንደሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ይመስለኛል። የእምነት ነጻነትም እስከመንጠቅ የሄዱበት ምክንያት ከፍራቻ ውጭ ሌላ ሊሆን አይችልም። የፍርሃት ገጹ ይለያያል።  የህወሃት መራሹ መንግስት ፍርሃት በአንድ በኩል በጥጋብ እና በማናለብኝነት የተከናነበ ይመስላል በሌላ በኩል ደሞ በልማት ዲስኩር ተከልሎ ከዲስኩሩ በስከጀርባ በምናቡ የሚስላቸውን "ጸረ-ልማት ሃይሎች" (ኢትዮጵያውያኖች እኮ ናቸው የኢትዮጵያ ልማት ጠላቶች?) እንደምክንያት እየተጠቀመ የአፈና የሚጧጡፍበት የሞራል ፈቃድ አብረውት ክሚሰሩት "እህት ድርጂቶች"  ይወስዳል፡፡ በህወሃት "የማይበገር ጀግንነት" ውስጥ ያለው እውነታ ('ሪያሊቲ') ሃሳብን በነጻነት የመግልጽ መብትን እስከመፍራት የሚያደርስ ፍርሃት ነው። የደህንነት ተቋማቱም እወቃቀር የሚሰማቸውን የፍርሃት ደረጃ ግምት ውስጥ ያስገባ ይመስላል።

ስለ ህወሃቶች እና ስለገነቡት የማፈኛ ተቋም የራሴም የሰዎችም ተሞክሮ አለኝ። ገና በልጂነት ባደኩባት የደሴ  ከተማ ፓሊስ(ህወሃት ለአፈና ተግባር ካሰለጠናቸው ውስጥ ነበር)   አንዱን ያለ እግባብ እያንገላታ ለማሰር ዱብ እንቅ ሲል (እንደዛ ይደረግ የነበረው ደሞ ለሃገሩ በብሄራዊ ውትድርና ዘምቶ የመጣ ዜጋ ነው-የገባው የሚመስለው የፖለቲካ ሁኔታ እንገቱን ባያስደፋው ኖሮ የዛን ለፍዳዳ ፖሊስ ጥርሱን የሚያራግፍ ጎበዝ ነበር። አውቀዋለሁ ) ነገሩ ከንክኖኝ ከፖሊሱ ጋር "የምን እደረገህ" ያደረገውም ነገር ካለ በስነ-ስርዐት ውሰደው የሚል ሙግት ውስጥ ገባሁ። ከዚያ በኋላ ፖሊሱ ልጁን ትቶ ወደኔ ዞረ። ዱላም ጀመረ። ታሳሪው እኔ ሆንኩ፡፡ እና ሂድ እልሄድም ውዝግብ ተጀመረ።  ጓደኛየ ታደሰ ባየ( ፌስ ቡክ ላይ አለ) በዛ በዝናብ ተንበርክኮ ሁሉ ለመነው ፓሊሱን፡፡ እኔ ደሞ እንኳን ልለምነው እንዴት ድንጋይ እንደሆነ በተጋጋሚ እነግረዋለሁ። የመምታት አቅሙን ተጠቅሞ ያ ሁሉ የፖሊስ ዱላ ወረደብኝ። በመጨረሻ ላለመታሰር ጨለማውን ምክንያት እድርገን ሁለታችንም አመለጥነው። የተመታሁት ብዙ እንደነበረ የገባኝ ግን በነገታው  መሄድ እቅቶኝ ቀኑን አልጋ ላይ ሳሳልፍ ነው።  ያኔ ተናድጄ ስለነበር ምንም አልተሰማኝም።   ሶስት ቀን ያህል ሳያስነክሰኝ አልቀረም።

ኮተቤ እያለሁ ደሞ ሮብ  ሮብ መብራት ይጠፋ ነበር። በዚያ ምክንያት ረቡዕ ማታ አካባቢ ጥናት የለም ። ወክ ነው የምናደርገው። ወደ ገደራ እየሄድን ስናወራ የነበረውን ከኋላ ይሰማ የነበረ አስቁሞን መታወቂያችንን ከጠየቀ በኋላ እዚያው እካባቢ ወደ ነበረ ፓሊስ ጣቢያ ተወስደን ተመዝግበን የሚጠይቁትን ጠይቀው ተመልሰናል።  ሌላ ጊዜ እንዲሁ አራት ኪሎ ላይ የከተማ አውቶብስ ይዞ የነበረ የትግሪኛ ተናጋሪ ሾፌር  በራሱ ስህተት እና ትክምህት ምክንያት ተሳፋሪውን ከአራት ኪሎ ይዞ ሚኒሊክ እካባቢ ወደነበረው ፓሊስ ጣቢያ ወሰደን። በትግሪኛ አወራ ከሰዎቹ ጋር። እኛ "ጥፋተኞች ሆንን።" የተማሪዎች ዲን ነው ጣልቃ ገብቶ ነገሩ ያለቀው።

የሌሎችን ተሞክሮ በሚመለከት እዚያው ያደኩባት ደሴ ከተማ ላይ በጠራራ ጸሃይ አፉን በደንብ ያልፈታ የህወሃት ታጣቂ እንድ ባዶ እጁን የነበረ ወጣት አሯሩጦ ከደረሰበት በኋላ ሰው እየተጯጯኽ የክላሹን አፈሙዝ ደረቱ  ላይ አድርጎ ተኩሶ ከገደለው በኋላ ክላሹን እንቆ እንደያዘ  ሲሄድ ያስቆመው ፓሊስ አልነበረም። ሌሎች ታጣቂዎችም ያሉት ነገር የለም። (በነገራችን ላይ ያኔ እስከማውቀው ድረስ የልጁ ገዳይ ለፍርድ እልቀረበም)

እንደዛ እይነቱ የህወሃት ጭራቅነት በርሃ ባልነበሩት ዘመድ እዝማዶቻቸው ላይ ተጋብቶ "ምክንያታዊ" በሚመስል ሁኔታ  ስለፍትህ በሚጮሁ ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ቅጥ ያጣ ንቀት ማየት እሁን የተጀመረው እይነት ዘመቻ በበታችነት ስሜት በሚናጥ ስብናቸው እና እስተሳሰባችው ላይ የበላይነት እና የገዠነት ካባ ከሚደርብላቸው በስተቀር ትርጉም ያለው ጩኽት ይሆናል የሚል እምነት የለኝም። የማስጮህ ስሜት እንዲሰማቸው አልፈልግም። ዛሬ ፌስ ብክ ላይ እንዲህ ያለ ዘመቻ ባለበት ሰዐት እዚሁ ፌስ ቡክ ላይ እስክንድር ነጋን በሚመለክት የነዚሁ የህወሃት ወገን የሚመስሉ ሰዎች ያደረጉትን ምልልስ ለአብነት እንዲሆን ያህል ከ'ሆም ፔጂ ላይ ስክሪን ሾት' ወስጃለሁ፡፡

ከዚያ ውጭ የህግ ስርኦት ያለበት ሃገር ቢሆን ኖሮ እንደ ዳንኤል ብርሃነ ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች ሃገር ውስጥ ያለው የሃሳብ ሙግት በጸጥታ ሃይል እና በ"ፍትህ አካላት" እየታፈነ ባዶ ሆኖ ሙግታቸውን እና የሃሳብ ክርክራቸውን ከውጭ ሃገራት ሰዎች ጋር ሲያደርጉ ማየት የህወሃት ደጋፊዎች እና ዘመዶች ባይሆኑ ኖሮ ሊያስገርም ይችል ነበር።  ከታች በሊንክ ባስቀመጥኩት የዳንኤል ጽሁፍ የሂውማን ራይቱ ቤን ራውለንስ የእንግሊዝ መንግስት የዕርዳታ እሰጣጥ የሚተች የመጽሃፍ ሪቪው  አወጣ ብሎ  የእንግሊዝ መንግስት ትችት ሳይሆን ምስጋና ነው የሚገባው የሚል ጽህፍ አውጥቶ ብሎጉም ላይ ጭምር ለጥፎታል። የጽሁፉ ዓላማ ምን ነበር የሚለው ሌላ ጥያቄ ሆኖ መነሳት ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ እንደ ዳንኤል ያለው የህወሃት ፖለቲካ ደጋፊ ስለሆነ ብቻ ሃገር ቤት በሚታተሙም ራሱ በፈጠረውም ብሎግ ላይ የመጻፍ ነጻነት ሲሰጠው ሌሎች ዜጎች (ለምሳሌ የዞን ዘጠኝ ብሎገር አባላት) የሚታፈኑበት ምክንያት ከላይ የገለጽኩት ነው። እፈናውን ተቃውሞ የሚደረገውን ተቃውሞ ያልተቀላቀልኩበት ምክንያት የሚጨምርላቸውን -ተዋጋን እያሉ ለሚያወሩት ብቻ ሳይሆን ያኔ ልጆች ለነበሩት እና የደም ትስስር በሚመስል ምክንያት ብቻ እፈናን በምክንያታዊነት ለማስተባባል እና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ለሚሞክሩትም ጭምር- ለትምክህታቸው  የሚጨምረላቸውን ሃሴት ላለመስጠት ነው።  የዳኤል ፓስት

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አምባገነናዊነት ሌላ ዓለም ከሚስተዋለው በመሰረታዊነት የሚለይ እንደሆነ እምኖ ተቀብሎ የሚደረገው ተቃውሞ የህወህትን እምባገነናዊ ባህሪ ግምት ውስጥ ያስገባ እና ህወሃቶች በመንፈስም በፖለቲካም የማይጠቀሙበት እና ትምክህት የማይጨምርላቸው መሆነ አለበት ብየ ስለማምን ነው፡፡  በሌላ አንጻር ደሞ የሚደረገው ዘመቻ መሬት ላይ ያለ እና ለህዝቡ ስነ-ልቦና እና አስተሳሰብ ቅርበት ያለው ፣ በቀላሉ የሚገባ ቢሆንም ጥሩ ነው። ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ነው በፌስ ቡክ እና ትዊተር ላይ ያለው? ፌስ ቡክ ላይ ካለውስ የህወሃት ደጋፊ ከሆነው ውጭ ስለ ህወሃት መራሹ መንግስት አፈና እና ቅጥ ያጣ እምባገነናዊነት የማያውቀም ምን ያህሉ ነው? ለ "ዓለማቀፉ" ማህበረሰብ ነው እንዳይባል ለዚሁ አፈና ለሚያደርሰው መንግስት ትብብር እና ርዳታ የሚሰጡት እነዚሁ ወገኖች ናቸው። ዳንኤል የእንግሊዝን የእርዳታ አሰጣጥ በመደገፍ የእንግሊዝን መንግስት የሚከላከል ጽሁፍ መጻፍ ደረጃ ላይ የደረሰበት ''የዲፕሎማሲ" ልምምድ ሳይሆን የፖለቲካ ትስስርንም ጭምር የሚያመላክት ይመስለኛል። ለሃወሃት የጥጸጥታ ሃይሎች ስልጠና እና ሎጂስቲክ የሚያቀርበው ማን ነው? ብዙዎቹ የህወሃት ፖሊሲዎች በርግጥ ከህወህት ብቻ የመነጩ ናቸው? "የመለስ" ራዕይን ጨምሮ?

Monday, February 18, 2013

Revere not the wicked, revere the virtuous!


Sometime in August, I shared a picture of a homeless man, which I took with my cellphone, here on facebook. What was very captivating about it was the sense of ease I read on his face. For those who bought into the idea of "loser" and "successful people", which appears to be a 'dominant world view' as things stand now in the prospered and not prospered part of the world alike, the homeless guy that captured my imagination is kind of "looser." Yet, the ease I read on his face appeared to me very mysterious!

This very story caused back and forth conversation (inbox) with a friend of mine of European background with whom I have exchanged views on different topics of political and philosophical nature.

His position about the picture I shared reads "...Freedom looks like that..."(imagine a homeless man) Well, it was thought provoking , and I didn't yet finish the writing I started back then and I have no idea as to when I will go back to the business of struggling with that idea and finish the writing.

The picture (and story) I am sharing below took me back to that experience of struggling with idea of "freedom" and the qualities of human nature essential for 'freedom.' The thing is, in my view, people who value honesty and their conscience most are likely to end up being "unsuccessful" in the 'conventional' sense of the term "success." Honesty has very little or no material reward.

What is even sad is that people who stick to values of being human - those who are morally upright, those who value their conscience most and care less for material- could even be equated with idiocy. Caring for conscience and honesty sometimes feel like, to me, spiritual ideals. As a Christian, what Jesus went through reminds me that. My readings in other religious books affirms this to me.

For me this man is brave! The reason I am saying so is that this man could have escaped what looks like destitution If he was willing to trade off his conscious for comfort. Besides naivety, my view may sound a little speculative but it is grounded on my observation of what could be said quite considerable cases. Many opt for leading a life of slavery (no matter how fancy it looks like and no matter how the state of slavery is given a different comforting image and name) due to fear of "destitution" or due to love of "comfort."

Oddly enough, people tend to revere those who trade off freedom and their conscience for slavery, those with a remarkable pretentious quality, and those who afford a fancy lifestyle with a sordid gain. On the contrary, those who bravely live for and with their conscience are despised simply because honesty and conscience do not garner material richness. Implication of revering the pretentious, the morally corrupt and wicked ones may mean triumph of evil over good. Of course, this will have a negative implication for fate of our country.

Seen from the trajectory of Ethiopian politics, this is how TPLF managed to dominate Ethiopian politics and economy! 'Rewarding' the morally corrupt ones (and by creating them at a level needed to sustain a regime of moral corruption), and punishing the wise and morally upright ones. The question is why is it that many appear to be willing to buy a morally corrupted world view and of life as something very desirable? This is in total , I mean total contradiction to the world view of those Ethiopians who managed to maintain a very sensible notion of freedom and a free country.

The story below could normally make people feel pity. It didn't make me feel so. I rather venerated his bravery and wished just a few thousands of us were brave enough like him. We could have written not a history of theft and aspiration of ethnic supremacy but an incredible story of struggle for freedom and free our country from moral corruption. Yes, I want to be part of helping this guy but I am not doing it in a sense of pity! If we can read his life, it is an incredible story of courage, which is very essential for those who think in terms of struggling for freedom and saving Ethiopia and Ethiopians! It does not narrate a story of defeatism. It narrates determination: It is a reminder of Ethiopian story! Rebirth of Ethiopian patriotism and consequent project of saving Ethiopia depends, I think to a great extent, on the type of world view we buy. Moral sanity versus moral corruption, and if the former, how determined are we to pursue it? Sensible notion of 'freedom' streams from moral virtue. Partly, if not all about, it's about philosophy(and purpose ) of life. Do we dare to bargain 'freedom' for "success?"  This is the story behind great personalities.

        The material below is cited from facebook page of Yessuf Abdo


እነዛ ለአምባገነኑ እና ሙሰኛው መለስ ዜናዊ የቀብር ማስፈጸሚያ ገንዘብ ያሰባሰቡት የ ሃገራችን ጋዜጠኞ እና አርቲስቶች ለዚህ ጥያቄ መልስ ይስጡ !!
              

የጋዜጠኛና ደራሲው አሳዛኝ ሕይወት
እውቁ ጋዜጠኛና ደራሲ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰ፥ ያገለገላት አገሩ፣ የተገለገሉበት <የዛሬ ታዋቂ> አርቲስቶችና የፊልም ባለሙያዎች …ብቻ ሁሉም ፊት ነስተውታል። አንገቴን አቀርቅሬ ከልብ ከማለቅስላቸው ውድ የኢትዮጲያ ልጆች አንዱ ሰሎሞን ነው!! በእርሱ ድንቅ የጥበብ ጭንቅላት በጣም በርካቶች የናጠጡ ሃብታም ሆነዋል። በጣም በርካታ የጋዜጣና የቴሌቪዥን ድራማዎች ሰርቶዋል። ዛሬ ግን የጎዳና ተዳዳሪ ነው፤ ይህን አስከፊ ሕይወት ከተላመደው አምስት አመት ገደማ ሆነው። …ስለዚህ ታላቅ ሰው የቱን ተናግሬ የቱን እንደምተው ይቸግረኛል!.. በ ፊደል ስማቸው የሚጀምር የአለም መሪዎችን በተመለከተ ከ17ዓመት በፊት የፃፈውና ፥ « ሙባረክ፣ መለስ፣ መንግስቱ፣ ሙጋቤ፣ ሙአመድ ጋዳፊ፣ ሚሎሶቪች፣ …ወዘተ» ጠቅሶ ስለ ባህሪያቸውና ስለአቋማቸው (ተመሳሳይነት) ሰፊ ትንታኔ የሰጠበትና አስደናቂ ፀሃፊነቱን (ነብይ ጭምር) የተባለበት አይረሳም። በተለይ ስለ መለስ የፃፈው ውሎ አድሮ ብዙ መዘዝ አስከትለውበታል። እንደትንቢት የገለፀው ግን አንድም መሬት ጠብ ያለ ነገር የለም። ሰሎሞን፥ በዚህ ህይወትም ውስጥ ሆኖ ይህን ይላል፥ « የሰው ልጆች የስፕሪት ሃይልን.. መከራ አያውቁትም!» ….
ለድንቅ ደራሲው ፈጥነን የምንደርስ ስንቶች ነን?...ተግባራዊ መልስ እንስጥ!

Wednesday, February 6, 2013

"ጂሀዳዊ ሀረካት "

ጂሀዳዊ ሀረካት ከሚለው ወንጀል ነክ ፓለቲካዊ ተውኔት ጀርባ በዋነኛነት ልናይ ይገባል ብየ የማስበው የህወሀትን ስነ-ልቦና ነው :: ከዚያ ቅጥ ካጣ የትምክህት ስነ -ልቦና ጀርባ ደሞ የህወሀት ደጋፊዎችን ስነ -ልቦና እና ከስርአቱ ጋር አለን የሚሉትን "የደም " ትስስር ማሰብ ያስፈልጋል :: ጀሀዳዊ ሀረካት ብለው ባቀናበሩት ህወህት -ወለዳዊ (ልብ ወለድ እንዳልለው የጥላቻ እና የትምክህት ፓለቲካ ወለድነቱ ያደላል ) የተፈጠረው ቁጣ ባብዛኛው የመጣው (እስካሁን እንዳየሁት ) የህወሀት ደጋፊ ካልሆኑ ኢትዮጵያውያን ነው ::

የህወህት ደጋፊዎች ወይንም "የደም ' ትስስር ያላቸው ከሌላው ኢትዮጵያዊ የከፋ እፈና ስላለባቸው ነው እንዳይባል ከዚህ በፊት በተለያዮ ጥቅማችን ወይ መብታችን ተነክቶአል በሚሉብት ጉዳይ መቀሌ ላይ ሰልፍ ሲወጡ በኢትዮጵያ ቴሌቭዢን እንደታየ የሚዘነጋ እይደለም :: ስለዚህ ዝምታው የተቃውሞ ነው ለማለት ያስቸግራል :: ዝምታው የድጋፍ ቢሆን ነው ::

እየደገፉ ያሉትን ፓለቲካ ከዚህ በፊት ከነበረው እየከፋ ከሊቀመንበሩ መለስ ዜናዊ ሞት በኍላ "ዲፕሎማሲያዊ ' በመጠኑ ደሞ ስልታዊ ይመስል የነበረው ፓለቲካቸው የነበረችውንም ባህሪውን አጥቶ የዕውር የድንብር እየሄደ እንዳለ ሊቀመንበሩ ከሞተ በኍላ ያሉት ተከታታይ ፓለቲካዊ ሁነቶች በግልጽ እያሳዮ ነው :: በዚህ የመደናበር ሂደት ግን እየደረሰ ያለው ጥፋት ወደፊት በቀላሉ መመለስ የሚቻል ነገር ለመሆኑ እጠራጠራለሁ ::

ሕወሀት እና የህወሀት ደጋፊዎች እያደረሱት ያለው ጥፋት እና ህዝብ እየኖረው ያለውን የግፍ ጽዋ ለመታገል እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት ( እስከማውቀው ደረስ ) ተመጣጣኝ እይደለም ::

ክርስቲያኑ ቤተ -ክህነትን ከህወሀት ካድሬዎች አስረክቦ ከእጂ በደረት ብዙ በማይለይ ሁኔታ በተሽናፊነት ያመነ ይመስላል :: ጠንከር ያለው ተቃውሞ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኩል ስለነበረ ህወሀት በዛ ላይ የወሰደው ወታደራዊ የሚመስል ርምጃ የፓለቲካ ርምጃውና "በፍትህ ተቋማት "አማካይነት እየወሰደ ያለው ርምጃ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን የመብት ጥያቄ የሚያረግበው ስላልመሰለው ጉዳያቸውን ሌላ መልክ ለመስጠት እያደረግ ያለውን ነገር እያየን ነው :: ውሸት ጥላቻ እና ትምክህት የህግ እና የፓለቲካ ሽፋን እግኝቶ ;ውሸት እና ትምክህት ወታደራዊ ጥበቃ እየተደረገለት ስው በሀገሩ ባለቤት እንዳይሆን የተደረገበት ሁኔታ ሳያንስ : ጭራሽ መንፈሳዊ እምነቱንም ጭምር በጉልበት እንዲተው መደረጉን አስከፊነት ለመግለፅ ቋንቋ ያጥራል ::

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በስህተት 'ኤዲት ' ሳያደርግ ለቀቀው በተባለው ከታች ባለው የቪዲዮ ክሊፕ ላይ አፉን በውል የፈታ የማይመስል የህወት ሰው እጁን በካቴና አስረው ባዶ ክፍል ውስጥ ለምርመራ ያስቀመጡት ልጂ ላይ ሲሳለቁ ማየትም የሚፈጥረውን ስሜት ለመግለፀ እንዲሁ ቋንቋ ያጥራል ::

Clik here to watch the clip

የህወሀት ሰዎች እንዲህ የሚሳለቁበትን ልጂ ልጂ እያለን የማውቀው መልክ በመሆኑ ልቤ እጂጉን አዝኗል :: እሁንም ከሚያሳርፉበት ዱላ ከሚያደርሱበት ግርፋት የበለጠ የሚያሳዝነኝ እንዲህ እጁን እስረው የሚለፋደዱት ነገር ነው :: በዚህ ድርጊት ህወህትን ልታዘብ አልችልም :: ተው ይሄ ነገር ጥሩ አይደለም ሊሉ ያልቻሉትን ደጋፊዎቻቸውንም ወላጆቻቸውንም አልታዘብም ::
የማዝነው በራሳችን ነው -እንዲህ እንዲሆኑ በፈቀድንላቸው እና ስልጣኔ እና ያስተሳሰብ እድገት በሚመስል የባርነት እስተሳሰብ ለተናጥን::

Blog Archive